ጸሐፊው በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዓቃቤ ሕግ ሲሆኑ በስልክ ቁጥር - 0914505008, 0947931110 ወይም ኢ-ሜይል wgebregziher@gmail.com ሊያገኟቸው ይችላሉ፡፡

ማቀባበል (Facilitating Act of Bribery)

(ለጉቦኞች አይላላኩ፤ ከተላኩ ዘብጥያ ይላካሉ!)

ይህ አጭር ጽሑፍ በማወቅም ባለማወቅም የወንጀል አድራጊዎች ተልእኮ የሚያስፈጽሙ ሰዎች እንዲጠነቀቁ ለማስቻል በግርድፉ የቀረበ ነው፤ ጥልቀት ያለው ትንተና እንዳይጠብቁ። ጽሑፉ ሰዎች የቆሸሸ ገንዘብ የሚያቀባብሉበት እጃቸው፣ እንዲሁም የጉቦኞች የገንዘብ መላላኪያ የሚያደርጉት የባንክ ሂሳብ ቁጥራቸው አደገኛ መዘዝ ይዞባቸው እንዳይመጣ ሊጠነቀቁ ይገባል የሚል መልእክት ለማስተላለፍ፣ ምናልባትም ለማስጠንቀቅ የቀረበ የሕጉ አጭር መግለጫ ነው። ለሕግ ሙያተኞች ፈጽሞ ጥቅም የለውም ማለት ባይቻልም ዓይነተኛ ጥቅሙ ግን ከሙያው ዓለም ውጪ ላለው ለተራው ማኅበረሰብ ነው። ጽሑፉ ስለማቀባበል የሙስና ወንጀል ውስን የግንዛቤ ማስጨበጫ ነጥቦችን በመያዝ ተዘጋጅቷል። ሕግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንምና ይነበብ።

Continue reading
  1254 Hits

የኢትዮጵያና የግብፅ ውጥረት በናይል ወንዝ፡ ከዓለም አቀፍ ሕግ አንጻር

 

 

1)  መግብያ

ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ፀጋ የተከበበች ውብ ሀገር ብትሆንም በድህነት አዘቅት ውስጥ ተዘፍቃ የምትኖር፤ባደጉ ሀገራት ተረፈ ምርትና የአየር ብክለት ገፈት ቀማሽነት፤በሚጠጣ ንጹህ ውኃ እጥረት ተጠቂነት የምትነሳ ሀገር ነች፡፡ ኢትዮጵያ በመአድን፣ በለም መሬት፣ በእንስሳት፣ በውኃ ኃብት እንዲሁም በሌሎች አላቂና አላቂ ያልሆኑ የተፈጥሮ ሀብቶች ባለፀጋ መሆኗን የሚካድ ባይሆንም በተፈጥሮ የታደለችውን ኃብት ጥቅም ላይ ከማዋል ረገድ ግን እምብዛም አይደለችም፡፡ ሜዳዋንና ተራሯን የሚሸፍን የተፈጥሮ ዝናብ እየተቀበለች ይህ ዝናብ አፈሯንና ወርቋን ጠራርጎ በመውሰድ ለጎረቤት ሀገራት ነፃ ስጦታና ችሮታ እንዲሆን ከመፍቀድ ውጪ የልማት መንገዱን አልተገለጠላትም፡፡ ወንዞች በደራሽ ውኃ ተጥለቅልቀው የገበሬ ማሳ የጎርፍ ሲሳይ ሲያደርጉ ማየት ክረምት በመጣ ቁጥር የምንገነዘበው መራራ እውነት ነው፡፡ አባይን የሚያክል ግዙፍ የውሀ ኃብት ከጉሮሮዋ እየፈለቀቁ የራሳቸው ከርሰ ምድር ሲሞሉ ኢትዮጵያ  የበይ ተመልካች ሆና መኖሯን ግርምት ይፈጥራል፡፡

