- Details
- Category: About the Law - ስለሕጎቻችን
ሰላም የአቢሲኒያ ሎው ድረገጽ ተከታታዮች፤ እንዴት ናችሁ!
1. የሚፈልጉትን ማናቸውንም ሕግ ወይም የሰበር ውሳኔ መፈለጊያ ውስጥ በተየባችሁ (ታይፕ ባደረጋችሁ) በአንድ ሰከንድ ውስጥ ቢያገኙ ምን ይሰማዎታል?
2. የአንድን ሕግ ሁኔታ ማለትም ይሻር፣ ይሻሻል ወይም ተፈፃሚ ይሁን በአንድ ሰከንድ ጊዜ ውስጥ ቢያገኙ ምን ያህል ሥራዎትን ያቀላል?
3. የሰበር ውሳኔዎችን በመዝገብ ቁጥራቸው ወይም በተከራካሪ ወገኖች ስም ብቻ ሳይሆን በክርክሩ ወይም ውሳኔው ውስጥ በተጠቀሰው አዋጅ ወይም ሕግ አንቀጽ ፈልገው ቢያገኙ ምን ያህል ይደነቃሉ?
- Abyssinia Law | Making Law Accessible! By
- Hits: 31499
- Details
- Category: Inapplicable Provisions - ተፈፃሚነት ያላገኙ ድንጋጌዎች
የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ከቁጥር 132 እስከ 135 ድረስ ምትክ ዳኞች /Judicial Commissioners/ በፍርድ ቤቶች ስለሚሾሙበት፣ የሥራ ኃላፊነታቸው ምን እንደሆነና ሌሎች ተያያዥ ነጥቦችን ያስቀምጣል፡፡ ለመሆኑ የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ምትክ ዳኞችን አስመልክቶ የሚያስቀምጣቸው ነጥቦች ምንድን ናቸው? ለተከራካሪ ወገኖች የምትክ ዳኞች መሾም አስፈላጊነቱ ምንድን ነው? ሕጉ በተግባር እየተፈፀመ ነው ወይ? የሚሉና ሌሎች ነጥቦችን እንዳስሳለን፡፡
- Abiyou Girma Tamirat By
- Hits: 13116
- Details
- Category: Inapplicable Provisions - ተፈፃሚነት ያላገኙ ድንጋጌዎች
በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 112 እና 113 መሠረት በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ በምስክርነት የሚቀርቡ ምስክሮች ለምስክርነት ወደ ፍርድ ቤት በሚመጡበት ጊዜ ለመጓጓዣ እና ሌላ የቀን ወጪ የሚሆን ገንዘብ ሊከፈላቸው እንደሚገባ፤ ለምስክርነት የሚመጣው ሰውም የባለሙያ ምስክር ከሆነ የሚሰጠው ምስክርነት እንደሚፈጀው ጊዜ እና አድካሚነት ተጨማሪ አበል ሊከፈለው እንደሚገባ፤ ለምስክሮቹ ወጪ የሚከፈለው ገንዘብ አከፋፈል ፍርድ ቤቱ በሚያዘው ሁኔታና ጊዜ መሠረት እንደሚሆን እንዲሁም ለምስክሮች የሚቀመጠው ገንዘብም የማይበቃ ከሆነ ፍርድ ቤት ተጨማሪ አበል ሊያዝ እንደሚችል ተመልክቷል፡፡ በተጨማሪም ለምስክሮች የሚከፈለውን አበል መክፈል ያለበት አስመስካሪው ወይም እንዲመሰከርለት የሚፈልገው ተከራካሪ ወገን መሆኑንና ተከራካሪው ፍርድ ቤቱ ለምስክሮች እንዲከፍል ያዘዘውን የምስክሮች ወጪ ለመሸፈን እምቢተኛ ከሆነ ፍርድ ቤቱ የተከራካሪው የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ተሸጦ እንዲከፈል ወይም የተጠራው ምስክር ቃሉን ሳይሰጥ እንዲመለስ ወይም ሁለቱንም አጣምሮ ሊወስን እንደሚችል ተመልክቷል፡፡
- Abiyou Girma Tamirat By
- Hits: 11821
- Details
- Category: Inapplicable Provisions - ተፈፃሚነት ያላገኙ ድንጋጌዎች
በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 97 መሠረት ኤግዚቢት ወይም ከወንጀል አፈፃፀም ጋር በተያያዘ ወንጀል የተፈጸመበት ወይም ወንጀል ለመፈጸም በመሣሪያነት የዋሉ ቁሶች (ነገሮች) እንዴት ሊቀመጡና በማስረጃነት ሊያገለግሉ እንደሚገባ ተመልክቷል፡፡
