የኮንስትራክሽን መብቶች (Claims) ምንነት እና የሚስተዋሉ ችግሮች

 

እንደ መነሻ

ማንኛውም ሰው በማህበራዊ ኑሮ ውስጥ በሚገጥመው መስተጋብር የተለያዩ ጥያቄዎች ወይም መብቶች (Claims) ሊኖረው ይችላል፡፡ ከዚህ ንድፈ ሃሳብ በመነሳት ታዲያ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውም በርካታ የመብት ጥያቄዎች መነሳታቸው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው! እንደሚታወቀው የግንባታ ዘርፍ ብዙ ባለድርሻ አካላትን ማሳተፋ ብቻ ሳይሆን የሚገርመው በተለያየ ሙያ ያሉ ሰዎች መሳተፋቸውም ጭምር ነው፡፡ ይህም በመሆኑም በርካታ የመብት ጥያቄዎች መነሳታቸው የግድ ነው፡፡ ከዚህ ብሂል በመነሳት አንዳንዶች ከውል በመነጨ ጉዳይ የውል የመብት ጥያቄ ሲያነሱ ሌሎች ደግሞ ሕጉ አስቀድሞ ባስቀመጠው ቅድመ ሁኔታ መሠረት ውል ሳይኖር አላፊነት በመኖሩ ምክንያት መብታቸውን ከውል ውጭ ሲጠይቁ ይስታዋላል፡፡

ምናልባት በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ለሚነሱ አለመግባባቶች እና ቁርሾዎች እንደ ምክንያትነት የሚነሣው የመብቶች ጥያቄ ጉዳይ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ቅድሚያውንም የሚወስዱት በተለይም ከሥራ ርክክብ መዘግይት እንዲሁም ከውል መለወጥ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጉዳዮች ናቸው፡፡ በሃገራችንም ምንም እንኳን ልማዱ በዓለም አቀፍ ሥራ ተቋራጮች በርከት ቢልም ቅሉ፤ የሃገር ውስጥ ሥራ ተቋራጮችም ቢሆን አሁን አሁን የተለያዩ የኮንስትራክሽን የመብት ጥያቄዎች ሲያስተጋቡ ይስተዋላል፡፡

Continue reading
  19591 Hits