ናይል የሚባለው የአለም ረዥሙ ወንዝ ላይ ያለው ውኃ 85%ቱ የኢትዮጵያ ነው፡፡ ይሁንና ከ50% በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ኑሮውን በኩራዝ መብራት ይመራል፡፡ ይህ ክስተት ወገብን ይቆርጣል፡፡ ”ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል” እንዲሉ ግብፅ በናይል ወንዝ ላይ 5% እንኳን አስተዋፅኦ ሳታደርግ በምስራቅም በምእራብም የዚሁ ወንዝ ብቸኛ አለቃ ነኝ በማለት በሌሎች የናይል ተፋሰስ ሀገራት ላይ የምትሰነዝረው ዛቻና ማስፈራርያ የሚያስገርም ነው፡፡ የናይል ወንዝ ብቸኛ ባለቤት እንደሆነች በመግለፅ አሁናዊ ተጠቃሚነቷን የሚነካ ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴ የደም መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ እንደሆነች በተለያዩ አጋጣሚዎች ስትገልፅ መስማት የተለመደ ሆኗል፡፡ ሆኖም ኢትዮጵያ የግብፅ ሽለላና ቀረርቶ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት በግዛታዊ ክልሏ ውስጥ በሚገኝ በጥቁር አባይ ላይ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ጀምራ ከ70% በላይ ማድረሷን ይታወቃል፡፡ በሌላ በኩል ይህ ግድብ ለግብፅ ራስ ምታት እንደሆነባት፤ኢትዮጵያ የያዘቸውን የልማት መንገድ ለማደናቀፍም ያልፈነቀለችው ድንጋይ እንደሌለ፤በቀጣይም የማትቆፍረው ጉድጓድ እንደማይኖር ኢትዮጵያውያን የምንገነዘበው እውነት ነው፡፡ የናይል ወንዝ በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል የፈጠረውን ውጥረት በተለያዩ ወቅቶች የውጭና የሀገር ውስጥ ሚድያዎች ርእሰ ዜና በመሆን የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ቀልብ መሳብ የቻለ፤አሁንም ውጥረቱ በስምምነት ያልተቋጨ ክስተት ሆኖ ቀጥሏል፡፡

Continue reading
  7787 Hits

የሰበር ዓላማ ወጥነትን ማስፈን ወይስ ሕገ-ወጥነትን ማስፋፋት?

 

ጊዜው እ.ኤ.አ 1954 ነው፡፡ ለአለም ሀገራት የዲሞክራሲ አርአያና መምህር ነኝ ብላ በምትደሰኩር በአሜሪካ ሀገር ነጭና ጥቁር ተማሪ በአንድ ላይ አይማርም ነበር አሉ፤ ምክንያቱም ጥቁር ተማሪ ከነጭ ተማሪ ጋር በአንድ ላይ እንዲማር መፍቀድ ማለት በነጭ ተማሪዎች ሞራልና ክብር መቀለድ ነው ብላ ታምን ነበር፤ አሜሪካ፡፡ በመሆኑም ጥቁሮችና ነጮች ተለያይተው ይማሩ ነበር ማለት ነው፡፡ በዚሁ አይን ያወጣ አድልዎ የተበሳጨው ብራውን የተባለው ግለሰብ በአሜሪካ ሀገር የካንሳስ ክልል የትምህርት ጉዳይ ቦርድን በፍርድ ቤት ገተረው፡፡ ሚስተር ብራውን ለጥቁሮች ሽንጡን ገትሮ ከተከራከረ በኃላ ጥቁሮችን አንገት የሚያቀና ፍርድ አስፈረደ፡፡ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥቁርና ነጭ ተማሪዎች ተለያይተው እንዲማሩ ማድረግ የሰው ልጆች በተፈጥሮ እኩል ሆኖው የመፈጠር መብትን የሚቃረን በተለይም ደግሞ የጥቁሮች ክብርና ሞራል የሚነካ እኩል የትምህርት እድል የሚነፍግ ህገ ወጥ ድርጊት በመሆኑ ከተፈጥሮ ሕግና የአሜሪካ ህገ መንግስት ጋር የሚጣረስ ነው ሲል ለሰው ልጆች እኩልነት የሚያረጋግጥ ፍርድ ሰጠ፡፡ ጥቁሮች ከነጮች ጋር ያለአድልዎና ልዩነት ሳይደረግባቸው እኩል የትምህርት እድል የማግኘትና የመማር መብት አላቸው የሚል መደምደሚያ ላይ ተደረሰ፡፡ በዚሁ ውሳኔ የተበሳጨው "ጆርጅያ ኩሪዬር" የተባለ ጋዜጣ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ዳኞችን እንዲህ ሲል ገለፃቸው፡፡

“No man knows today what his rights are in this country. No man today has any liberties left. His rights and his liberties are in the laps of the nine crazy men who sit on the Supreme Court bench. And the lord only knows what these crazy men will do next. Today they are most dangerous tyrants that ever existed. Like Hitler, Mussolini, and the other modern day tyrants, they are mentally deranged. They are crazed with a desire to serve a minority for political purposes. Their insanity has made them unscrupulous in the methods they have employed to do the bidding of this minority. They are mentally deranged tyrants ruling as unscrupulously as any tyrant in all of history. The members of this court must be curbed or they must be removed from the bench.”

