Ilmi Maqaan Abbaa Isaa akka jijjiirramuuf kallattiidhaan gaafachuu ni danda’aa?

Ilmi Maqaan Abbaa Isaa akka jijjiirramuuf kallattiidhaan gaafachuu ni danda’aa? Xiinxala Raawwatiinsa SHH Kwt 42 fi 43 irratti taasifame.

Bu’uura Heera Mootummaa Federaalaa Kwt 36(1)(b) tiin daa’imni kamuu maqaa fi lammummaa qabaachuuf mirga qaba jechuun kaa’eera. Gama kanaan seerri maqaa namni tokko qabaachuu kan danda’u haala kamiin akka ta’e kaa’u immoo S/H/H kwt 32-46 akkasumas kwt 3358- 3360 tti jiran jalatti kaa’ameera. Bu’uuruma kanaan namni tokkoo maqaa firaa(family name),maqaa dhuunfaa tokko ykn isaa ol (first name) fi maqaa abbaa(patronymic ) qabaachuu akka qabu qajeeltoon isaa S/H/H kwt 32 jalatti kaa’ameera.

Continue reading
  2539 Hits

አባትነትን በDNA በትክክል ማወቅ ይቻላል?

 

 

አባትነትን DNA በትክክል ማወቅ ይቻላል?

ስለ ኪሜራ ምን ያውቃሉ?

 ሰላም እንዴት ናችሁ በማለት እስኪ ሙያችን በተመለከተ አንድ ቁምነገር ላንሳ፡፡

Continue reading
  16331 Hits
Tags:

የቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 107/2/ ከሌሎች የቤተሰብ ሕጉ ድንጋጌዎች እና ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 36 ጋር ያለው ተቃርኖ

መግቢያ

እናትነት እውነት አባትነት ግን እምነት ነው የሚለው አባባል ተደጋግሞ የሚሰማው አባትነትን ማረጋገጥ ፈታኝ የሆኑ ማህበራዊ ባይሎጂካዊና ሕጋዊ ውስብስብነት ያለው ፈታኝ ጉዳይ በመሆኑ ነው፡፡ አባት ለልጁ ግዴታዎችን  አሉበት፤ አባት ከልጁ የሚጠይቀው መብት አለው፡፡ ልጅ ለአባቱ የሚጠይቀው ግዴታዎች ያሉበትን ያህል ከአባቱም የሚጠይቀው መብት አለው፡፡ እኚህ በመሀላቸው መብትም ግዴታም ያስተሳሰራቸው ሁለት ሰዎች ታዲያ በርግጥም አባትና ልጅ ናቸው? የሚለው ጥያቄ ፈታኝ ነው፡፡ ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ከባድ ስለመሆኑ አባትነትንና ልጅነትን ስለማወቅ በሕጉ የተቀመጡ ድንጋጌዎች ለጥያቄው ምላሽ በሚሰጡበት አካሔድ መረዳት ይቻላል፡፡ ይህ ጽሑፍም የሚያጠነጥነው ከጋብቻና እንደባልና ሚስት አብሮ ከመኖር ግንኙነት ውጭ በአንድ አጋጣሚ ግብረ ሥጋ ግንኙነት ምክንያት የተወለደን ልጅ በተመለከተ ሆኖ በእንደዚህ ዓይነት ግንኙነት የተወለደ ልጅ በርግጥ በሕግ አይን አባት አለው? ካለውስ ሕጉ በዚህ ረገድ ግልጽና ወጥ ነው? የቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 107/2/ በርግጥስ ፋይዳው ምንድን ነው? የሚሉ ጉዳዮችን ለውይይት መነሻ እንዲሆን ያህል ለመዳሰስ ይሞክራል፡፡

