ወይኖን ግረፈው ኳሊ እንዲሰማህ፤ የወንጀል ኢኮኖሚክስ ክፍል ሁለት

 

1.  የመያዝና የመቀጣት እድል፤ ማጅራት መቺዎችን እና ቤት ሰርሳሪዎችን ከተማን በማጽዳት እንዋጋቸው ወይኖን ግረፈው ኳሊ እንዲሰማህ እና ሌሎችም አሳቦች

1.1 አጠቃላይ

ማስታወሻ ለአንባቢ፤ ይህ በወንጀል ኤኮኖሚክስ ዙሪያ የጻፍኩት ሁለተኛው ጽሑፌ ነው፡፡ የመጀመሪያውን ክፍል እዚህ ማግኘት ይቻላሉ:: አሳቦቼን ለማስረዳት ስል አንዳንዴ ተጓዳኝ ጉዳዮችን እያነሳው ባወራም፤ የዋናው ሃሳብ ፍሰት አይዛባም የሚል ዕምነት አለኝ፡፡

በመጀመሪያው የጽሑፉ ክፍል የተቀመጠው ቀመር ሌላኛው አካል የመያዝና የመቀጣት እድልን መጨመር ነው፡፡ ለማስታወስ ያህል ቀመሩ ይህ ነው፤

Continue reading
  12341 Hits

እያመለጠ ያለን የጊዜ ቀጠሮ እስረኛ ተኩሶ መግደል በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ

 

መግቢያ

አንድ ሰው ወንጀል በመስራት በመጠርጠሩና የተጠረጠረበት ወንጀል በሕጉ ዋስትና የማያስፈቅድ በመሆኑ ወይም በዋስትና ለመውጣት አስፈላጊ የሆኑት ነገሮች እስኪከናወኑ ጊዜ ድረስ በእስር ላይ ሊቆይ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ እስረኛው በሕጉ የተፈቀደለት የሰብአዊ ክብር እንክብካቤና በሕይወት ለመቆየት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች በሙሉ እየተሟሉለት የፍርድ ሂደቱን የመከታተል መብት አለው፡፡ እስረኛው በፍ/ቤት ወንጀለኛ ተብሎ ያልተፈረጀ ይልቁንስ በህገመንግስቱ አንቀፅ 20/3/ መሠረት ንፁህ ሆኖ የመገመት መብት ያለው በመሆኑ ተገቢው ክብርና እንክብካቤ የሚገባው ነዉ፡፡

የዚህ ጽሑፍ መነሻ በአንድ በተጠረጠሩበት ወንጀል ምክንያት የታሰሩ ሰዎች የታሰሩበት እስር ቤት በራሳቸው ባልሆነ ጥፋት በእሳት እየተቃጠለ በመሆኑ ምክንያት ከሚነደው የእሳት ቃጠሎ ራሳቸውን ለማዳን ሲሉ በሕግ ወንጀልነቱ የተደነገገ ሌላ ወንጀል ፈፅመው ቢገኙ ለምሳሌ ከታሰሩበት እስር ቤት ለማምለጥ ቢሞክሩ የእስር ቤቱ ጠባቂ ይህን የማምለጥ ድርጊት ለማቆም የሚወስደው የግድያ ተግባር በወንጀል ሕጉ መሠረት ያለውን ህጋዊነት መፈተሽ ነው፡፡

ቅጣት አልባው ወንጀል

Continue reading
  25066 Hits
Tags:

ሕዝባዊ የግዴታ አገልግሎት መስጠት (የግዴታ ሥራ) እንደ ወንጀል ቅጣት

 

