የህሊና ጉዳት ካሳ (ህሊና ዋጋው ምን ያህል ነው?)
የህሊና ጉዳት ካሳ የተጎጂውን የስሜት መጎዳት ከግንዛቤ ባስገባ ሁኔታ መወሰን እንዳለበት ብዙዎቹ ይስማማሉ። የህሊና ጉዳት በተጎጂው ላይ የደረሰውን የስሜት መጎዳት፥ የስነ-ልቦና ጉዳት፥ ሐዘን፥ ሀፍረት፥ ውርደት ወዘተ... የመሳሰሉትን ጉዳቶች ያካትታል።
ይሁን እንጂ በፍታብሔር ሕጉ ካሳ የሚያስገኙ የህሊና ጉዳት ዓይነቶች እና ለህሊና ጉዳት የሚከፈለው የካሳ መጠን የጉዳት ካሳ መርህን በሚቃረን መልኩ የተጎጂውን ተገቢውን ካሳ የማግኘት መብት የሚያጣብብ ነው የሚል እምነት አለኝ። ለዚህም ምክንያት የማደርገው፦