በዚሁ መሠረት ኤግዚቢቶች ላይ የፍርድ ቤት መዝገብ ሹም ቁጥርና ምልክት አድርጎባቸው በተጠበቀ ስፍራ ሊያስቀምጣቸው እንደሚገባና ከተቀመጡበት ስፍራም ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደማይወጡ ተመልክቷል፡፡ ሆኖም በተግባር ፍርድ ቤቶች በወንጀል ጉዳዮች በኤግዚቢትነት የሚያዙ ንብረቶችን ተቀብለው አይመዘግቡም በተጠበቀ ስፍራም አያስቀምጡም፡፡
- Abiyou Girma Tamirat By
- Hits: 12219
- Details
- Category: Inapplicable Provisions - ተፈፃሚነት ያላገኙ ድንጋጌዎች
በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 148 (1) እና (2) ላይ እንደተደነገገው በወንጀል ጉዳዮች ላይ ማስረጃ ተሰምቶ ካበቃ በኋላ ዐቃቤ ሕግ እና ተከሳሽ ስለሕጉ፣ ስለነገሩ እና ስለማስረጃዎች ሁኔታ የክርክር ማቆሚያ ንግግር ያደርጋሉ፡፡ ይህንን ድንጋጌ ተከትሎ ከጥቂት ችሎቶች በስተቀር ፍርድ ቤቶች በሕጉ መሠረት ማስረጃ ተሰምቶ ሲያበቃ ዐቃቤ ሕግና ተከሳሽ የክርክር ማቆሚያ ንግግር እንዲያቀርቡ ያደርጋሉ፡፡
- Abiyou Girma Tamirat By
- Hits: 13349
- Details
- Category: Inapplicable Provisions - ተፈፃሚነት ያላገኙ ድንጋጌዎች
በ1992 ዓ.ም ወጥቶ በሥራ ላይ ያለው የፌዴራል ፍርድ ቤት ጠበቆች ፈቃድ አሰጣጥና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 199/1992 ማንኛውም ሰው የጥብቅና ፈቃድ ሳይኖረው የጥብቅና አገልግሎት መስጥ እንደማይችል በመደንገግ ፈቃድ እንዴት እንደሚገኝ፣ ፈቃድ ለማግኘት መሟላት ስላለባቸው መስፈርቶች፣ የፈቃድ ዓይነቶች፣ ፈቃድ ስለሚሰጥበት አኳኋን፣ ፈቃድ ስለማደስ፣ ስለመመለስ፣ ስለመሰረዝ እና ከዚሁ ጋር የተገናኙ ሌሎች ዝርዝር ነገሮችን አካትቶ ይዟል፡፡
- Abyssinia Law | Making Law Accessible! By
- Hits: 15381
Inapplicable Provisions - ተፈፃሚነት ያላገኙ ድንጋጌዎች Article Count: 5
በዚህ ክፍል አንድን ችግር ለመፍታት ወይም አንድን ድርጊት ለመቆጣጠር ከወጡ ሕጎች መካከል ሕጉ በሚፈልገው መጠን ያልተተገበሩ የሕግ ድንጋጌዎችን እንዲሁም ዝርዝራቸው በሕግ ይወሰናል ተብሎ ያልተወሰኑ ድንጋጌዎችን እንዳስሳለን፡፡ የዚህ ክፍል ዓላማ ለኅብረተሰቡ፣ ለሕግ አውጪው፣ ለሕግ አስፈጻሚው እና ለሕግ ተርጓሚው እየተሠራባቸው ስላልሆኑ የሕግ ድንጋጌዎች በማሳወቅ ድንጋጌዎቹ ወደ ተግባር የሚቀየሩበትን መንገድ ማመላከት ነው፡፡
Laws that need amendment - መሻሻል የሚገባቸው ሕጎች Article Count: 2
በዚህ ክፍል አንድን ጉዳይ አስመልክቶ ከወጡ ሕጎች (ድንጋጌዎች) መካከል ከሕጉ ዓላማ፣ የሕጉ አፈፃፀም እያደረሠ ካለው ችግር፣ ከሕጉ ኋላ ቀርነት፣ ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮዎችና ሌሎች ነጥቦች አንፃር ተጨባጭና ምክንያታዊ መከራከሪያዎችን በማንሳት ሊሻሻሉ ይገባል የምንላቸውን ድንጋጌዎች እንዳስሳለን፡፡ የዚህ ክፍል ዓላማ ለሕግ አውጪው ሊሻሻሉ የሚገባቸውን የህግ ድንጋጌዎች (ሕጎች) ከነምክንያታቸው ማመላከትና የሚሻሻሉበትን ሁኔታ መጠቆም ነው፡፡
Matters that need enactment - ሕግ ሊወጣላቸው የሚገቡ ጉዳዮች Article Count: 1
በዚህ ክፍል በኢትዮጵያ ሕጎች ውስጥ ሽፋን ያላገኙ ግን ደግሞ በኅብረተሠቡ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ሕግ የማያውቃቸው ጉዳዮች ሕግ ባለመውጣቱ የተነሳ እየደረሱ ያሉ ችግሮችንና ምርጥ ተሞክሮዎችን በማንሳት ሕግ ሊወጣላቸው ይገባል የምንላቸውን ጉዳዮች እንዳስሳለን፡፡ የዚህ ክፍል ዓላማ ለሕግ አውጪው ሕግ ሊወጣላቸው የሚገቡ ጉዳዮች ከነምክንያታቸው ማመላከትና ሕግ የሚወጣበትን ሁኔታ መጠቆም ነው፡፡
Page 1 of 2