ማስታዎሻ፡- ውደ አንባቢያን ይህ ጽሑፍ የተወሰደው በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያዎች በሚል ከታተመው በ2017 ዓ.ም ተሻሻሎ በቀረበው መጽሐፌ ላይ ሲሆን የግርጌ ማስታዎሻዎቹ እና ማጣቀሻዎቹ ለዚህ ጽሑፍ ሲባል ለንባብ በሚመች አግባብ እንደገና ተቀናጅተው ተሰርተዋል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የተካተቱት አብዛኛዎቹ ነጥቦች አወዛጋቢ ሆኖም በሕግ ባለሙያው ብዥታ እና ልዩነት የሚፈጥሩ ነጥቦች በመጽሐፉ የመጀመሪያ ዕትም ያልነበሩ አሁን ላይ በችሎት በሚገጥሙ ክርክሮች ሰበር ጭምር መፍትሔ የሰጣቸውን እና ሰበር መፍትሔ ያልሰጠባቸውን ደግሞ የመጽሐፉ አዘጋጅም የራሱን ምልከታ እና መፍትሔ የሚላቸውን ሃሳቦች ያሰቀመጠባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡
ይህ ፅሑፍ “የኢትዮጵያ የውርስ ሕግ መሰረተ-ሐሳቦች” ከሚለው 3ኛ ዕትም መፅሐፍ በ10ኛ ምዕራፍ ላይ የተከተበ ሲሆን በዚህ መፅሐፍ በመጀመሪያ እና በ2ኛ ዕትም ያልነበር ነው፡፡ በዚህ መፅሐፍ በ3ኛ ዕትም በምዕራፍ 10 ላይ ከተነሱ በርካታ ጉዳዮች መካከል ጥቂቶቹን ብቻ እነሆ ጀባ ብያለሁኝ፡፡
ማሳሰቢያ ይህ ፅሑፍ በመፅሐፉ በሕግ የሚጻፉ ጉዳዮችን የማጣቀሻ ሥነ-ሥርዓት (based on legal citation rule) ተከትሎ የተጻፈ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ፅሑፍ በበየነ-መርብ በሚለቀቅ በድህረ-ገፅ ላይ የሚነበብ በመሆኑ ይህንን ታሳቢ በማድረግ ለአንባቢዎች ይህንን ፅሑፍ ሲያነቡ በሚመች አግባብ የማጣቀሻ ሁኔታዎች ከመፅሐፉ ከነበረው በሕግ የሚጻፉ ጉዳዮችን የማጣቀሻ ሥነ-ሥርዓት (based on legal citation rule) በተለየ መልኩ የተቀመጡ ለመሆኑ ለማሳሰብ እወዳለሁኝ፡፡
በመዲናችን የመሬት ሕግ ላይ ትኩረት ያደረገውና ”የከተማ መሬት ሕግ በአዲስ አበባ” የሚል አርዕስት ያለው መጽሐፍ ስለ መሬት ሕግ ጠቅላላ ጽንሰ ሃሳባዊ ጉዳዮችን ጨምሮ ስለ እስከዛሬው የአገራችን የመሬት ስሪት ሁኔታ፣ ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ስላላቸው የመዲናችን ዋና ዋና ጉዳዮች ለምሳሌ የመዲናችንን የቆዳ ስፋት፣ የወሰን አከላለል እና ሕጋዊ አቋም የሚያብራሩ እንዲሁም ከመዲናችን ምስረታ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን የመሬት ስሪት ሁኔታ የሚያስረዱ ነጥቦችን አሁን ለንባብ በበቃው የመጀመሪያው ክፍል ይዟል፡፡
ስለሆነም ይህንኑ የምርምር መጽሐፌን እንድታነቡልኝ ስል በአክብሮት እጋብዛለሁ፡፡