ጣልያንን ለዘጠኝ ዓመታት የመሩት የቀድሞው የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የኤሲ ሚላን እግር ኳስ ክለብ ፕሬዚዳንትና ባለቤት እንዲሁም ቢሊየነሩ ሲልቪዮ ቤርሎስኮኒ በተከሰሱበት የታክስ ማጭበርበር ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው በሚላን ከተማ የሚገኘው ፍርድ ቤት ቤርሎስኮኒ የአራት ዓመታት እስራት ቢፈረድባቸውም የእስራት ቅጣቱ በተለያዩ ምክንያቶች ቀርቶ በተቃራኒው ቤርሎስኮኒ በአረጋውያን ማቆያና መንከባከቢያ ማዕከል ውስጥ ሕዝባዊ የግዴታ አገልግሎት እንዲሰጡ እ.ኤ.አ. በ2013 መወሰኑ ይታወቃል፡፡ በውሳኔው መሠረትም ቤርሎስኮኒ ሴሴኖ ከተማ ውስጥ በሚገኘውና ከ2000 በላይ በእድሜያቸው የገፉ፣ የአእምሮና የአካል ጉዳተኛ የሆኑ አረጋውያን በሚገኙበት ማዕከል ውስጥ ለአንድ ዓመት ያህል በሳምንት ለአራት ሠዓታት በማዕከሉ እየተገኙ አረጋውያኑን እንዲመግቡ፣ እንዲንከባከቡ፣ እንዲያንሸራሽሩ እንደ አጠቃላይም በማንኛውም መልኩ ከአረጋውያኑ ጎን እንዲሆኑ ተወስኖባቸው ሕዝባዊ የግዴታ አገልግሎቱን ፈፅመው አጠናቀዋል፡፡        

ታዋቂው አሜሪካዊ የሙዚቃ አቀንቃኝ ቦይ ጆርጅም በመኖሪያ ቤቱ የኮኬይን ዕፅ ይዞ መገኘትና በሀሰት የመኖሪያ ቤቴ ተዘርፏል በሚል ካቀረበው የሀሰት ጥቆማና ሪፖርት ጋር በተያያዘ እ.ኤ.አ. በ2006 በማንሀተን የወንጀል ችሎት ጥፋተኛ ከተባለ በኋላ የተወሰነበት ቅጣት ሕዝባዊ የግዴታ አገልግሎት እንዲሰጥ ይኸውም በኒውዮርክ ከተማ ለአምስት ቀናት ያህል የከተማዋን መንገዶች እንዲያፀዳ ሲሆን ከኒውዮርክ ከተማ የፅዳት አገልግሎት ክፍል ጋር በመሆን የከተማዋን አውራ ጎዳናዎች ለአምስት ቀናት ያህል በማፅዳት ቅጣቱን ፈፅሟል፡፡

ሆላንዳዊው የእግር ኳስ ተጫዋች የነበረውና ለአያክስ አምስተርዳም፣ ኤሲ ሚላንና ባርሴሎና እግር ኳስ ክለቦች ተጫውቶ ያሳለፈው ፓትሪክ ክላይቨርትም የ19 ዓመት ወጣት በነበረበትና ለአያክስ አምስተርዳም እግር ኳስ ክለብ በሚጫወትበት ወቅት በአምስተርዳም ከተማ ከፍጥነት ወሰን በላይ መኪና ሲያሽረክር ባደረሰው የመኪና አደጋ የቲያትር ዳይሬክተር የነበሩ የ56 ዓመት ጎልማሳ ሕይወታቸው እንዲያልፍ በማድረጉ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብሎ ዕድሜው ገና 19 ዓመት የነበረና ተስፈኛ ስፖርተኛ መሆኑ ከግምት ገብቶ የተጣለበት የሶስት ወራት የእስራት ቅጣት በሁለት ዓመት የፈተና ጊዜ እንዲገደብ፣ ለ18 ወራት መኪና ከማሽከርከር እንዲታቀብ እና ሕዝባዊ የግዴታ አገልግሎት እንዲሰጥ ተወስኖበታል፡፡ በሕዝባዊ የግዴታ አገልግሎቱም ፓትሪክ ክላይቨርት ለ240 ሰዓታት ታዳጊ ሕፃናትን በእግር ኳስ ስፖርት እንዲያሰለጥንና ለሕፃናቱ መልካም አስተዳደግ አስተዋፅኦ እንዲያደርግ ተወስኖበት ቅጣቱን መፈፀሙም ይታወቃል፡፡ ከእነዚህ ሠዎች በተጨማሪ ሌሎች ሠዎችም ለፈፀሙት የወንጀል ድርጊት ቅጣት እንሆን ሕዝባዊ የግዴታ አገልግሎት እንዲሰጡ ሲወሰንባቸው ይታያል፡፡     

