የንግድ እቃን ማከማቸት፣ መደበቅ፣ ዋጋ ጨምሮ መሸጥ እና የኮረና ወረርሽኝ ከኢትዮጵያ ሕግ አንፃር

 

መግቢያ

በአገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወረርሽኝ ሲከሰት የሰዎች ህይወትን ከመቅሰፉ በተጨማሪ የንግድ እንቅስቃሴዎችንም አደጋ ላይ ይጥላል። ንግድ የተሳለጠ እና ለሁሉ ተደራሽ የሚሆነው የተረጋጋ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር ሲኖር ብቻ ነው። በንግድ ዓለም ውስጥ የነጋዴዎች ዋነኛ ግብ ተደርጎ የሚወሰደው በአጭር ጊዜ ወይም በረጅም ጊዜ ውስጥ ትርፋማ መሆን ነው። ነገር ግን ይህ ትርፋመነታቸውን የሚያሳኩት ሕግ እና ሥርዓትን በአከበረ መንገድ በሚደረግ እንቅስቃሴ ሊሆን ይገባል። ከሕግ እና ሥርዓት ውጭ ትርፍ ለማጋበስ የሚንቀሳቀስ ነጋዴ የተመሰረተበት አላማ ማትረፍ ስለሆነ በሚል ተልካሻ ምክንያት ዝም ተብሎ ሊታለፍ አይገባም። ይህንም መሰረት ለማስያዝ ሕግ እና ሥርዓት አስፈፃሚ አካላት ትልቅ ድርሻ አላቸው። ትርፍ ለማግኘት ከሚደረጉ ጥረቶች ጎን ለጎን ማህበራዊ ሀላፊነትን መወጣትንም መዘንጋት አይገባም። የነጋዴዎች ትርፍን ለማሳደግ የሚያርጉት እሩጫ ሕግ እና ሥርዓትን ለማስከበር ከተቋቋመ አካል ጋር በጥብቅ ከሚካረሩባቸው ወቅቶች አንዱ ወረርሺኝ የሚከሰትበት ወቅት ነው። ወረርሽኝ በሚከሰትበት ወቅት ሁሉም ከወረርሽኙ ለመዳን በሚያደርገው እሩጫ ወቅቱ የሚፈልጋቸው እቃዎች እና አገልግሎቶች እጥረት ሊከሰት ይችላል። በዚህ ጊዜ ማህበራዊ ሀላፊነትታቸውን ለመወጣት ደፋ ቀና የሚሉ ነጋዴዎች የሚኖሩትን ያክል አጋጣሚውን ተጠቅመው ሀብት ለማካበት እና ከችግር ለማትረፍ የሚሯሯጡም አሉ። እነዚህ ከችግር ለማትረፍ የሚሯሯጡ ነጋዴዎች ከሚተገብሯቸው ነገሮች መካከል እጥረት ያለበትን እቃ ማከማቸት እና በተፈላጊ እቃዎች ላይ አለአግባብ ዋጋ መጨመር ይገኙበታል። እነዚህ ተግባራት በሸማቹ ማህበረሰብ ላይ ከቀላል እስከ ከባድ አደጋዎችን ሊያስከትሉ ይችላሉ። ይህንንም ታሳቢ በማድረግ ሀገራት የሸመቾች ጥበቃ ሕግን በማውጣት ሸማቹን ማህበረሰብ ከእንደዚህ አይነት ችግር ለመጠበቅ ጥረት ሲያደርጉ  ይስተዋላል። ሀገራችን ኢትዮጵያም ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ ለሸማቾች መብት ጥበቃ ልዩ ትኩረትን የሰጠች ሲሆን በመካከልም ሁለት ህጎችን አርቅቃለች። አሁን ላይ በስራ ላይ ያለው የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 ትኩረት ከሰጣቸው ነገሮች መካከል እጥረት ያለባቸውን እቃዎች ማከማቸት እና ተፈላጊ እቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች ይገኙበታል። በሀገራችን ዓለም አቀፍ የሆነው የኮረና ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ ከወረርሽኙ እኩል በሚባል ደረጃ የመገናኛ ብዙሀንን ትኩረት የሳበው ጉዳይ የነጋዴዎች እጥረት ያለባቸውን እቃዎች ማከማቸት ተግባር እና የተፈላጊ እቃዎችን ዋጋ  ጨምሮ መሸጥ ይገኙበታል። የዚች አጭር ፅሁፍ አላማም እነዚህን የነጋዴው ማህበረሰብ ተግባራት ከኢትዮጵያ የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ አንፃር መተንተን እና መወሰድ ያለባቸውን ተግባራት መጠቆም ነው።

