የኮንስትራክሽን ዋስትና ምንነትና በተግባር የሚስተዋሉ የሕግ ክፍተቶች - ክፍል 1

መግቢያ

ይህ ጹሑፍ በ6ኛው የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ “የኮንስትራክሽን ዋስትና ሕጎች እና የገንዘብ ተቋማት አሰራር” በሚል አውደ ጥናት ላይ ለውይይት የቀረበ ነው፡፡

ዋስትና በውል አፈጻጸም ወቅት እንደተጨማሪ ግዴታ የሚቆጠር በሕግ ፊት ሊጸና የሚችል (juridical act) ተግባር ነው፡፡ በአለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ በአለማችን ከኢኮኖሚያዊ እድገት ጋር ታያይዞ ዋስትና (security) የመጠቀም ልማድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጧል፡፡

ሆኖም ግን እኤአ ከ2007 ዓ.ም በኋላ ከዓለም ኢኮኖሚ መዳከም ጋር ተያይዞ የዋስትና ጥቅም በአግባቡ የታየበት ብሎም አሰፈላጊነቱም ጭምር ጥያቄ ምልክት ውስጥ የገባበት ጊዜም አይዘነጋም፡፡

ዋስትና መልኩ ይለያይ እንጂ በተግባር አገልግሎት ላይ መዋል የጀመረው እእኤ ከ2750ዓ.ዓ ገደማ ጀምሮ ነበር፡፡ በወቅቱም ዋስትናው ጥሬ ገንዘብ እንደመያዣነት በማቅረብ ነበር፡፡ በተለይ ስለ ሰው ዋስትና (surety) ሕግጋት እና መርሆዎች በተመለከተ ጥናታዊ ሮማዊያን እኤአ በ150ዓ.ም ገደማ ያዘጋጁት ተጠቃሽ ነው፡፡ (ጄፈሪ በርተን፡2000፡9) ከዚያም የሦስተኛ ወገን ዋስትና ወደ ማቅረብ የተሄደበትም ጊዜ ነበር፡፡ ዘመናዊ የፋይናንስ ተቋማት ማደግን ተክትሎ በዋናነት ለዓለምአቀፍ የሽያጭ ግብይቶች ክሬዲ (letters of credit) እየተስፋፋ የመጣበትን ሁኔታ እናገኛልን፡፡

Continue reading
  16469 Hits