ለመሆኑ የወንጀል አጥፊዎች ላይ የሚጣሉ ቅጣቶች ምን ዓይነት ናቸው? ሕዝባዊ የግዴታ አገልግሎት መስጠት ወይም የግዴታ ስራ ምን ዓይነት ቅጣት ነው? ዓላማውስ ምንድን ነው? በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግስ ሽፋን ተስጥቶታል ወይ? ሕዝባዊ የግዴታ አገልግሎት መስጠት ወይም የግዴታ ስራ የሚወሰነው ምን ምን ሁኔታዎች ሲሟሉ ነው? ስንት ዓይነት የግዴታ ስራዎች አሉ? ፍርድ ቤቶችስ የግዴታ ስራን አስመልክቶ በሕግ ተለይቶ የተሰጣቸው ሥልጣን ምንድን ነው? ሕዝባዊ የግዴታ አገልግሎት መስጠት ወይም የግዴታ ስራን አስመልክቶ የሚስተዋሉ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው ምንድን ናቸው? የሚሉና ተያያዥ ነጥቦችን በዚህ ፅሁፍ በአጭሩ እንዳስሳለን፡፡

Continue reading
  15113 Hits

ቅጥ አልባ ቅጣቶች በኢትዮጵያ ሕጎች    

             

መግቢያ

ከጥንት ጀምሮ እስከዛሬ ወንጀል የዚች ዓለም እውነት ነው፡፡ ቃኤል አቤል መግደሉ ከተሰማበት ይህን ጽሑፍ እርሶ እያነበቡ እስካሉት ቅፅበት ድረስ ወንጀል በሰው ልጆች ላይ በሰው ልጅ በራሱ ይፈፀማል፡፡ ይህ ከሰው ልጆች ታሪክ ጋር መሳ የሆነ ታሪክ ያለው ወንጀል ወደፊትም ማቆሚያ የሚኖረው አይመስልም፡፡ የሰው ልጅ ማድረግ የቻለው  ወንጀል የሚቀንስበትን አማራጭ መዘየድ እንጂ ወንጀል አልባ ዓለም መፍጠር አይደለም፡፡ ምናልባትም ወንጀል የመቀነስ ሙከራውም ተሳክቶ እንደሆነ እንጃ፡፡

ወጣም ወረደ ሁሉም ማህበረሰብ እንደ ማህበረሰቡ ታሪካዊና ማህበራዊ ዳራ ራሱን ከወንጀል ለመከላከል በዋናነት የዘየደው መላ ቅጣት ነው፡፡ የዚህ ጽሑፍ ማጠንጠኛም የወንጀል ቅጣት በኢትዮጵያ ሕግ ያለውን መልክ በመጠኑ ከጠቅላላ የቅጣት መርሆች አኳያ በመቃኘት በአሁኑ ሰዓት እርስ በእርሳቸው ተናባቢነት የሌላቸው በተመሳሳይ ጉዳይ የተለያየ ቅጣት የያዙ፣ ለቀላል ወንጀል ከባድ ቅጣት ለከባድ ወንጀል ቀላል ቅጣት የደነገጉ  በግብታዊነት እዚህም እዚያም ቅጣትን እንደ ተራ የመንገድ ጨቃ እያነሱ የሚለጥፉ ሕጎች ከወንጀል ጠቅላላ ዓላማና ግብ አኳያ በአጭሩ መፈተሸ ነው፡፡

የወንጀል ሕግ ዓላማ

Continue reading
  16788 Hits

ተከላካይ ጠበቃ ስለማግኘት መብት ጥቅል እይታ

 

መግቢያ

በአሁኑ ወቅት በስፋት ተቀባይነት ካገኙ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች በወንጀል ተከሰው ለጠበቃ የመክፈል አቅም ለሌላቸው ሰዎች የሕግ  ድጋፍ መስጠት አንዱ ነው። በመሆኑም ተከላካይ ጠበቃ የማግኘት መብት የተከሰሱ ሰዎች ካሏቸው ሕገ-መንግስታዊ  መብቶች ቀዳሚው ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ለምን ቢሉ በዓለማቀፋዊም ይሁን በአሕጉራዊ ስምምነቶች እንዲሁም በዝርዝር ብሄራዊ ሕጎች እውቅና የተሰጣቸውና ጥበቃ የሚደረግላቸው የተከሰሱ ሰዎች መብቶች የሚከበሩበት በመሆኑ ነው።