  1. የኮረና ወረርሽኝ እና እጥረት የተከሰተባቸው እቃዎች

የኮረና ወረርሽኝን ለመከላከል ከሚደረጉ ጥረቶች መካከል የህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል። የዓለም ጤና ድርጅት በሰጠው መመሪያ መሰረት ሀገራት ሊከተሏቸው ከሚገቡ የመከላከያ መንገዶች አካላዊ እርቀት፣ ማስክ መጠቀም ፣አለመጨባበጥ እና እጅን በተደጋጋሚ መታጠብ ዋነኞቹ ናቸው። ከእነዚህም ውስጥ ማስክ መጠቀም የማስክ አቅርቦትን እንዲሁም እጅን በተደጋጋሚ መታጠብ ደግሞ የሳሙና እና የሳኒታይዘር አቅርቦትን ይጠይቃሉ። በአሁኑ ሰዓት በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ እነዚህ በሽታውን ለመከላከል የሚረዱ እቃዎች እጥረት የመንግስታት እና የህዝብ ጭንቀት ከሆኑ ውሎ አድሯል። ከዚህ በተጨማሪ እነዚህን እጥረት ያለባቸውን ቁሳቁስ በአገኙት አጋጣሚ የሚሰበስቡ እና በውድ ለመሸጥ የሚያከማቹ ነጋዴዎች እንዲሁም ከእራሳቸው እና ከቤተሰባቸው ፍጆታ በላይ የሚገዙ ግለሰቦች መበራከት ሌላ ትልቅ የእራስ ምታት ሆኗል። ከህክምና ቁሳቁሶች በተጨመሪ ለእለት ፍጆታ የሚውሉ እቃዎችም ለዚሁ ችግር ሰለባ ሆነዋል። መንግስት የሚያወጣውን መመሪያ ተከትሎ ዜጎች እቤት ውስጥ ለመቀመጥ ከሚገዙት ከመጠን ያለፈ የምግብ እቃዎች በተጨማሪ ወደፊት የዋጋ ጭማሪ ሊከሰት እንደሚችል በመተንበይ ዜጎች ሊገዙ የሚፈልጉአቸውን እቃዎች አከማችቶ የለም iማለት ወይም አላግባብ ዋጋ በመጨመር የሸማቹን የመግዛት አቅም የመቀነስ ተግባር በነጋዴው ማህበረሰብ ዘንድ ይስተዋላል። እነዚህ ተግባራት በወቅቱ ተገቢ የሆነ ህጋዊ እርምጃ ካልተወሰደባቸው በጊዜ ሂደት የሚያስከትሉት አደጋ በጣም ከባድ ይሆናል። የህክምና ቁሳቁሶች ላይም ሆነ የእለት ፍጆታ እቃዎች ላይ የሚደረገው የማከማት እና ሰው ሰራሽ የእቃ እጥረት ችግር ሸማቹን ማህብረሰብ ለርሀብ ብሎም ለሞት የሚዳርግ ችግር ውስጥ ሊከተው ይችላል። ወረርሽኙን ለመከላከል የሚረዱ እቃዎች በአግባቡ እንዲሰራጩ ከአልተደረገ ከእለት ወደ እለት ወረርሽኙ እየተስፋፋ ከሚያስከትለው ሰብዓዊ ኪሳራ በተጨማሪ የእለት ከእለት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን በመገደብ ሀገርን ከባድ የማትወጣው አዘቅት ውስጥ ሊከት ይችላል። የእለት ፍጆታ አቅርቦቶችን መገደብም በእራሱ ዜጎችን ለርሀበ እና ሲቃይ በመዳረግ ወረርሽኙ ሊያስከትል ከሚችለው አደጋ የበለጠ ችግር ሊያመጣ ይችላል። እነዚህን ከባድ ችግሮች መቋቋም የሚቻለው ሕግን መሰረት አድርጎ በእንደዚህ አይነት ተግባራት ላይ የተሰማሩ አካላትን ማስተካከል እና አስፈላጊ እርምጃዎች ሲወሰዱ ብቻ ነው።

