ሕዝባዊ ፍርድ፣ ፍርድ ቤቶች እና ገላጋይ ዳኞች

 

የፍርድ ቤቶችን ችግር ለመፍታት፣ ጫናቸዉን ለመቀነስ፣ የሚያቀርቡትን የዳኝነት አገልግሎት ጥራት ለመጨመር ከሚቀርቡት የመፍትሄ ሃሳቦች መካከል አማራጭ የሙግት መፍቻ ስልቶችን (ለምሳሌ ግልግል ዳኝነት) ማበረታት ነዉ።

አማራጭ ስልቶችን ማበረታታት ተገቢ ነዉ፣ ጠቃሚ እስከሆነ ድረስ።  ነገር ግን ፍርድ ቤቶች በችግሮች በተተበተቡበት ሁኔታ፣ ምንም እንኳን ሕጉ ለአማራጭ ስልቶች እውቅና እና ድጋፍ ቢሰጥም፣ የፍድ ቤቶችን ችግር በመፍታት ወይም አለመግባባትን በመቀነስና በመፍታት ረገድ ግን የሚፈይደው ነገር ጥቂት ነው፡፡

የፍርድ ቤቶች መጠናከር ነዉ ቅድሚያ ሊስጠዉ የሚገባዉ። ፍርድ ቤቶች ሲጠናከሩ (ለምሳሌ በፍጥነት ዉሳኔ ሲሰጡ፣ ዉሳኔዎቻቸዉ ግልጽ፣ ተደራሽ፣ ተገማች ሲሆኑ፤ ሙስና ሲቀንስ) ብቻ ነዉ፤ ግለሰቦችና ድርጅቶች ሌሎች አማራጭ የግጭት መፍቻ ስልቶችን ሊጠቀሙ የሚችሉት። ፍርድ ቤት ቢሄዱ፤ መቼ፣ እና ምን አይነት ዉሳኔ፣ በምን ዋጋ ማግኘት እንደሚችሉ መገመት ሲችሉ ብቻ ነዉ አማራጭ መንገዶችን ለመጠቀም ሊወስኑ የሚችሉት።

ወደ ፍርድ ቤት ነዉ የሚሄዱት። ፍርድ ቤቶችራሳቸዉ በችግሮች በተተበተቡበት ሁኔታ፣ ምንም እንኳን አንደኛዉ ወገን ዉጭ በገላጋይ ዳኞች መዳኘት ቢፈልገም፣ ሌላኛው በተለይ ደግሞ የፍርድ ቤቶችን ችግር የሚፈልገው ላይስማማ ይችላል፡፡ በዚህም የበለጠ ፍርድ ቤት እንዲጨናነቅ ያደርገል፡፡

Continue reading
  9459 Hits