በዚህ ጽሑፍ በኢትዮጵያ የወንጅል ፍትሕ ሥርዓት ውስጥ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ሥር ስለመዋል ወይም ስለመያዝ የሚመለከቱ መሠረታዊ ጉዳዮችን ለማብራራት ጥረት ተደርጓል፡፡ በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠውን የሰዎች የነፃነት መብትና በፖሊስ በወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር ስለመዋል መካከል ስላለስ ግንኙነት በትንሹ ገለፃ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡ በተጨማሪም ተጠርጣሪዎች የሚያዙባቸውን መንገዶችና እንዴት በቁጥጥር ሥር እንደሚውሉ የሚደነግገውን የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ክፍል በጥልቀት ለመርመር ሙከራ ተደርጓል፡፡
“…ይቅርታ ይደረግልን አዲስ የኢትዮጵያ ባህል ነው፡፡”
የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕ/ት ኮ/ል መንግሥቱ ኃ/ማሪያም
መግቢያ
ይቅርታ በእለት ተእለት እንቅስቃሴችን ውስጥ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው እና ለማኅበራዊ ህይወታችንም ጥሩ መሆን እንዲሁም መልካም መስተጋብር ጉልህ ሚና እንደአለው የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡
መጠይቅ ደግ ነው፡፡ የአስፈጻሚ አካላት ሥልጣንና ተግባራትን ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 691/2003 አንቀጽ 16(6) ፍትሕ ሚኒስቴር በቂ ምክንያት ሲኖር በሕግ መሠረት ሂደት ላይ ያለን ክስ ያነሳል በሚል ይደነግጋል፡፡ ፍትሕ ሚኒስቴር የተሰጠው ክስ የማንሳት ሥልጣን እስከምን ድረስ ነው? ክስ ማንሳት በማንኛውም ጊዜ ይቻላል? ክሱን ሲያነሳስ በቂ ምክንያቱን ለፍርድ ቤቱ ያቀርባል? በቂ ምክንያትስ የምንለው ምንድን ነው? የክስ መነሳትስ ተከሳሾች ላይ ያለው ውጤት ምንድን ነው? በዚህ ሂደት የፍርድ ቤቶች ሚና ምን መሆን ይገባዋል? የሚለው ጥያቄ ሊመለስ የሚገባው ነው፡፡
አባትነትን በDNA በትክክል ማወቅ ይቻላል?
ስለ ኪሜራ ምን ያውቃሉ?
ሰላም እንዴት ናችሁ በማለት እስኪ ሙያችን በተመለከተ አንድ ቁምነገር ላንሳ፡፡
ሊዲያ ፌርቻይልድ አሜሪካዊ ሴት ናት። ሦስተኛ ልጇን እንደፀነሰች ከባሏ ጋር በፍቺ ትለያያለች። በፍቺ ወቅት ባሏ ለልጆቿ ማሳደጊያ ቀለብ እንዲቆርጥላት እንዲወሰንላት ለፍርድ ቤት ክስ ታቀርባለች። ፍርድ ቤቱም የወለደቻቸው ልጆቿ በትክክል ከባሏ ለመወለዳቸው የዲ ኤን ኤ ምርመራ እንዲደረግ ትእዛዝ ይሰጣል። ይሁን እንጂ ሁለቱም ልጆች ከባሏ መወለዳቸውን የዲ ኤን ኤ ምርመራ ውጤቱ ቢያረጋግጥም እሷ ግን የዘር እናታቸው (Biological Mother) አልነበረችም።
በአንድ ወቅት በፌደራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በታየ የስርቆት ወንጀል ጉዳይ ተከሳሹ ድርጊቱን መፈፀሙ ተረጋግጦ ጥፋተኛ ከተባለ በኋላ፣ የቅጣት አስተያየቱን እንዲሰጥ የተጠየቀው ዐቃቤ ሕግ ‹‹…ተከሳሽ ድርጊቱን የፈፀመው መጥፎ አመልን በሚያሳይ ሁኔታ በወስላታነት…›› መሆኑን ለፍርድ ቤት በማስታወስ ቅጣቱ ከብዶ እንዲወሰን ይጠይቃል፡፡ ይሄንን የሰማው ተከሣሽም ዐቃቤ ሕጉን አቋርጦ ‹‹ኧረ የተከበረው ፍርድ ቤት ዐቃቤ ሕጉ ራሱ ወስላታ ነው፣ መቀጣቴ ካልቀረ መሰደቤ ለምን?›› ብሎ መከራከሩን ሰምቻለሁ፡፡
በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ሥርአት ውስጥ የወንጀል ምርመራ አላማ ስለ ወንጀል የማወቅ፣ ወንጀል እንዳይፈፀም የማስቆም፣ ወንጀሉ ከተፈፀመ ጉዳቶችን የመቀነስ፣ የወንጀል ኢላማ የሆኑትን ሰዎች፣ ንብረቶች ወይም ጥቅሞችን የመከላከል፣ ወንጀል ፈፃሚዎችን ለሕግ የማቅረብ ወይም የወንጀል ተጎጂዎችን መብቶችና ጥቅሞችን ማስከበር እንደሆነ የኢትዮጵያ ወንጀል ፍትሕ ፖሊሲ ይገልፃል፡፡
የቅርብ ጓደኛው ጋር ተጠግቶ ይኖር የነበረ ግለሰብ፣ ጓደኛው በሌለበት አሳቻ ሰዓት 10000 ብር የሚገመት ቶሺባ ላፕቶፕ ወስዶ ለግል ጥቅሙ አውሏል በሚል የወንጀል ሕግ አንቀጽ 665(1)በመተላለፍ በስረቆት ወንጀል ተከሶ፣ ክሱን በዝርዝር በማመኑ ጥፋተኛ ይባላል::
የተዋጣለት የወንጀል ምርመራ ሥራ ለወንጀል ፍትሕ ሥርዓት መስፈን ቁልፍ የሆነ ሚና እንደሚጫወት በርካታ በወንጀል ምርመራ ሥራ ላይ የታተኮሩ መጽሐፍት የሚገልጹት ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን፡፡ በወንጀል ምርመራ ወቀት የተፈጸመ ወንጀልን ለማግኘት እና ጥፋተኛውን ለይቶ ለማውጣት ከሚጠቅሙ ቀዳሚ ነገሮች መካከል የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡
በእኛ ሀገር የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ተከሳሽ ምስክር መሆን ይችላል? ተከሳሽ ምስክር መሆን አለመሆን ጥቅምና ጉዳቱ ምንድነው?
በአንድ ወቅት አንድ አስታጥቄ የሚባል ሰው ማረሚያ ቤት ልንጠይቀው ሔደን የተናገረውን አልረሳውም፡፡ ይኼው ጓደኛችን በስድብና ማዋረድ፣ ዛቻና የእጅ እልፊት ወንጀሎች ስድስት ወር ቀላል እስራት ተወስኖበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከወረደ በኋላ፤ በክርከሩ ሂደት መመስከርና ምስክር መሆን አትችልም መባሉ እንዳሳዘነው ሲነገረን ተደንቄ ነበር፡፡
የተከበራችሁ አንባቢዎች ለዛሬው ርዕሰ አንቀፅ መነሻ የሆነኝ የውንብድና ወንጀልን የሚያቋቁሙ ፍሬ ነገሮች በአግባቡ ባለመረዳት ወይም በተለያዩ መልኩ በመተርጎም የሚፈፀሙ የክስ አመሰራረት ልዩነቶች ናቸው፡፡ በመሆኑም ያለውን አሰራር እና አንቀፁን እኔ በምረዳው መልኩ በማቅረብ ለአንባቢዎቼ እንደሚከተለው ለውይይት እና አስተያየት ክፍት አድርጊያለሁ፡፡