ሳፔቶ ሩባቲኖ የተባለ ኩባንያን በማቋቋም ወዲያው የባህር ንግዱን ማጧጧፍ ጀመረ፡፡ ከአሥራ ሁለት ዓመታት በኋላ የኢጣሊያ መንግሥት የጂቡቲን ጠረፋማ አካባቢ እንዲሁ በገንዘብ በመግዛት ከራስ ዱሜራ እስከ ራስ አሊ ከተቆጣጠረችው ፈረንሣይ ጋር ለመሻማት ኩባንያውን ከነካፒታሉ በመግዛት የአሰብን ጠረፋማ አካባቢዎች ተቆጣጠረ፡፡
ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ፀጋ የተከበበች ውብ ሀገር ብትሆንም በድህነት አዘቅት ውስጥ ተዘፍቃ የምትኖር፤ ባደጉ ሀገራት ተረፈ ምርትና የአየር ብክለት ገፈት ቀማሽነት፤ በሚጠጣ ንጹህ ውኃ እጥረት ተጠቂነት የምትነሳ ሀገር ነች፡፡ ኢትዮጵያ በመአድን፣ በለም መሬት፣ በእንስሳት፣ በውኃ ኃብት እንዲሁም በሌሎች አላቂና አላቂ ያልሆኑ የተፈጥሮ ሀብቶች ባለፀጋ መሆኗን የሚካድ ባይሆንም በተፈጥሮ የታደለችውን ኃብት ጥቅም ላይ ከማዋል ረገድ ግን እምብዛም አይደለችም፡፡ ሜዳዋንና ተራሯን የሚሸፍን የተፈጥሮ ዝናብ እየተቀበለች ይህ ዝናብ አፈሯንና ወርቋን ጠራርጎ በመውሰድ ለጎረቤት ሀገራት ነፃ ስጦታና ችሮታ እንዲሆን ከመፍቀድ ውጪ የልማት መንገዱን አልተገለጠላትም፡፡ ወንዞች በደራሽ ውኃ ተጥለቅልቀው የገበሬ ማሳ የጎርፍ ሲሳይ ሲያደርጉ ማየት ክረምት በመጣ ቁጥር የምንገነዘበው መራራ እውነት ነው፡፡ አባይን የሚያክል ግዙፍ የውሀ ኃብት ከጉሮሮዋ እየፈለቀቁ የራሳቸው ከርሰ ምድር ሲሞሉ ኢትዮጵያ የበይ ተመልካች ሆና መኖሯን ግርምት ይፈጥራል፡፡