  1. የንግድ እቃን ማከማቸት እና ሰው ሰራሽ እጥረት መፍጠር በኢትዮጵያ ሕግ

እቃን ማከማቸት እና ሰው ሰራሽ እጥረት መፍጠር የገቢያ አለመረጋጋት እና የዋጋ ንረትን ከሚያስከትሉ ተግባራት መካከል የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል። በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች የእቃውን በገቢያ ላይ ያለውን ተፈላጊነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የአቅርቦት ችግር በሌለበት ሁኔታ የአቅርቦት ችግር ያለ በማስመሰል በግለሰብ ወይም በቡድን ደረጃ ሊያከማቹ እና ሰው ሰራሽ እጥረት ፈጥረው በትልቅ ዋጋ የመሸጥ ተግባር ሊፈፅሙ ይችላሉ። ነጋዴዎች እቃውን አከማችተው የሚያስቀጡበት ዋነኛ አላማቸው ጊዜውን ጠብቆ ከተገቢው በላይ ትርፍን ለማጋበስ ነው። ከነጋዴው ማህበረሰብ በተጨማሪ የሸማቹ ማህበረሰብም በእንደዚህ አይነት ተግባራት ተሰማርቶ ሊገኝ ይችላል። የሸማቹ ማህበረሰብ በዋነኝነት እንደዚህ አይነት ተግባር ውስጥ የሚሰማራው እቃው ከገቢያ ላይ ይጠፋል የሚል ፍራቻ ሲያድርበት ነው። ይህ የንግዱ ማህበረሰብም ሆነ የሸማቹ የማከማቸት ተግባር በዜጎች ላይ ወይም እንደ አጠቃላይ በሀገር ላይ የሚያደርሰው ኪሳራ በጣም ከባድ የሆነ ነው። ይህንም ተግባር ለመከላከል ይረዳ ዘንድ የኢትዮጵያ ንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 እቃን ስለማከማቸት እና ሰው ሰራሽ እጥረት መፍጠርን አስመልክቶ ድንጋጌዎችን የአካተተ ሲሆን የማስፈፀም ሀላፊነቱንም ለንግድ ሚኒስትር፤ ለንግድ ዉድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን እና ለንግድ ቢሮዎች ሰጥቷል።

Continue reading
  8131 Hits

የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ትኩረት ያልሰጠበት የገበያዉ ሁኔታ እና አተገባበሩ

 

