የብሮድካስቲንግ ቁጥጥር/ሪጉሌሽን እና የባለሥልጣኑ ደብዳቤ

ስለሪጉላቶሪ መሳሪያዎች መግቢያ

ዛሬ የብሮድካስቲንግ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ለሁለት ብሮድካስተሮች ጽፈውታል የተባለ ደብዳቤ በፌስቡክ መለጠፉን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች እየተስተናገዱ ነው። በደብዳቤው ብሮድካስተሮቹ ለምን የቅዳሜውን የድጋፍ ሰልፍ እንዳላስተላለፉ መረጃ በተጠቀሰው ቀን ይዘው በመምጣት ከባለሥልጣኑ ጋር እንዲወያዩ ያሳስባል። ባለሥልጣኑ ይህን ደብዳቤ “ሊመልሰው፣ ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል”፣ እና የመሳሰሉት አስተያየቶች በመሰጠት ላይ ይገኛሉ። የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ምንም እንኳን በሚዲያ ተቋማት ዙሪያ የግሌ ጠቅላላ አስተያየትና እምነት ቢኖረኝም የብሮድካስቲንግ አዋጁን አስመልክቶ ያለኝን ግንዛቤና አረዳድ እንደሚከተለው አካፍላለሁ።

እንደሚታወቀው ብሮድካስቲንግ ባለሥልጣን ተቆጣጣሪ አካል ወይም ሪጉሌተር ነው። በመሆኑም ለመግቢያ ያህል በጠቅላላው በተለያዩ ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮች የተለያዩ ሪጉላቶሪ አካላት የመቆጣጠር ስልጣናቸውን ምን ዓይነት የፓሊሲ ወይም የሪጉላቶሪ መሳሪያዎችን በመጠቀም እንደሚያሳኩ ባጭሩ እንመልከት። የተለያዩ ሪጉላቶሪ አካላት የሚከተሉትን ስምንት ዋና ዋና መሳሪያዎች በአማራጭ ወይም በስብጥር ይጠቀማሉ።

አንደኛው የፈቃድ ሥርዓት መዘርጋት ነው። በአንድ የተለየ ተግባር ላይ መሰማራት የሚፈልግ አካል፣ ወደ ተግባር ከመግባቱ በፊት ከሚመለከተው ተቆጣጣሪ/ሪጉሌተር ፈቃድ እንዲያወጣ ይጠበቅበታል። የፈቃድ ሥርዓት ከማሳወቅ ሥርዓት ይለያል። ምክንያቱም ፈቃዱ ሊከለከል ይችላል። ፈቃዱን ለማግኘት አመልካቹ ማሟላት ያለበት ቅድመ ሁኔታዎች በሕግ ይቀመጣሉ። እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች የተለያዩ መልኮች ሊይዙ ይችላሉ፤  የዜግነት ወይም የነዋሪነት ግዴታ፣  የትምህርት ወይም የብቃት ደረጃ፣ የድርጅት ዓይነት (ለምሳሌ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ለመሰማራት፣ የግድ አክሲዮን ማህበር ማደራጀት ያስፈልጋል ሊባል ይችላል)፣ የገንዘብ አቅም፣ ፈተና፣ ልምድ፣ እና የሃላፊነት መድን (በሥራው የተነሳ በሌሎች አካላት ላይ ጉዳት ቢያደርስ፣ ጉዳቱን የሚክስ መድን አስቀድሞ እንዲገባ ማድረግ።

