- Details
- Category: Advertise with Us
- Abyssinia Law | Making Law Accessible! By
- Hits: 378
የሙስና ወንጀሎች ሕግጋትና አተገባበራቸው በኢትዮጵያ - የሚል አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ ዋለ
የመጽሐፉ ርዕስ፡ “የሙስና ወንጀሎች ሕግጋትና አተገባበራቸው በኢትዮጵያ” (የመሠረታዊ፣ የሥነ ሥርዓትና የንብረት ማስመለስ ሕግጋት ከሰበር ውሳኔዎች፣ ከዓለም አቀፍ ስምምነቶችና ልምዶች ጋር በማነጻጸር የተዘጋጀ)
የመጽሐፉ አዘጋጅ፡- ገብረእግዚአብሔር ወልደገብርኤል ስልክ ቁጥር 0914505008
የመጽሐፉ ጠቅላላ ገጽ 416
መጽሐፉ በስምንት ምዕራፎች የተከፈለ ነው።
በመጽሐፉ ውስጥ ከሙስና ወንጀሎች መሰረታዊ፣ የሥነ ሥርዓትና የንብረት ማስመለስ ሕግጋት ጋር በተያያዘ የታተሙ 78 ያልታተሙ 27 በድምሩ 105 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ ውሳኔዎች ተካተዋል። ይህ ማለት በሙስና ወንጀሎች ዙሪያ የተሰጡ ሁሉንም የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች (Exhaustively) የዚህ መጽሐፍ የትንታኔ አካል ሆነዋል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በርካታ የሙስና ወንጀል የክርክር መዛግብት ላይ የሰጣቸውን ውሳኔዎች በመጽሐፉ ውስጥ የተካተቱና ትንተኔ የተሰጠባቸው ከመሆኑ ባለፈ ጸሐፊው ከባባድና ውስብስብ የሙስና ወንጀሎች ምርመራን በመምራት፣ ውሳኔ በመስጠትና በመከራከር ሂደት ላይ በቀጥታ የተሳተፈባቸው፣ በአካልም የታዘባቸው (Observations) በሙሉ የመጽሐፉ የትንተና አካል ሆነዋል።
መጽሐፉ የተለያዩና የተመረጡ የዓለም ሀገራት የጸረ ሙስና ብሔራዊ ሕግጋትና አተገባበር እንዲሁም ኢትዮጵያ ፈርማ የሕጎቿ አካል ያደረገቻቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸረ ሙስና ኮንቬንሽን (UNCAC)፣ የአፍሪካ ሕብረት የሙስና መከላከያና መዋጊያ ኮንቬንሽን እንዲሁም ሌሎች ስምምነቶች፣ ፕሮቶኮሎች… በማካተት በርካታ የተዛማጅ ጽሑፍ ክለሳ በማድረግ ከንድፈሐሳባዊ ፍልስፍናዎች አንጻር ሰፊ ትንተና የተደረገበት ነው።
መጽሐፉ በተግባር ላይ የተመሰረቱ ተጨባጭ ማስረጃዎችን (Empirical evidences) መሰረት በማድረግ በርካታ አዳዲስ ግኝቶችን ይዞ የቀረበ (Exploratory kind of research) ነው። በመሆኑም ለዳኞች፣ ለጠበቆች፣ ለዓቃቤያነ ሕግ፣ ለዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎች፣ ለአጥኚዎችና ተመራማሪዎች፣ ለማንኛውም የሕግ ባለሙያ እንዲሁም ሕግን አለማወቅ ከተጠያቂነት እንደማያድን ታውቆ ሕግን ማወቅ ግዴታው ለሆነው ለማንኛውም ሰው ጠቀሜታው ከፍ ያለ ነው። በኢትዮጵያ ተጠያቂነት፣ ፍትሕና የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን ለሚተጋ ሁሉ መጽሐፉን ቢያነብ ያተርፍበታል።
- Details
- Category: Advertise with Us
- Abyssinia Law | Making Law Accessible! By
- Hits: 10837
የኢትዮጵያ የባንክ እና የሚተላለፉ የንግድ ሰነዶች ሕግ (Ethiopian Banking and Negotiable Instruments Law) በሚል በቅርቡ የታተመው መጽሐፍ በገበያ ዋለ
Read more: የኢትዮጵያ የባንክ እና የሚተላለፉ የንግድ ሰነዶች ሕግ የሚል አዲስ መጽሐፍ በገበያ ዋለ
- Details
- Category: Advertise with Us
- Abyssinia Law | Making Law Accessible! By
- Hits: 10377
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ
"የግልግል ዳኝነት በኢትዮጵያ ሕግ" የሚል ርዕስ ያለው አዲስ የሕግ መጽሐፍ በገበያ ላይ ውሏል፡፡ መጽሐፉ አቶ ሲራክ አካሉ እና አቶ ሚካኤል ተሾመ በተባሉ ሁለት ወጣት የሕግ ሙሁራን የተፃፈ ነው፡፡ መጽሐፉ 326 ገጽ ያለው ሲሆን ዋጋው 77 ብር ነው፡፡ መጽሐፉ በሜጋ መጽሐፍት መሸጫ መደብር ያገኙታል፡፡
Read more: "የግልግል ዳኝነት በኢትዮጵያ ሕግ" የሚል ርዕስ ያለው አዲስ የሕግ መጽሐፍ በገበያ ላይ
- Details
- Category: Advertise with Us
- Abyssinia Law | Making Law Accessible! By
- Hits: 8311
As the Internet becomes more prevalent in our society, it has become common place to turn to the Internet for shopping, finding directions, researching products, and even to find a church or seek answers to spiritual questions. As businesses and other organizations begin to understand this dynamic, they are increasingly beginning to recognize the importance and the need for an effective web presence – not just a web site, but a real presence on the web.