Font size: +
3 minutes reading time (555 words)

የሳይበር ክልልና የሀገሮች የለአላዊነት ስልጣን እስከ ምን ድረስ

የሳይበር ክልል ሲባል የኮምፒውተር ፕሮግራሞች፣ ዳታዎች፣ የኮምፒውተርና የቴሌኮምንኬሽን ግንኙነት፣ የኮምፒውተር ስርአትና በአጠቃላይ እነዚህ መሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ እንዲሁም ተጠቃሚዎችን የሚያካትት ክልል ነው በማለት በአጭሩ መግለጽ ይቻላል፡፡ ታዲያ ይህ ክልል የሀገሮች የፖለቲካ ይሁን የመልክአ-ምድር አቀማመጥ የማይገድበው እንዲሁም በሀገሮችና በህዝቦች መካከል ያለው የባህል፣ የቋንቋና የአኗኗር ዘዴ ጫና የማያሳድርበት ከመሆኑ አንጻር ክልሉን የሚመለከቱ ገና ምላሽ ያላገኙ በሀገሮች መካከል ለውዝግብና ያለመግባባት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ ነጥቦች መከሰታቸው አልቀረም፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ይህን ዘርፍ እንዴትና በማን ይተዳደር፣ ዘርፉንስ ከህገወጦች እንዴት እንከላከል እንዲሁም በሀገሮችና ዜጎቻቸው ላይ ደህንነትና ጥቅሞች በህገ ወጦች ይሁን በአንድ አንድ የሀገር መንግስታት አመካኝነት አደጋ ሲቃጣ የሀገሮች ምላሽ ምን ሊሆን ይገባል ህገወጦችንስ ለፍርድ የማቅረብ ስልጣን የማን ሊሆን ይገባል በአጠቃላይ የሀገሮች ሉአላዊነት እንዴት ማስከበር ይቻላል እና የመሳሰሉትን ጉዳዮች ላይ ገና ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡

ከዚህም ብዙም ሳንርቅ ለሳይበር ክልል መፈጠርና ማደግ በዋናነት ቁልፍ ሚና በመጫወት ላይ ካሉት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ውስጥ የኮምፒውተሮች ግንኙነት ወይም ደግሞ በይነ-መረብ በዋናነት ከሚጠቀሱ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አንደኛው ነው፡ ይህ ዘርፍ ከሚሰጣቸው በርካታ አገልግሎቶችና ከተጠቃሚዎች ብዛት አንጻር በተጠቃሚዎች መካከል ልዩ ልዩ አለመግባባቶች ማጋጠማቸው አይቀርም፡፡ ለምሳሌ ከውል አፈጻጸም፣ የካሳ ጥያቄና አከፋፈል የዳኝነት ስልጣንና የመሳሰሉት አለመግባባትና ግጭቶች ያጋጥማሉ፡፡ ታዲያ እንደእነዚህ አይነት ግጭቶችና ያለመግባባት እንዴት ይፈቱ፡ በተለይም ደግሞ ሀገሮች ዘርፉን በመቆጣጠርና ማስተዳደር እንዲሁም የራሳቸውን ሉአላዊነት ከማስከበር ጋር ተያይዞ ያለባቸውን ክፍተት በመሙላት ረገድ ገና ምላሽ የሚያስፈልጋቸው ልዩ ልዩ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡


እንደሚታወቀው ማንኛውም ለአላዊ መንግስት በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የሚሰጣቸው የሉአላዊነቱ መገለጫ የሆኑ ስልጣኖች አሉት፡፡ ይሄውም፣ አንድ ነጻ የሆነ የሀገር መንግስት እነዚህን የሉአላዊነቱን መገለጫ የሆኑትን ተግባራት በግዛቱ ውስጥ በሚገኙ ሰዎች፣ የሚንቀሳቀሱ ይሁን የማይንቀሳቀሱ ነገሮች እንዲሁም ክንውኖች ላይ ህግ የማውጣት፣ የወጣውን ህግ ተግባር ላይ እንዲውል የማድረግና ያወጣቸውን ህጎች ተጥሰው ሲገኙ ያለማንም ጣልቃ ገብነት ህግን የማስከበርና እንደነገሩ ሁኔታ አጥፊዎችንም ለፍርድ በማቅረብ የማስቀጣት ሙሉ የለአላዊነት ስልጣን አለው፡፡ በመሆኑም ሀገሮች አለም አቀፍ የሳይበር ክልል መፈጠርን ተከትሎ ይህንን የለአላዊነታቸው መገለጫቸው የሆኑትን ስልጣኖች በዚሁ ክልል ላይም ለመተግበር እንዲችሉ ልዩ ልዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡


ይሁን እንጂ የአንድ ሀገር ለአላዊነት ስልጣን እስከምን ድረስ ሊሆን ይገባል በሚለው ላይ አንድ መደምደሚያ ላይ ለመድረስ አልተቻለም፡፡ ስለሆነም፣ በዚህ ጉዳይ ላይ የተለያዩ ሙህራን የተለያዩ አስተያየቶች ይሰጣሉ፡ ለምሳሌ ይህ ዘርፍ በየትኛው ህግ ሊመራ ይገባል በሚለው ጉዳይ ላይ አንድ አንዶች እንተርኔት ሳይበር ክልል በለአላዊ ግዛቶች መካከል የቴክኖሎጂ፣ የህግና ስርአት ትስስር እንዲፈጠር የሚያደርግ ዘርፍ እንደመሆኑ መጠን ዘርፉ በየትኛው ህግ ሊተዳደር ይገበዋል ያልን እንደሆነ በነጻ ለኣላዊ ሀገሮች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚመለከተው የህግ ክፍል አለም አቀፍ ህግ ነው፡፡ ስለሆነም፣ እንተርኔትም በዚሁ የህግ ማእቀፍ ሊተዳደር ይገባል የሚሉ ሙሁራን የመኖራቸው ያክል ሌሎች ደግሞ ልክ ነው በሀገሮች መካከል ላለው ግንኙነት በተመለከተ ግንኙነታቸው የሚመራው በአለም አቀፍ ህግና ስምምነቶች ነው ነገር ግን እንተርኔት የሀገሮች ግንኙነት ጉዳይ ብቻ አይደለም ዘርፉ ከሀገሮች ጋር ያለውን ግንኙነት ቁርኝት እንዲፈጠር በማድረግ አለም አቀፋዊነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ይህ ጉዳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይም ጭምር ነው በቀጥታ በሀገር ደህንነት፣ ሰላም፣ ልማት፣ ዲሞክራሲ እድገትና ውድቀት ላይ ትልቅ ሚና ያለው ዘርፍ ነው፡፡


ስለሆነም ይህ ለአለም አቀፍ ግንኙነት ብቻ የሚተው ጉዳይ አይገባም፡፡ በሌላ በኩል ይህ ጉዳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ነው ስለሆነም የሀገሪቱ ህግ ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ ይሁን ሊባልም የሚችል ጉዳይ አይደለም ምክኒያቱም የሳይበር ክልል በአንድ ሀገር ድንበር የታጠረ አይደለምና ነው፡፡ ለምሳሌ ከተጠቃሚዎች አንጻር ብንመለከተው የየትኛው ሀገር ተጠቃሚ የትኛውም ሀገር ካለው ተጠቃሚ ጋር ግንኙነት በመፍጠር መረጃ ይለዋወጣሉ ሀሳባቸውን ይገልጻሉ የንግድ እንቅስቃሴ ያካሂዳሉ ሌላው ቀርቶ ግንኙነታቸውን በማጠናከር ማህበራዊና ቤተሰባዊ ትስስር እስከመፍጠር ይደርሳሉ፡፡ ስለዚህም በአንድ ሀገር ህግና ደንብ መመራት አለበት የሚለውም በተወሰነ ደረጃ ልክ ሊሆን ቢችልም፣ ነገር ግን ዘርፉ የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ ጉዳዮችን አጣምሮ የሚይዝ እንደመሆኑ መጠን፣ በሀገር ውስት ህግ ብቻ መተዳደር ይኖርበታል የሚለውም አግባብነቱ አጠያያቂ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ 


ስለሆነም፣ በዚህና በሌሎች በርካታ ምክኒያቶች ዘርፉ በአለም አቀፍ ህግ ማእቀፍ ሊወድቅ ወይስ በሀገር ውስጥ ህጎች ሊካተት ይገባል የሚለውን ጉዳይ ይከራከሩበታል፡፡


እርሶን ብንጠይቆትስ?

×
Stay Informed

When you subscribe to the blog, we will send you an e-mail when there are new updates on the site so you wouldn't miss them.

የሳይበር ክልልና የሀገሮች የለአላዊነት ስልጣን እስከ ምን ድረስ ለሚለው ጥያቄ ...
"ድፍረት" ፊልም - የቅጅ መብት ጥበቃ ለታሪካዊ እውነታ ወይስ ለአእምሮ ፈጠራ?

Related Posts

 

Comments

No comments made yet. Be the first to submit a comment
Already Registered? Login Here
Abebe
Sunday, 08 September 2024