Font size: +
4 minutes reading time (782 words)

ደብዳቤው

ያው ጉባኤው የሚለውን ርእስ መኮረጄ ነው

እየመረጥክ ከዘገብክ የገለልተኝነት እና የእኩልነትን መርህ ጥሰሃል፡፡

/በበውቀቱ እስታይል/

ተከታዮ የመጀመሪያ አንቀፅ ለአገላለፅ ውበት እንጅ በጉዳዩ ላይ ያለኝ መቆጨት እንዳገላለፁ አለመሆኑ ይታወቅልኝ፡፡

የኢትዮጵያ ፕሮድካስቲንግ ባለስልጣል ለኢ ኤን ኤን የቴሌቪዚን ጣቢያ የፃፈውን ደብዳቤ እዚህ የፌስቡክ መንደር ውስጥ እያወቁ በድፍረት ሳያውቁ በስህተት እንደሆን እንጃ እጅጉን ሲተች ባይ ሆድ ባሰኝ፤ እንባየ መጣ ፤ቁጭት ልቤን መዘመዘው፤ አላስችል አለኝ በመጀመሪያ መብት የለውም አሉ ዝም አልኩኝ እነሱ ግን ይህን ሳያርሙ ሌላ ገደፉ እንዴት  ማለት ሲገባቸው ስህተት ነው ብለው ተናገሩ፡፡ በዚህ መች አብቅተው  እኩልነት ተጥሷል እል ብለው የሀሳብ ነጻነት ተደፍሯል ብለው አረፉ እንግዲህ ይህን ዝም ብሎ ማለፍ እንደምን ይቻላል፡፡ ምእመናን  አሳምራችሁ እንደምታወቁት የመገናኛ ብዙሃን መሰረት ገለልተኝነት እና በእኩልነት መርህ መገዛት አይደለምን? የመረጃ ነጻነት አደጋ ላይ የወደቀው እነዚህን መርሆች በጥብቅ ባለመከበራቸው መሆኑስ ይዘናጋል ምእመናን፡፡ እነዚህን መርሆች አለማክበርስ የመገናኛ ብዙሃንን ሃላፊነት በቅጡ ካለመረዳት የመጣ አይደለምን? መቼም ይህን ለማወቅ በዘርፉ ሙህር መሆን ይጠይቃል እያልኩ አይደለም ጎበዝ አስተዋይ ለሆነ ሰው ባለፈው ግዜ ሚዲያዋች የሰሩትን በማየት  ሚዲያዎቹ አድር ባይ የመንግስት አፈ ቀላጤ የነበሩ መሆናቸውን  መረዳት ይቸግረዋል ወይ ምእመናን? ስለዚህ እንደኔ እንደኔ ይን ጉዳይ በቀላሉ ልናልፈው አይገባም ባይ ነኝ፡፡

አዎ የሀሳብ ነጻነት ተከብሯል፡፡  አዎ ማንም ያሻውን ለማሰብ ነፃ ነው፡፡ ይህ በህገመንግስቱ አንቀፅ 29 እና ሌሎች አዋጆች የታፈረ መብት ነው፡፡ በተለይ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት  የተከበረው በዋናነት ለዴሞክራሲ ስረአት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች፤ ሃሳቦች እና አመለካክቶች በነፃ መንሸራሸራቸውን ለማረጋገጥ ፤ዲሞክራሲ እንዲሰፍን መተኪያ የሌለው ሚና እንዲጫወቱ፤ በከፍተኛ ሙያዊ ብቃት እና በነጻ እንዲሳተፉ በተለይም የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት እንዲከበር ለተከታያቸው የመራጃ ምንጭ እንዲሆኑ  ለማድረግም ጭምር ነው፡፡

