የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን በዋስትና በማስያዝ ብድር የመስጠት የባንኮች ኃላፊነት

 

 

መግቢያ

በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ባንኮችና አበዳሪ የገንዘብ ተቋማት ብድር ለማበደር እንደመያዣነት ከሚመርጧቸው ንብረቶች መካከል በዋናነት የማይንቀሳቀስ ንብረት (ማለትም ህንጻዎችንና ቤትን) እንዲሁም ከተንቀሳቃሽ ንብረቶች ውስጥ ደግሞ መኪናን እንዲሁም ትላልቅ ማሽነሪዎችን ብቻ ላይ የተመሰረተ ነበር፡፡ በዚህም በተለይም አበዳሪ ባንኮች በዋናነት በቀላሉ ብድራቸውን ማስመለስ የሚችሉት በቀላሉ ሊጠፉ የማይችሉ ንብረቶችን በመያዣነት በመያዝ ነበር፡፡ ይህ ሁኔታም በተለይም ተበዳሪዎች የብድር ገንዘብ አግኝተው የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ለመሳተፍ እና ለኢኮኖሚው እድገትም አስተዋጽኦ ከማድረግ አንጻር ሁኔታው አዳጋች እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡ በዚያው ልክም የብድር አቅርቦት ውስኑነትም ባንኮች ብድርን በሰፊው ላለማቅረባቸው ሌላው ምክንያት ነው፡፡

አሁን በተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ በነጋሪት ጋዜጣ የታተመው የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን በዋስትና በማስያዝ ብድር ለመበደር የሚያስችል አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 1147/2011 (pdf)) (አዋጅ ቁጥር 1147/2011 በነጋሪ መተግበሪያ) በቅርቡ በስራ ላይ እንዲውል ታትሟል፡፡ በተለይም አዋጁ የያዛቸውና የሚያተኩርባቸው ነጥቦች ለአበዳሪ ባንኮችም ጭምር አዲስ በመሆናቸው አዋጁን የሚጠቀሙት አስፈጻሚዎችም ሆኑ የባንክ ባለሙያዎች እንዲሁም ከዚህ አዋጅ ተጠቃሚ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ስለአዋጁ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ ውስብስብነት የሚታይበትን ይህንኑ አዋጅ መሰረታዊ ነጥቦቹን ለማስገንዘብ ከፍኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ከዚህ በዘለለም አዋጅ የያዛቸው ሀሳቦች አዳዲስና ውስብስብ በመሆናቸው አዋጁ ላይ ግንዛቤ ካልተፈጠረ አዋጁ ከመውጣቱ ውጪ ተግባራዊነቱ እጅግ ከባድ እንደሚሆን የአዋጁን ይዘት በመመልት በቀላሉ መናገር ይቻላል፡፡ በመሆኑም በዚህ ጽሑፍ ስለአዋጁ እና በባንኮች እንደት ሊፈጸም እንደሚችል እንዲሁም የሚንቀሳቀሱ ንብረቶች ሲባል ምን ምንን ያካትታል፤ በዚህ አዋጅ ተጠቃሚ ለመሆን ምን ምን ጉዳዮችን ማማላት ያስፈልጋል፤ የአዋጁ ዋነኛ ትኩረት ምንድን ነው የሚሉና ሌሎች መሰረታዊ ነጥቦችን ጠቅለል ባለ መልኩ ዳሰሳ ተደርጎባቸዋል፡፡

Continue reading
  7720 Hits

የአክሲዮን መያዣ አመሠራረትና የመያዣ ተቀባዩ መብቶች

 

 

መያዣ ለአንድ ግዴታ አፈፃፀም ማረጋገጫ የሚሰጥ የንብረት ዋስትና ነው፡፡ ዋና ግዴታ በሌለበት መያዣ ስለማይኖር መያዣ በንብረት ላይ የሚፈፀም ደባል ግዴታ (accessory obligation) ነው፡፡ መያዣ በሚንቀሳቀስ ወይም በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚመሠረት ሲሆን በዚህ ጽሑፍ ምልከታ የሚደረግበት የአክሲዮን መያዣ የሚንቀሳቀስ ንብረት መያዣ /pledge/ በመሆኑ ከማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ጋር በተገናኘ በንጽጽር ካልሆነ በቀር የሚነሱ ነጥቦች አይኖሩም፡፡ የፍትሐብሔር ሕጋችን ፕሌጅ ከውል የሚመሠረት ግዴታ እንደሆነ ይደነግጋል፡፡ የሕጉ አንቀጽ 2825 የመያዣ ውል ማለት አንድ ባለዕዳ በባለገንዘቡ በኩል የገባውን ግዴታ ለመፈፀም መቻሉን በማረጋገጥ መያዣ ተብሎ የሚጠራውን ዕቃ ለመስጠት የሚገደድበት ውል ማለት ነው ሲል ግልጽ ትርጉም ይሰጣዋል፡፡ በመያዣ ሊሰጥ የሚችለውን ነገር በመወሰን ረገድ የፍትሐብሔር ሕጉ የሚታይም ሆነ የማይታይ ተንቀሳቃሽ ንብረትን ሊያካትት እንደሚችል ይደነግጋል፡፡ ሕጉ በቁጥር 2829 በመያዣነት የሚሰጠው አንድ ተንቀሳቃሽ ንብረት (a chattel) ወይም በጠቅላላው ዕቃ ተብለው ከሚጠሩ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች አንዱ (a totality of effects) ወይም አንድ የገንዘብ መጠየቂያ መብት ሰነድ (a claim) ወይም በአንድ ተንቀሳቃሽ ንብረት ላይ ያለ የመብት መጠየቂያ ሰነድ ለመሆን እንደሚችል ይደነግጋል፡፡ አክሲዮን የአንድ የንግድ ማኅበር (የአክሲዮን ማኅበር ወይም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር) የአባልነት ማስረጃና በካፒታሉ ውስጥ ያለ ድርሻ (ጥቅም) ማረጋገጫ ነው፡፡ አክሲዮን የገንዘብ መጠየቂያ ሰነዶች (claims) ውስጥ የሚወድቅ ግዙፍነት የሌለው ተንቀሳቃሽ ንብረት (incorporeal Movable) ነው፡፡ የፍትሐብሔር ሕጉን አንቀጽ 1125 ይመለከቷል፡፡ አክሲዮን በመያዣ የሚሰጥበት የሕግ ማዕቀፍ በፍትሐብሔር ሕጉ ቁጥር 2863-2874 እንዲሁም በንግድ ሕጉ ቁጥር 329 ላይ የተካተተ ሲሆን በዚህ ጽሑፍ የአክሲዮን መያዣ የሚቋቋምበትን ሁኔታ እና አክሲዮን በመያዣ የተቀበለ ባለገንዘብ ያሉትን መብቶች የተመለከቱ ነጥቦችን ለማየት ሙከራ ይደረጋል፡፡

 

የሚንቀሳቀስ ንብረት መያዣ (ፕሌጅ) አመሠራረት

Continue reading
  17158 Hits