ትችቱ ወደ አማርኛ ስንመልሰው በዚች ሀገር መብቱን እና ነፃነቱን የሚያውቅ ሰው የለም፡፡ ነፃነቱንና መብቱን በጠቅላይ ፍርድ ቤት ወንበር ቁጭ ባሉ በእነዚህ  ዘጠኝ ያበዱ ዳኞች እጅ ላይ ነው፤በቀጣይም እነዚህ እብድ ዳኞች የሚሰሩት ነገር ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡ አሁን በዘመናችን አይተነው በማናውቅ ሁኔታ እነዚህ ዳኞች አደገኛ አምባገነኖች ናቸው፤እንደ እነ ሂትለር፣ሙሶሎኒና ሌሎች ዘመናዊ አምባገነኖች በጭካኔ ያበዱ ናቸው፤ለፖሊቲካ አላማ ሲባል አናሳ ማህበረሰብን ለማገልገል አብደዋል፡፡ እብደታቸውን አናሳውን ለማገልገል ይሉኝታ እንኳን ሊገድበው አልቻለም፤እነዚህ ሰዎች ሊወገዱ ይገባል ለማለት ነው፡፡ (ትርጉም የራሴ)

እኔ ደግሞ እላለሁኝ፡፡ ያበዱት ዳኞቹ ሳይሆን ጋዜጣውን ያወጣው ፀኃፊ ራሱ ነው፡፡ ይህ ጋዜጣ በወቅቱ ይዞት የወጣ ትችት ብሽቅ እና በዘረኝነት የተነዳ ከአንድ ዲሞክራሲያዊት ሀገር ፈፅሞ የማይጠበቅ ነው፡፡ የእብደት እብደት፡፡ ይህ ማለት ከፍትህ እና ከእኩልነት አንፃር የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ከትክክልም በላይ ነበር፡፡

Continue reading
  6830 Hits

ደረሰኝ አለመቁረጥ እና የወንጀል ተጠያቂነት

 

(‘ደረሰኝ የማይሰጥ ከሆነ አይክፈሉ')

ረሰኝ  ምን ማለት ነው?

የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 19፣120 እና 131(1)(ለ) እንዲሁም የፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀጽ 82 ላይ የተደነገጉ ድንጋጌዎችን ጣምራዊ ንባብ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸው ሕጎች  መሠረት በማድረግ የደረሰኝ ትርጉም እና ምንነት፣ የደረሰኞች ዓይነቶች እና ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ ያለባቸው ግብር ከፋዮችን እነማን እነደሆኑ እንዲሁም ደረሰኝ መሰጠት ያለበት መች እንደሆነ በወፍ በረር መልኩ ለመዳሰስ እሞክራለሁኝ፡፡

ደረሰኝ ማለት የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ያለበት ማንኛውም ታክስ ከፋይ ከደንበኞቹ ጋር ለሚያከናውነው ግብይትና ለሚሰበስበው ገንዘብ እውቅና የሚሰጥ ሕጋዊ ሰነድ ለደንበኞቹ ቆርጦ በመስጠት በመንግስት የተጣለበትን ግብር የማስከፈል እና የመክፈል ግዴታው የተወጣ ስለ መሆኑ የሚረጋገጥበት  የማረጋገጫ ወረቀት ነው፡፡ የሽያጭ መመዝገብያ መሣርያዎች ስለመጠቀም ለመደንገግ በሚኒስትሮች ምክርቤት የወጣ ደንብ ቁጥር 139/2007 አንቀጽ 2(3) ላይም ደረሰኝ (Receipt) ማለት የጥሬ ገንዘብ ሽያጭ ሲሆን፣ የዱቤ ሽያጭ ኢንቮይስና ያለክፍያ የሚሰጥ እቃ ወይም የአገልግሎት ማስተላለፍያ ደረሰኝን ይጨምራል በማለት ይደነግጋል፡፡በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008  አንቀጽ 19(3) መሠረት የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ያለበት ማንኛውም ግብር ከፋይ ደረሰኝ እንዲሰጥ ይገደዳል፡፡የደረሰኙ አይነት በህግ መሠረት የሚወሰን ሆኖ ማንኛውም ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ ያለበት ግብር ከፋይ ካለደረሰኝ ግብይት ካከናወነ እንደየሁኔታው በአንቀጽ 120 ወይም በአንቀጽ 131(1)(ለ) መሠረት በወንጀል ይጠየቃል፡፡

Continue reading
  15779 Hits