አባትነትን እና ልጅነትን ስለማረጋገጥ

በቤተሰብ ሕጉ አቀራረጽ መሠረት ልጆች በሦስት ይከፈላሉ፤ እነዚሁም በጋብቻ ውስጥ የተወለዱ፤ እንደ ባልና ሚስት አብረው ከሚኖሩ ሰዎች የተወለዱ ልጆች እና ከሌላ ዓይነት ማለትም ከመጀመሪያዎቹ ከሁለቱ ውጭ በሆነ  ሌላ ግንኙነት የተወለዱ ልጆች ናቸው፡፡

የመጀመሪያዎቹ ሁለት ግንኙነቶች በሕግ ፊት ዕውቅና የተሰጣቸውና በሕጉም ተገቢውን ጥበቃ የሚደረግላቸው ሲሆን የመጨረሻው ይነት ሌላ ግንኙነት ግን በሕግ ፊት ውጤት  የማያስተካከል በዚህም ምክንያት በሕግ ጥበቃ የማይደረግለት ተራ ግንኙነት ነው፡፡

Continue reading
  15852 Hits
Tags:

DNA አባትነትን ማረጋገጫ ማስረጃ ስላለመሆኑ

 

ሁሉም ሰው ባዮሎጂካዊ አባት አለው ሁሉም ሰው ግን ህጋዊ አባት ላይኖረው ይችላል፡፡ ይህ አረፍተ ነገር በብዙዎቻችሁ ጭንቅላት እንዴ! የሚል ግርምት እንደሚያጭር እገምታለሁ፡፡ በተለይ ሁሉም ልጅ እኩል ነው ልጆች አባትና እናታቸውን የማወቅ ሕገ መንግሥታዊ መብት አላችሁ የሚለው አነጋገር አብዝቶ ከመሰማቱ የተነሳ በሕግ አባት የሌለው ልጅ ሊኖር ይችላል ብሎ መገመት ሩቅ ሊሆን ይችላል በቀጣዩ ጽሑፍ በመግቢዬ የገለፅኩት ሀሳብ ምን ያህል እውነት እንደሆነ ለማሳየት እታትራለሁ፡፡

በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 36(1)(ሐ) ላይ ለህፃናት ከተደነገጉላቸው መሠረታዊ መብቶች አንዱ ህፃናት እናት አባታቸውን የማወቅ የእነሱንም ክትትልና እንክብካቤ ማግኘት ነው፡፡ ታዲያ ይህ ጥያቄ ተግባራዊ ምላሽ ሊያገኝ የሚችለው በየክልሎቹ የቤተሰብ ሕግና በፌደራሉ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ መሠረት ነው፡፡ ይሁን እንጂ በነዚህ የቤተሰብ ሕጎች ላይ ሁሉም ልጆች እናታቸውን እንጂ አባታቸውን ለማወቅ አልታደሉም የዚህ ጽሑፍ ማጠንጠኛም እነዚህ በሕግ አባታቸውን ለማወቅ ማወቅ አይደለም በሕግ አባት የሌላቸው ልጆች በእንዴት አይነት ሁኔታ የተወለዱ ልጆች ናቸው እጣፋንታቸውስ ምንድን ነው የሚለውን ሀሳብ መፈተሸ ነው፡፡ በተለይም ከእውነትነቱ ይልቅ በእምነትነቱ ይበልጥ የሚገለፀው የአባትንት ጥያቄ በቤተሰብ ሕጉ እንዴት ይመለሳል በተለይም ይህን ጥያቄ ከመመለስ ብኋላ የሚከተሉትን ሌሎች ይሕግ ጥያቄዎችን (ውርስ፣ቀለብ…) ባግባቡ ለበመልስ ይዚህ ጥያቄ ምላሽ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

በሕግ የአንድ ልጅ አባት ማነው?

እንግዲህ የአንድን ልጅ አባትና እናት ለማወቅ በመጀመሪያ መመልከት ያለብን በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ስለ እናትነትና አባትነት ስለማወቅ የተደነገገበትን የሕግ ክፍል በመመልከት ነው በዚህ የሕግ ክፍል መሠረት የአንድን ልጅ አባት በሶስት የተለያዩ መንገዶች ማወቅ ይቻላል፡፡

Continue reading
  25191 Hits
Tags: