እንደ መግቢያ
ይህ ፅሑፍ “የኢትዮጵያ የውርስ ሕግ መሰረተ-ሐሳቦች” ከሚለው 3ኛ ዕትም መፅሐፍ በ9ኛ ምዕራፍ ላይ የተከተበ ሲሆን በዚህ መፅሐፍ በመጀመሪያ እና በ2ኛ ዕትም ምዕራፍ 9 ተብሎ የነበረውን በአዲስ መልክ የውርስ ጉዳይ ይርጋዎችን በማዋቀር በመፅሐፉ ተሰንዷል፡፡ በምዕራፍ 9 ላይ ከተቃኙ ከ20 በላይ የሆኑ የውርስ ይርጋ ጉዳዮች መካከል ለቅምሻ ያክል በጣም ጥቂቶቹን ማለትም ሶስት ጉዳዮች ብቻ እነሆ ጀባ ብያለሁኝ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ይህ ፅሑፍ መፅሐፉ በሕግ የሚጻፉ ጉዳዮችን የማጣቀሻ ሥነ-ሥርዓት (based on legal citation rule) ተከትሎ የተጻፈ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ፅሑፍ በበየነ-መርብ በሚለቀቅ በድህረ-ገፅ ላይ የሚነበብ በመሆኑ ይህንን ታሳቢ በማድረግ ለአንባቢዎች ይህንን ፅሑፍ ሲያነቡ በሚመች አግባብ የማጣቀሻ ሁኔታዎች ከመፅሐፉ ከነበረው በሕግ የሚጻፉ ጉዳዮችን የማጣቀሻ ሥነ-ሥርዓት (based on legal citation rule) በተለየ መልኩ የተቀመጡ ለመሆኑ ለማሳሰብ እወዳለሁኝ፡፡