አዎ ቅድመ ሳንሱር ተከልክሏል፡፡ የህዝብን መረጃ ጥቅም የሚመለከት መረጃን የማግኘት መብትም ተከብሯል ሚዲያዎች በተለይ በህግ በግልጥ በመክንያት ከተከለከሉ ውስን መረጃዎች በቀር ያሻቸውን መረጃ ጠይቅው የማግኘት መብታቸው ተከብሯል( አዋጅ ቁጥር 590/2000) ይህ ሁሉ የሆነው ይህን መብት  ተጠቅመው ሚዲያዎች የሃሳብ ነጻነት እንዲከብር እነዲሰሩ መራጃ ለህዝቡ እንዲያደርሱ ለማድረግ እንጅ ይህን እንድል ያለምክንያት ላለመጠቀም አይደለም  ለዝምታ ጣቢያ መክፈት ማይክራፎን መደገን አስፈላጊ አይደለም፡፡ ለመዘገብ ተመዝግበህ ያለምክንያት አለመዘገብ ነፃ  መሆንህን አያሳይም ይልቁንስ  በአዋጅ ቁጥር 533/99 አንቀፅ  16 እና 30 ላይ በግልፅ እንደተደነገገው አንድ ሚዲያ ለትርፍ የተቋቋመ ቢሆንም ፈቃድ በወሰደበት አካባቢ የሚገኘውን ማህበረሰብ በእኩልነት የማስተናገድ በፕሮግራሙ ውስጥ አካባቢያው እና አገራዊ ዜናዎችን የማካተት ስልሳ በመቶ ለሚሆን የሀገሪቱ ጉዳዮች ሽፋን የመስጠት  ግዴታ አለበት፡፡ይህን በሚያደርግበት ግዜም ከአድሎ ነጻ መሆን እና ሚዛናዊ መሆንም ግዴታው ነው፡፡

እንግዲህ የነጻ ሚዲያ መመዘኛው ይህ ከሆነ በእነዚህ መመዘኛዎች የጣቢያውን  ቅዳሜ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ/ም ዶክትር አብይ አህመድን ለመደገፍ የተደረገውን ሰልፍ በዜና መልክ ወይም በየትኛውም ሌላ መንገድ አለመዘገብ እንዴት ይታያል? ይህን ነጥብ ለመመርመር በመጀመሪያ የጣቢያውን ያለፉ ዘገባዎችን አይነት እና ብዛት ሰኔ 16 ቀን የተደረገውን ሰልፍ ዜና ወይም መረጃ የመሆን አቅም ለነጻ ሚዲያ መመዘኛ በሆኑት እኩልነት እና ሚዛናዊነት መርህ አንጻር መመዘን ያስፈልጋል፡፡

ጣቢያው ለምን ሰልፉን አልዘገበውም? በርግጥ ክስተቱ ዜና የመሆን አቅም የሌላው ተራ የመንደር መሰባሰብ ነበር?  በርግጥ በእለቱ ሲያስተላልፈው ከነበረው ከጀርመን አሸነፈች ያነሰ የዜና አቅምስ ነበረው? ተጣሉን ዘግበህ  ተደመሩን ካልዘከብክ በርግጥ ነጻ ገለልተኛ ሚዛናዊ መሆንህን ያሳያል፡፡ በሰልፉ ላይስ ንፁህ ዜጋህ ላይ የደረሰውን አደጋ ለህዝብ አለመግለጽ ኢትዮጵያን ኒውስ ኔትዎርክ በሚል ስም በዋናነት በዜና ላይ ከሚሰራ ሚዲያ አንጻር ስናየው የውጭ ሀገርን ፍንዳታዎች እና የድጋፍ እንቅስቃሴዎችን ሲዘግብ ኖሮ ፈቃድ በወሰደበት ክልል ውስጥ ጣቢያው ከሚገኝበት  10 እና 20 ኪሎሜትር እርቀት ላይ በሚሌዮኖች የሚቆጠረሩ ዜጎች የወጡበትን ንፁሃን የተጎዱበትን ሀገራዊ አጀንዳ መዝለል ነጻ መሆንን ሚዛናዊነትን እና በኩልነት መርህን መገዛትን ያሳያል?