ሁለተኛው የሪጉላቶሪ መሳሪያ የጥራት ቁጥጥር ነው። አንዴ ፈቃድ አግኝቶ ወደ ተግባር የገባ አካል፣ የሚያቀርባቸው ምርትና አገልግሎቶች ሊያሟሏቸው የሚገባቸውን የጥራት ደረጃ ቁጥጥር ማድረግ። የጥራት ቁጥጥር ሁለት ዓይነት ዋና ዋና የጥራት ስታንዳርዶችን በመጠቀም ይከናወናል። አንደኛው የተግባሩ ውጤት ወይም ፍሬ ሊያሟላው የሚገባ የጥራት መለኪያ በወለል ወይም በጣሪያ መልክ ሊቀመጥ ይችላል። ለምሳሌ የታሸገ ውሃ ሊኖረው የሚገባው ከፍተኛ የአርሰኒክ መጠን በተቆጣጣሪው አካል በሕግ ሊደነገግ ይችላል። ሁለተኛው የጥራት ስታንዳርድ ዓይነት የግብአት ወይም ቴክኖሎጂ ወይም የሂደት ጥራት ነው። በዚህኛው መሠረት የተግባሩ ውጤት ወይም ፍሬ ሊያሟላው የሚገባ የጥራት ደረጃ ሳይሆን ትኩረት የሚደረገው፣ ውጤቱን ወይም ፍሬውን ለማምረት ወይም ለማቅረብ አምራቹ ወይም አቅራቢው ሊጠቀመው የሚገባ የግብአት፣ ቴክኖሎጂ፣ ወይም ሂደት ዓይነትና ጥራት በሪጉላቶሪ አካሉ ወይም በሕግ አውጪው በሕግ ሊደነገግና ክትትል ሊደረግበት ይችላል። ሁለቱንም ዓይነት ስታንዳርዶችን አሰባጥሮ መጠቀም ቢቻልም ብዙ ጊዜ ሁለተኛው ዓይነት ስታንዳርድ የምንጠቀመው፣ የመጀመሪያውን ዓይነት ስታንዳርድ ማውጣት ወይም ክትትል ማድረግ አስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜ ነው። ለምሳሌ የትምህርት ተቋማትን የአገልግሎት ጥራት ለመለካት የስራቸው ፍሬ የሆኑትን ተማሪዎቻቸው ሊያሟሏቸው የሚገቡ የጥራት መለኪያዎችን ማስቀመጥ ከባድ ስለሆነ የትምህርት ተቋማቱ ሊጠቀሙባቸው በሚገቡ ግብአቶች (ለምሳሌ የትምህርት መጽሐፍት፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ የተማሪና የአስተማሪ የቁጥር ምጣኔ)፣ ሂደቶችና ቴኬኖሎጂዎች ላይ ትኩረት ይደረጋል። እንዲሁም በከተሞች የሚቀርቡ የቧንቧ የመጠጥ ውሃን አስመልክቶ የመጀመሪያውን ዓይነት ስታንዳርድ ማውጣትቢቻልም፣ ክትትሉ ግን እጅግ አስቸጋሪ ስለሚሆንን እና አስተማማኝነቱም ዝቅተኛ ስለሚሆን በዋናነት በሁለተኛው ዓይነት የጥራት ስታንዳርድ ስራ ላይ ሲውሉ ይስተዋላል። ሊታወቅ የሚገባው ጉዳይ ሁለተኛው ዓይነት የሪጉላቶሪ መሳሪያ ለኪራይ ሰብሳቢነት የተጋለጠ ከመሆኑ በተጨማሪ፣ አማራጭ ቴክኖሎጂዎች፣ ግብአቶች፣ ወይም ሂደቶች እንዳይዳብሩ ወይም እንዲከስሙ ማድረጉ ነው።

Continue reading
  7846 Hits

ደብዳቤው

ያው ጉባኤው የሚለውን ርእስ መኮረጄ ነው

እየመረጥክ ከዘገብክ የገለልተኝነት እና የእኩልነትን መርህ ጥሰሃል፡፡

/በበውቀቱ እስታይል/

ተከታዮ የመጀመሪያ አንቀፅ ለአገላለፅ ውበት እንጅ በጉዳዩ ላይ ያለኝ መቆጨት እንዳገላለፁ አለመሆኑ ይታወቅልኝ፡፡

የኢትዮጵያ ፕሮድካስቲንግ ባለስልጣል ለኢ ኤን ኤን የቴሌቪዚን ጣቢያ የፃፈውን ደብዳቤ እዚህ የፌስቡክ መንደር ውስጥ እያወቁ በድፍረት ሳያውቁ በስህተት እንደሆን እንጃ እጅጉን ሲተች ባይ ሆድ ባሰኝ፤ እንባየ መጣ ፤ቁጭት ልቤን መዘመዘው፤ አላስችል አለኝ በመጀመሪያ መብት የለውም አሉ ዝም አልኩኝ እነሱ ግን ይህን ሳያርሙ ሌላ ገደፉ እንዴት  ማለት ሲገባቸው ስህተት ነው ብለው ተናገሩ፡፡ በዚህ መች አብቅተው  እኩልነት ተጥሷል እል ብለው የሀሳብ ነጻነት ተደፍሯል ብለው አረፉ እንግዲህ ይህን ዝም ብሎ ማለፍ እንደምን ይቻላል፡፡ ምእመናን  አሳምራችሁ እንደምታወቁት የመገናኛ ብዙሃን መሰረት ገለልተኝነት እና በእኩልነት መርህ መገዛት አይደለምን? የመረጃ ነጻነት አደጋ ላይ የወደቀው እነዚህን መርሆች በጥብቅ ባለመከበራቸው መሆኑስ ይዘናጋል ምእመናን፡፡ እነዚህን መርሆች አለማክበርስ የመገናኛ ብዙሃንን ሃላፊነት በቅጡ ካለመረዳት የመጣ አይደለምን? መቼም ይህን ለማወቅ በዘርፉ ሙህር መሆን ይጠይቃል እያልኩ አይደለም ጎበዝ አስተዋይ ለሆነ ሰው ባለፈው ግዜ ሚዲያዋች የሰሩትን በማየት  ሚዲያዎቹ አድር ባይ የመንግስት አፈ ቀላጤ የነበሩ መሆናቸውን  መረዳት ይቸግረዋል ወይ ምእመናን? ስለዚህ እንደኔ እንደኔ ይን ጉዳይ በቀላሉ ልናልፈው አይገባም ባይ ነኝ፡፡

Continue reading
  7199 Hits