የተከሰሱ ሰዎች ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ሊከበሩላቸው የሚገቡ በርካታ መብቶች አሏቸው። ከእነዚህ ውስጥ በዳኝነት አካላት ፊት በእኩልነት የመታየት፣ ጥፋተኝነታቸው እስካልተረጋገጠ ድረስ ንፁህ ተደርገው የመገመት፣ ፍትሀዊ በሆነና በግልጽ ችሎት የመዳኘት፣ የተፋጠነ ፍርድ የማግኘትና ይግባኝ የማቅረብ መብቶች ይገኙበታል። በተጨማሪም ክሱን በጽሁፍ የማግኘት፣ ተከሳሾች በራሳቸው ላይ ያለመመስከር፣ የመከላከያ ምስክሮችንና ማስረጃዎቻቸውን የማቅረብ፣ ለአቃቤ ሕግ ምስክሮች መስቀለኛ ጥያቄ የማቅረብ፣ እንዲሁም በመንግሥት እጅ የሚገኙ ማስረጃዎችን የማግኘት መብቶቻቸውም ሳይጠቀሱ የማይታለፉ ናቸው።

ይሁን እንጂ እነዚህ ሁሉ በበርካታ ሕገ-መንግስታት፣ በዓለማቀፋዊና በአሕጉራዊ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች እውቅና ያገኙ መብቶች ብዙውን ጊዜ ሲከበሩ ሳይሆን ሲጣሱ ነው የሚታየው። ይህም የሚሆነው ለእነዚህ መብቶች መከበር መሰረታዊ የሆነው የተከሰሱ ሰዎች ተከላካይ ጠበቃ የማግኘት መብት ሕጉ ላይ በተቀመጠው ልክ በተግባር እየተፈጸመ ባለመሆኑ ነው።

Continue reading
  14471 Hits

የዘገየ ፍርድ

                እኔ አንቺን ስጠብቅ

ጠበኩሽ እኔማ…….

እዚያው ሰፈር ቆሜ

በአክሱም ቁመና በላሊበላ ዕድሜ

እግሮቼን ተክዬ ቀኔን አስረዝሜ

Continue reading
  11745 Hits

ስለ “የታሰሩ ሰዎች መብቶች” አንዳንድ ነጥቦች

 

በማያ ጋዜጣ ሐምሌ የታተመ በሰሞኑ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የችሎት ውሎዎች በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የጋራ የወንጀል ሕጉን የማስፈጸም ተግባር ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የተለያዩ መንግስታዊ መሥሪያ ቤቶች ዳይሬክተሮችን ጨምሮ በሙስና ወንጀል ተጠርጣሪነት ተይዘው የጊዜ ቀጠሮ እየተጠየቀባቸው የሚገኙት እስከ ሣምንቱ አጋማሽ ድረስ ቁራቸው 45 የደረሱ ተጠርጣሪዎች በእሥር ላይ የሚገኙ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ የሕግ እርምጃው ቀጣይነት ያለው መሆኑንም በመንግስት መገናኛ ብዙሃን በኢቢሲ መግለጫ ተነግሯል፡፡ የተጠርጣሪዎችን በእሥር ላይ መዋል ተከትሎ በመንግስትም ሆነ በግል መገናኛ ብዙሃን ተጠርጣሪዎቹ ፈጽመውታል ተብሎ ስለተጠረጠሩበት ወንጀል ዝርዝር የገንዘቡን መጠን ጨምሮ በስፋት ሲዘገብ እየተመለከትንና በጋዜጦች እያነበብን ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎቹን በሕግ መሠረት በቁጥጥር ሥር አውሎ፣ ክስ አቅርቦ ጥፋተኝነታቸው በማስረጃ የተረጋገጠባቸውን በህጉ መሠረት እንዲቀጡ ማድረግ መሰረታዊ የህግ ዓላማ እንዲሁም አንደኛው የሕግ አስፈጻሚዎች ሥልጣንና ተግባር ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በእሥር ላይ የሚገኙት ተጠርጣሪ እሥረኞችን ሕገመንግሥታዊ መብቶችን የማክበሩ ጉዳይም ከተጠያቂነቱና የወንጀል ህጉን ከማስፈጸሙ እኩል ጎን ለጎን ትኩረትን የሚሻ ነው፡፡ የሰዎች መብቶችና ግዴታዎች ሁል ጊዜ ጎን ለጎን በትይዩ የሚፈጸሙ መሆናቸው መሠረታዊ የህግ መርህ ነው፡፡ 