መግቢያ

የኮሮና ወረርሽኝን ተከትሎ በሽታዉን ከመቋቋም ጎን ለጎን ኢተዮጵያ ካጋጠማት ችግሮች መካካል አንዱ የገበያ በተለመደዉ የፍላጎትና አቅርቦት መርህ (Demand and supply) አለመሄድ ነዉ፡፡ ይህ ችግር በአብዘኃኛዉ ያደጉ ሃገራት ላይ በተለይ በእንደዚህ አስጊ ሰዓት የመፈጠር እድሉ በጣም ዝቅተኛ ነዉ፤ ይህም የሆነበት ምክንያት በንጽጽር በአደጉት ሃገራት ያሉ ነጋዴዎች ያዳበሩት የንግድ ስነ ምግባር (Business ethics) ከእኛ የላቀ መሆኑ ነዉ፡፡ በሽታዉን አስመልክቶ በገበያዉ ብዙ አይነት ሸማቹን አደጋ ላይ የጣሉ ነገሮች ከአዋጁም በፊት ይሁን እሱን ተከትሎ እየተከሰቱ ይገኛሉ፡፡ ለአብነት ያክል ወደ ጎን /ወደ ታች/ ባሉ ነጋዴዎች የሚደረግ የንግድ ዉድድሩን የሚገቱ ስምምነቶች፤ እነዚህም ስምምነቶች ዋጋን ከፍ ማድረግ፣ መጠንን መቀነስ፣ የንግድ እቃዎችን መደበቅ፣ ሸማቾችን መምረጥ (ማግለል ) እና መሰል ድርጊቶችን ያካተቱ ናቸዉ፡፡ እንዲሁም ነጋዴ ወይንም ነጋዴ ባልሆኑ ሰዎች ደግሞ የማከማቸት ስራዎች በተለይ በከተሞች ላይ ጎልተዉ የሚስተዋሉ ችግሮች ናቸዉ፡፡ ኢትዮጵያ ምንም እንኳን እነዚህን ጉዳዮች የሚገዛ የህግ ማዕቀፍ ማለትም (የገበያ ዉድድር ና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ 813/2006) ቢኖራትም ነገር ግን ችግሩን ለማቃለል ብዙ የአፈጻፀም ጉድለቶች ይስተዋሉበታል፡፡ ይሀንንም አስመልክቶ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ና አሱን የሚያብራራዉ ደንብ ነበር፡፡ ነገር ግን በተጠበቀዉ ደረጃ ሳይሆን ገበያን ከመቆጣጠር አንጻር ትልቅ ክፍተትን ያሳያል፡፡

በዚህ አጠር ያለ ፅሁፍ ላይ አዋጁ ገበያን ከማረጋጋት አንጻጻር ትኩረት ማድረግ የነበረበትን ነገሮች እና ክፍተቶቹን፣ እንዲሁም ደግሞ በአፈጻጸም ደረጃ መሻሻል ያለባቸዉን ነገሮች ለመዳሰስ እንሞክራልን፡፡

 

Continue reading
  5629 Hits

Regional Market Under Siege

It is generally agreed amongst the international community, at least in principle, that liberalization of trade and allowing the free movement of goods, services and people, among countries that share common geographic boundaries and states situated at different poles of the earth, is a must.

In order to make the liberalization of trade a reality and to ensure the free flow of goods and services, states initiate various types of structures. The Common Market for Eastern & Southern Africa (COMESA) is Africa's largest economic community. COMESA was established by a treaty agreed in 1993 by 15 east and southern African states. Before this, some east and southern African states had tried to develop other structures. These include the sub-regional Preferential Trade Area (PTA) in 1978 and later the establishment of a Preferential Trade Area for Eastern & Southern Africa, in 1981. The latter became a stepping stone for the inauguration of COMESA.

This economic community embraces states with very differing economic, political and social experiences and legacies. Countries ranging from those with a large population size, such as Ethiopia, to countries with very small number of people, like Swaziland or Lesotho, are all members of this block.

Moreover, this block encompasses countries colonized by various European powers, such as Great Britain and France. This continues to test the vitality and stamina of African states to establish structures able enough to quench the interest of African minds and hearts. Hence, the difference of interests among member states of the common market makes the forum special.

Of course, the block is vital, in that its success or failure would help to test the capacity of African states to establish alliances ready to accommodate the differing interests of various states.

Continue reading
  8908 Hits