ፍላጎት ላጣው መራጭ ምን ይደረግ?

 

ለፌዴራል እና ለክልል ሕግ አውጪ ምክር ቤቶች የሕዝብ እንደራሴዎችን ለመምረጥ የሚከናወነው መጪው አገር አቀፍ ምርጫ ከተደጋጋሚ መስተጓጎሎች በኋላ የድምጽ መስጫ ዕለቱ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲደረግ ቀን ተቆርጦለት ዝግጅቶቹ ቀጥለዋል፡፡ ይህ ምርጫ ከዓመት በፊት ማለትም በሕገ-መንግሥታዊ ትርጉም ከመራዘሙ በፊት ካለው ጊዜ ጋር ሲነጻጸር፤ በትግራዩ ጦርነት፣ በሰላምና ደህንነት ስጋቶቹ፣ የተዳከመው የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ፣ የተጽዕኖ ፈጣሪ ፖለቲከኞች እስር፣ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እና የውጪ አገራት ጫና ያደበዘዘው ይመስላል፡፡ እንዲህም ሆኖ ግን፤ ድህረ-2010 የታዩት የሕግ እና የተቋማት ማሻሻያዎች፣ አንጻራዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመገናኛ ብዙኃን እና የሲቪክ ምሕዳሮች ስፋት የዘንድሮውን ምርጫ በጉጉት ተጠባቂ እንዲሆን ማድረጋቸው አልቀረም፡፡

ምርጫ 2013 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳውን ይፋ ካደረገበት ወርኃ ጥር ጀምሮ እስካሁን ድረስ በርከት ያሉ የቅድመ-ምርጫ ተግባራት ተከናውነውበታል። ከእነዚህ መካከል የምርጫ ቁሳቁሶች ዝግጅት፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላ፣ የእጩዎች ምዝገባ፣ የመራጮች ትምህርት እና የመራጮች ምዝገባ ተጠቃሽ ክንውኖች ናቸው።

በእነዚህ ወሳኝ የቅድመ-ምርጫ ክንውኖች ውስጥ የተነሱት እና በቀሩት ጊዜያትም ሊነሱ የሚችሉት በተለይም የሕግ ጉዳዮች የዘንድሮውን ምርጫ የተለየ መሆንነት አጉልተው የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ለአብነት እንኳ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ያስከተለው ውዝግብ፣ ከፌዴራሉና ከሌሎቹ ክልሎች ምክር ቤት አባላት ምርጫ ቀን ተለይቶ የነበረው የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ምክር ቤቶች ምርጫ ጉዳይ፣ የአፋር እና የሶማሌ ክልሎች የምርጫ ጣቢያዎች ውዝግብ፣ የሐረሪ ክልል ብሔራዊ ጉባኤ አባላት ምርጫ እና አነጋጋሪው የእጩዎች ምዝገባ የፍርድ ቤቶች ክርክር የዘንድሮው ምርጫ በቀጣይ ለሚከናወኑ ምርጫዎች አስቀምጦ የሚያልፈው ልምምድ ቀላል የሚባል አለመሆኑን የሚያስገነዝቡ ናቸው፡፡

ወሳኝ የምርጫ ባለድርሻ አካላት ከሆኑት ልዩ ልዩ ተቋማት መካከል ምርጫ ቦርድ፣ ፍርድ ቤቶች እና የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች በእስካሁኖቹ የምርጫ ሂደቶች ያሳዩት  ጥረት የምንመኘውን ነጻ፣ ትክክለኛ እና ተዓማኒ ምርጫ ወደፊት ለማድረግ እጅግ ጠቃሚ ናቸው። በዚያው ልክ ግን በሒደቶቹ ውስጥ የታዩ የጎሎ ክፍተቶች የዘንድሮውን ጨምሮ በቀጣይ ለሚደረጉትም ምርጫዎች የራሳቸው አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደራቸው አይቀርም።

Continue reading
  3204 Hits
Tags:

የክልሎች (የትግራይ ክልል) ምርጫ ሕገ-መንግሥታዊነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ብሎም የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት

 

መግቢያ

ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ 6ተኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ የፌደራል መንግሥቱ ማራዘሙን ተከትሎ የትግራይ ክልላዊ ብሔራዊ መንግሥት ምርጫውን በክልሉ ለማካሔድ በመወሰን የምርጫ ቦርድ በማቋቋም ምርጫውን ለማድረግ አስፈላጊ ናቸው ያላቸውን ዝግጅት በማድረጉ ሲሆን የትግራይ ክልል መንግሥት ምርጫውን ማድረግ ይችላል አይችልም? ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቁጥጥር ውጭ የሆነና ራሱን የቻለ ምርጫ ቦርድ ማቋቋም ይችላል አይችልም? ምርጫውስ ከተካሄድ ሊኖረው የሚችለው ውጤት ምን ድን ነው? የሚሉትንና ተያያዥነት ያላቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲሁም የትግራይ ክልል ምርጫውን ማድረግ መቻሉ ጋር የምርጫውን በክልል ደረጃ መደረጉን የሚደግፉ ፖለቲከኞችና አስተያየት ሰጭዎች ራስን በራስ ከማስተዳደርና የራስን እድል በራስ ከመወሰን ሕገ መንግሥታዊ መብት ጋር ስለሚያያይዙት ከነዚህ መብቶች ጋር ምርጫ ማድረግ እንዴት ሊታይ ይገባል? የሚለውን ከፌደራሉ ሕገ መንግሥት እና ከምርጫ አዋጆች (አ/ቁ. 1133/2011 እና አ/ቁ. 1162/2011) አኳያ ለማብራራትና ሃሳብ ለማቅረብ በሚል የተዘጋጅ አጭር ጽሑፍ (Article) ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ ላይ ማንኛውም አስተያየት ሰጭ ለሚሰጠው አስተያየት ጸሐፊው ለማስተናገድና ሃሳብ ለመለዋወጥ ዝግጁ መሆኔን ከወዲሁ ማሳወቅ እፈልጋለሁ፡፡ መልካም ንባብ፡፡

 

1. የትግራይ ክልል ምርጫ ምንነትና ዓይነት

Continue reading
  5035 Hits