የሰበር ትችት - Blog

በውርስ ሕግ አተረጓጎም ዙሪያ በተሰጡ አንዳንድ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ የሕግ ትርጎሞች ላይ የቀረበ ትችት

ይህ ጽሑፍ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከውርስ ሕጉ አጠቃላይ አወቃቀር እና አደረጃጀት ወጥተው በአንደኛው የውርስ ሕግ ክፍል የተደነገገን ድንጋጌ አግባብነት ለሌለው ሌላ የውርስ ሕግ ክፍል ተግባራዊ በማድረግ አንዳንዴም በጉዳዩ ላይ ተፈጻሚነት ያላቸዉን የውርስ ሕግ ድንጋጌዎች በመተዉ አጠቃላይ የዉል ሕግ ድንጋጌዎችን መሠረት በማድረግ ገዥ ትርጉም መስጠታቸውን እና ይህም ሕጉን የተከተለ አለመሆኑን ይከራከራል፡፡ እንዲሁም በዚህ ምክንየት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በራሱ ተቃራኒ እና ምክንየታዊ ያልሆኑ ውሳኔዎች እየተሰጡ መሆኑን በማሳየት የውርስ ሕጉ ሊተረጎም እና ተግባራዊ ሊሆን የሚችልበትን መንገድ ይጠቁማል፡፡

  7016 Hits