ከላይ የተጠቀሱትን ተጠርጣሪዎችን ጨምሮ ካሁን በፊት በሙስናም ሆነ በሌሎች ወንጀሎች ተጠርጥረው በእሥር ቤት/ በማረሚያ ቤት በሚገኙ ተከሳሾች የፍርድ ቤት ችሎት ውሎዎች የታሰሩ ሰዎችን መብቶች በተመለከተ የሚነሱ ዘርፈ ብዙ የመብት ጥያቄዎች፣ የመብት ጥሰት አቤቱታዎችና ክርክሮች ተደጋግመው ሲነሱ ይስተዋላል፡፡ የዛሬው የጽሁፋችን ርእስና ጭብጥ ሆኖ የተመረጠው ይህንኑ የእስረኞችን መብት ጉዳይ የሚመለከት ነው፡፡ በኢፌዲሪ ሕገመንግስት ከአንቀጽ 13 እስከ 44 ስለ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ከተደነገጉት መካከል በአንቀጽ 21 ሥር በጥበቃ ሥር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች መብት ከሰብአዊ መብቶች መካከል አንደኛው ሕገመንግስታዊ መብት መሆኑን ተደንግጓል፡፡ 
የሕገመንግስቱ አንቀጽ 21 ሁለት ንዑሳን ድንጋጌዎች እንደሚከተለው ይነበባሉ፡- 
(1) በጥበቃ ሥር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ሰብዓዊ ክብራቸውን በሚጠብቁ ሁኔታዎች የመያዝ መብት አላቸው፡፡

(2) ከትዳር ጓደኞቻቸው፣ ከቅርብ ዘመዶቻቸው፣ ከጓደኞቻቸው፣ ከሃይማኖት አማካሪዎቻቸው፣ ከሐኪሞቻቸው እና ከሕግ አማካሪዎቻቸው ጋር ለመገናኘትና እንዲጎበኟቸውም ዕድል የማግኘት መብት አላቸው፡፡

ለመሆኑ የታሰሩ ሰዎች ምን መብት አላቸው? መብቶቻቸውስ በየትኞቹ የሀገራችን ህግጋት ጥበቃ ተደርጎላቸዋል? የመብት ጥበቃውስ ከማን ነው? ጠባቂውስ ማን ነው? የት፣ መቼና እንዴትስ ይጠበቃል? ጽሁፉ እንዚህንና ተያያዥ ጭብጦችን ይዳስሳል፡፡

Continue reading
  12293 Hits

ያለ ፈጣን የፍርድ ሂደት ዋስትና የሚያስከለክል የወንጀል ድንጋጌ የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 20 የሚፃረር ተግባር ስለመሆኑ

 

ዋስትና በሕገ መንግሥትም ሆነ የሕገ መንግሥቱ የበታች በሆኑ በርካታ ሕጎች የታፈረና የተከበረ መሠረታዊው ከሆነው የሰው ልጅ የመዘዋወር ነፃነትና ንፁሕ ሆኖ የመገመት መብት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ሰብዓዊ መብት ነው፡፡

የሰው ልጅ እንደፈለገ ለመዘዋወር ሁለት እግሮች የተሰጡት፤ በአንድ ቦታ ተወስኖ እንዳይቀመጥ ሰዋዊ ተፈጥሮ ነፃ አድርጎ የፈጠረው ይህን ተፈጥሮውንም አብዝቶ የሚወድ ነፃ ፍጡር ነው፡፡ ይህ ፍጡር አሳማኝ የሆነ ማስረጃ በማቅረብ አንዳች ወንጀል መፈፀሙ ካልተረጋገጠበት በስተቀር ንፁህ ሆኖ የመቆጠር መብትም አለው፡፡ 