ሚዛናዊነት ሳታከብር በኩልነት ሳትመራ ሚዲያ መሆን አይቻልም፡፡ እነዚህ አላባዎች ሳይኖሩ ነጻ ሚዲያ የለም ነፃ ሚዲያ እኩልነትን መጣስ ሚዛናዊነት መሳት አይደለም፡፡ ነፃ መሆን ህዝብን መረጃ መከልከል ማለትም አይደለም ፡፡  ሀሳብህን ለመግለፅ ነፃ ነህ፣ ሳንሱር የለብህም ፣መረጃ የማግኘት መብት አለህ ተብለህ ስትቋቋም ይህኑ እንድትሰራበት እንጅ አንዱን አወደሽ ሌላውን ነካሽ ሁን ማለት አይደለም፡፡ ነፃ ማለት እንደተፈለገ ማለትም አይደልም ነፃነትም ህግ አላት፡፡

ነፃ ገለልተኛ ሚዛናዊ እና በእኩልነት መርህ የምተገዛ መሆንህ የሚረጋገጠው ነጻነትህን ተጠቅመህ ስተዘግብ ብቻ ሳይሆን  በዝምታህም  ዝምታ ድርጊት ነው፡፡   ጥፋት በማድረግም(commission) ባለመዳረግም (omission) ይፈፀማል:: ስለዚህ በዚህ ሰልፍ ላይ የተለየ መመዘኛ በመጠቀም ለህዝቡ መረጃ የማድረስ ሀላፊነትህን ካልተወጣህ ሽፋን ከሰጠሃቸው እና ዜና ከሰራህላቸው ሌሎች አካባቢዎች እና ሁነቶች አንጻር በእኩልነት መርህ ትሞገታለህ፡፡

አዎ ነፃ ነህ ነፃነትህን በደነገገው ህገመንግስታዊ ድንጋጌ ላይ እኩል የተከበረውን የዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ በተለይም መረጃ የማግኘት መብታቸውን እንዲከበር ካልሰራህበት አንተ በርግጥም ነፃ አይደለህም  ነጻ መውጣት ያለብህ ከራስህም ጭምር ነው (no self-censure too)

ባለፉት አመታት ሚዲያዎቹ የመንግስት አፈ ቀላጤዎች ናቸው አድር ባይ እና ሚዛናዊነት የጎደላቸው ናቸው ሲባል የነበረው ለመንግስት ጥቅም እየሰሩ ለህዝብ ጥቅም ያልቆሙ የህዝብን እሮሮ ትተው የመነግስት ባለስልጣናት የውጭ ጎዞ የሚያዳንቁ አሽርጋጆች በመሆናቸው ነበረ፡፡ ነፃ ነህ ማለት የምትመራበት መርህ እና ህግ የለም ማለት አይደለም፡፡

በተለይም በለስልጣኑ  ሰልፉን ያልዘገብክበትን ምክንያት አስረዳ መባሉ ባለስልጣኑ በአዋጅ ቁጥር 533/99  አንቀፅ 7 እና 40 እና 44 መሰረት ባለስልጣኑ ፈቃድ ሲሰጥ የፕሮድካስቲግ አገልግሎት ለሀገሪቱ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት አስተዋቅኦ ሊያበረክት በሚችል መልኩ ፈቃድ የመስጠት የማገድ እና የመሰረዝ ሀላፊነቱን ለመወጣት በተለይም አዎጁ መከበሩን ለማረጋገጥ እና ቁጥጥር ለማድረግ በጣቢያዉ በመገኘት ጭምር ምርመራ የማድረግ ስልጣን አለው፡፡ አስቀድሞ  ሰልፉ ያልተዘገበበትን ምክንያት አስረዳ ማለት በርግጥም ይህ የሆነው በእኩልነት በሚዛናዊ አስተሳሰብ እና ሀገራዊ ግዴታ ከመወጣት አኳያ ያለውን ተገቢነት ለመመዘን ስለሚረዳ ማብራሪያ መጠየቁ እርምጃውን በግብታዊነት ከመውሰድ ይልቅ ፤ጣቢያው ራሱን የመከላከል እድል እየሰጠው መሆኑን ስለሚያሳይ ማንንም ለመጠየቅ መብት ያለው ሚዲያ ማብራሪያ መጠየቁ ምክንያታዊ እና ህጋዊ ነው እላሁ፡፡

×
Stay Informed

When you subscribe to the blog, we will send you an e-mail when there are new updates on the site so you wouldn't miss them.

አንዳንድ ጉዳዮች ስለ ግብርና እድገትና የመሬት ፓሊሲና ሕግ
የብሮድካስቲንግ ቁጥጥር/ሪጉሌሽን እና የባለሥልጣኑ ደብዳቤ

Related Posts

 

Comments

No comments made yet. Be the first to submit a comment
Already Registered? Login Here
Abebe
Saturday, 14 December 2024