- Details
- Category: Laws that need amendment - መሻሻል የሚገባቸው ሕጎች
- Sentayehu Getachew By
- Hits: 17512
የህሊና ጉዳት ካሳ የተጎጂውን የስሜት መጎዳት ከግንዛቤ ባስገባ ሁኔታ መወሰን እንዳለበት ብዙዎቹ ይስማማሉ። የህሊና ጉዳት በተጎጂው ላይ የደረሰውን የስሜት መጎዳት፥ የስነ-ልቦና ጉዳት፥ ሐዘን፥ ሀፍረት፥ ውርደት ወዘተ... የመሳሰሉትን ጉዳቶች ያካትታል።
ይሁን እንጂ በፍታብሔር ሕጉ ካሳ የሚያስገኙ የህሊና ጉዳት ዓይነቶች እና ለህሊና ጉዳት የሚከፈለው የካሳ መጠን የጉዳት ካሳ መርህን በሚቃረን መልኩ የተጎጂውን ተገቢውን ካሳ የማግኘት መብት የሚያጣብብ ነው የሚል እምነት አለኝ። ለዚህም ምክንያት የማደርገው፦
- Details
- Category: Laws that need amendment - መሻሻል የሚገባቸው ሕጎች
- Abiyou Girma Tamirat By
- Hits: 23447
የኮንዶሚኒየም ቤትን (የጋራ ህንፃን) አስመልክቶ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 370/1995 ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስተዳደሩን ቤቶች የማስተላለፍ ኃላፊነትና አፈፃፀሙን ለመወሰን በወጣው አዲስ ነጋሪት ጋዜጣ አዋጅ ቁጥር 19/97 አንቀፅ 14 (2) ላይ የኮንዶሚኒየም ቤት እጣ የደረሰው ሰው ዕጣው ከደረሰው ቀን አንስቶ እስከ አምስት ዓመት ድረስ ለሶስተኛ ወገን በሽያጭ ወይም በስጦታ ለማስተላለፍ የማይችል ስለመሆኑ ተመልክቷል፡፡ ባለ እጣው እጣ ከደረሠው ቀን ጀምሮ አምስት ዓመታት ሳይሞላ ቤቱን አስመልክቶ በማናቸውም ሁኔታ የባለቤትነት መብቱን ለማስተላለፍ ውል እፈፅማለሁ ቢል የሠነዶች ማረጋገጫ ፅ/ቤት በዚህ ሕግ መሠረት አምስት ዓመት ሳይሞላ ማስተላለፍ እንደማይቻል በመግለፅ ተዋዋዮችን ይመልሳል፡፡