ጸሐፊዉ ከባህርዳር ዩንቨርሲቲ የመጀመሪያ ድግሪ ከኢትዮጵያ ሲቭል ሰርቪስ ዩንቨርሲቲ ሁለተኛ ድግሪ ያላቸው ሲሆን በወረዳ ፍርድ ቤት በዳኝነት፣ በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ እና አስተባባሪ በመሆን አገልግለዋል። ጸሐፊው የተጠቃለሉ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት የሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ የሕግ ትርጉሞችን በማጠናቀር ለተገልጋዮች ምቹ በሆነ መልኩ በመጽሐፍ አሳትመው ያሰራጩ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዳኝነት ሥራ ላይ ይገኛሉ።

በውርስ ሕግ አተረጓጎም ዙሪያ በተሰጡ አንዳንድ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ የሕግ ትርጎሞች ላይ የቀረበ ትችት
Melake Tilahun Ayenew
Succession Law Blog
ይህ ጽሑፍ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከውርስ ሕጉ አጠቃላይ አወቃቀር እና አደረጃጀት ወጥተው በአንደኛው የውርስ ሕግ ክፍል የተደነገገን ድንጋጌ አግባብነት ለሌለው ሌላ የውርስ ሕግ ክፍል ተግባራዊ በማድረግ አንዳንዴም በጉዳዩ ላይ ተፈጻሚነት ያላቸዉን የውርስ ሕግ ድንጋጌዎች በመተዉ አጠቃላይ የዉል ሕግ ድንጋጌዎችን መሠረት በማድረግ ገዥ ትርጉም መስጠታቸውን እና ይህም ሕጉን የተከተለ አለመሆኑን ይከራከራል፡፡ እንዲሁም በዚህ ምክንየት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በራሱ ተቃራኒ እና ምክንየታዊ ያልሆኑ ውሳኔዎች እየተሰጡ መሆኑን በማሳየት የውርስ ሕጉ ሊተረጎም እና ተግባራዊ ሊሆን የሚችልበትን መንገድ ይጠቁማል፡፡
Continue reading