ይህ ከላይ ከፍ ሲል የተገለፀው ነፃ ሰው በሕግ ከመዘዋወር ሊከለከል፤ በአንድ በተለየ ስፍራ ታስሮ ሊቀመጥ የሚችለው ለጠቅላላው ሕዝብ ጥቅም ሲባል፣ የጠቅላላውን ሕዝብ ጥቅም ከአደጋ ለመጠበቅ ከፍተኛ የሆነ ወንጀል ተፈፅሞ ሲገኝ ምንአልባት የተጠርጣሪውን የዋስትና መብት ማክበር ይህን የጠቅላላውን ህዝብ ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ ይህንን የጠቅላላውን የሕዝብ ጥቅም ለመታደግ ሲባል ብቻ አስቀድሞ በተቀመጠ ሕግ ሊገደብ የሚችል መሠረታዊ መብት ነው፡፡

የዚህ ጽሑፍ መነሻ ከመነሻው የዋስትና መብትን መገደብ ሕገ መንግሥታዊ ነው ወይስ አይደለም የሚል ሳይሆን ክርክርን በአጭር ጊዜ ለመጨረስ የሚያስችል ሥርዓት (speedy trial) መኖሩን እርግጠኛ ባልተሆነበት ሁኔታ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ አንድ ወንጀል ፈፅሟል በሚል ክስ ስለቀረበበት ወይም ሊቀርብበት ስለሚችል ብቻ ዋስትና መከልከል ሕገ መንግሥታዊ ነው ወይ? የሚለው ነው፡፡

Continue reading
  10299 Hits
Tags:

(Non) retroactivity of Ethiopian Criminal Law


1. Introduction

A criminal law may be changed owing to various reasons. Obsoleteness, loopholes and insufficiency of penalties on the part of the existing criminal law are some of the justifications which may warrant its amendment or replacement. Even though changing a criminal law following changes in circumstances is vital and advisable, the advent of a new criminal law may create the difficulty of determining the temporal scope of application of the former and the new laws. An interesting solution for such problem is the principle of nonretroactivity of criminal law, which states that a criminal law is applicable only to offences committed subsequent to its enactment. Nevertheless, this principle has some exceptions, which allow the retrospective application of a criminal law.

The purpose of this article is, therefore, to explicate the meanings of and justifications for the (non) retroactivity of criminal law, to show how they are incorporated and how they must be comprehended under Ethiopian criminal law.

2.  (Non)retroactivity of Criminal Law

The word “retroactive” denotes “extending in scope or effect to matters that have occurred in the past”. It follows that retroactive legislation, also known as ex post facto laws, are “[l]aws which, expressly or by implication, operate so as to affect acts done prior to their having been passed.” In the context of criminal law, retroactivity is “to make an action a crime that was not a crime at the time it was done.” As such, retroactivity of criminal law “means that even a person well-informed about the law will be ignorant of the illegality of her or his acts because those acts are not deemed illegal until the retroactive law is made.” Conversely, the notion of nonretroactivity of criminal law suggests that criminal law should be applicable only to crimes done after the coming into force of the law.

Continue reading
  14971 Hits

በወንጀል ጉዳይ የመጨረሻ ውሳኔን እንደገና ስለማየትና በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ

 

መግቢያ

በወንጀል ጉዳይ  የፍርድ ውሳኔ የሰጠው ፍርድ ቤት በድጋሜ ጉዳዩን ማየት ማለት ፍርድ ቤቱ የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ የግዜ ገደብ ሳይኖረው ጉዳዩን በድጋሜ በተለያዩ ምክንያቶች ማየትና በድጋሜ ውሳኔ መስጠት ማለት ነው፡፡ በተለይም በዚህ ዘመን የሐሰት ሰነዶች የመቅረባቸው ጉዳይ እራስ ምታት በሆነበት፣ ሐሰተኛ ምስክርነትን መሠረት በማድረግ በተቃራኒ ተከራካሪ ወገንም ሆነ በፍርድ ቤቱ ሊደረስበት ባለመቻሉ የተሳሳተና የተዛባ የፍርድ ውሳኔ በሚሰጥበት ዘመን የእነዚህን ሐሰተኛ ማስረጃዎች ግዜ ሳይገድበው የሚያገኝ የወንጀል ጉዳይ ተከራካሪ ወደዛው ፍርድ ቤት በመሄድ የተገኘውን አዲስ ማስረጃ መሠረት በማድረግ ክርክር በድጋሜ አድርጎ ውሳኔው እንዲሰተካከል ለማድረግ የሚያስችል የሕግ አካሔድ መኖሩን አስፈላጊነት ሁሉም የሚስማማበት ነው፡፡ አንዳዴም እንደሚሰማው በህይወት ያለን ግለሰብ ገድለኃል ተብሎ ጥፋተኛ የተባለን ግለሰብ ሞተ የተባለው ግለሰብ በህይወት መኖሩ ቢታወቅ እንኳን ጥፋተኛ የተባለውን ግለሰብ ነፃ የሚያወጣ የሕግ አካሔድ ሊኖር የሚገባ ስለመሆኑም የሚያስማማ ነው፡፡ በቅርብ ግዜ በተላለፈ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ከሚያጋጥማቸው ጉዳዮች በመነሳት የሐሰት ሰነዶች እና የሐሰት ምስክርነት ጉዳይ ከግዜ ወደ ግዜ እየተበራከተ መምጣቱን ሲናገሩ መስማቴ ትዝ ይለኛል፡፡ ይህን መሰል የፍትሕ ጠር የሆነ ተግባር ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት ባይቻል እንኳን ይህ ሁኔታ በታወቀ ግዜ ግን ጉዳዩን ውሳኔውን የሰጠው ፍርድ ቤት በድጋሜ እንዲያይ የሚያስችልና ሐሰተኛውን ማስረጃ እና የተሳሳተውን ውሳኔ ለማስተካከል የሕግ መሠረት ሊኖረን ይገባል፡፡

የሕጎች አጭር ቅኝት

አሁን በሥራ ላይ ያለው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓት በወንጀል ጉዳይ የመጨረሻ ፍርድ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በይግባኝ በተቀመጠው 15 ቀን ውስጥ የውሳኔውን ግልባጭ መጠየቂያ እንዲሁም የውሳኔ ግልባጩ ከደረሰ 30 ቀን ውስጥ የይግባኝ አቤቱታውን ውሳኔውን ከሰጠው ፍርድ ቤት አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ ላለ ፍርድ ቤት በተሰጠው ወሳኔ ላይ ውሰኔውን በሰጠው ፍርድ ቤት መዝገብ ቤት በኩል ይግባኝ ከማለት በስተቀር (የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ ቁጥር 182187/1/ እና /2/ መመልከት ይቻላል) አዲስ የሆነና ሐሰተኛ ማስረጃ ስለመቅረቡ የሚያስረዳ ማስረጃ አግኝቻለሁ በማለት ፍርዱን ለሰጠው ፍርድ ቤት ውሳኔውን በድጋሜ ለማየት አቤቱታ ለማቅረብ የሚያስችል የሕግ ድንጋጌ የለም፡፡ በይግባኝ ቢታይም እንኳን አዲስ ማስረጃ ሊሰማ የሚችለው የይግባኝ ፍርድ ቤቱ የመሰማቱን ጉዳይ ካመነበት ብቻ ነው ይህም ሁኔታ በጠባቡ የሚታይ ነው(የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ ቁጥር 194/1/ መመልከት ይቻላል)፡፡ ከወንጀል ጉዳይ በተቃራኒው በፍትሐብሔር ጉዳይ የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ቁጥር 6(1)() እና () የመጨረሻ ፍርድ ወይም ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ የተሰጠው በሐሰት ተዘጋጅቶ የቀረበውን ሰነድ ወይም ሐሰተኛ ምስክርነት ቃልን ወይም መደለያን ወይም ወንጀል ጠቀስ የሆነ ተግባርን መሠረት በማድረግ ሲሆንና አቤት ባዩም ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት አስፈላጊውን ትጋት አድርጎ ለማወቅ ያለመቻሉን ለማስረዳት የቻለ እንደሆነ እና እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ተግባሮች መፈፀማቸው ቢገለፅ ኖሮ ለፍርዱ መለወጥ ወይም መሻሻል በቂ ምክንያት ሊሆኑ ይችሉ እንደነበረ ለማስረዳት የቻለ እንደሆነ በእነዚህ ምክንያቶች መነሻነት ፍርዱን ለፈረደው ወይም ትዕዛዝ ወይም ውሳኔውን ለሠጠው ፍርድ ቤት የተወሰነውን የዳኝነት ክፍያ በመክፈል አቤቱታውን ለማቅረብ እንደሚችል በግልፅ ያስቀምጣሉ፡፡

Continue reading
  10271 Hits