የተፋጠነ ፍትሕ የማግኘት መብት እና ተግባራዊ አፈፃፀሙ

 

 

የተፋጠነ ፍትሕ ወይም ዳኝነት ያለመስጠትና የፍርድ ቤቶች በአሠራርና በውሳኔ አሠጣጥ ላይ መዘግየት ደግሞ ዋነኛው የዳኝነት ሠጪው አካል ሊመልሰው የሚገባ የተገልጋዩ ጥያቄ ነው፡፡

ፍትሕ /ዳኝነት/ በመስጠት ላይ ያለ መዘግየት አንድ ጉዳይ ለፍርድ ቤት ቀርቦ የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥበት ጊዜ ድረስ ያለውን ያለበቂ እና አሳማኝ ምክንያቶች ያሉ መዘግየቶችን የሚያካትት ነው፡፡ ሁሉም ጉዳዮች እንደየባሕሪያቸውና ፀባያቸው የሚወስዱት የየራሳቸው ጊዜ ያላቸው ቢሆንም ተገልጋዮች ለፍርድ ቤት ያቀረቡት ጉዳይ እስኪወሰን ይፈጃል ወይም ይወስዳል ብለው የሚያስቡት ጊዜ ይኖራል፡፡ ችግሩ የሚያመጣውም በጉዳዮች ላይ ይፈጃል ወይም ይወስዳል ተብሎ ከሚገመተው ጊዜ በላይ እጅግ የተራዘመና ተከታታይ ቀጠሮዎች እየተሰጡ ጉዳዮች ሲጓተቱ ነው፡፡

እጅግ የተራዘመና የተዘገየ የፍትሕ ወይም የዳኝነት አሠጣጥ ሂደት ያለበት ሁኔታና አሠራርም ተከራካሪ ወገኖች ላይ ጥርጣሬ እና እምነት ማጣትን የሚያሳድር ከመሆኑም ባሻገር የፍትሕ ስርዓቱን ውጤታማነት እና ብቃት አጠያያቂ ሊያደርገው ይቻላል፡፡

Continue reading
  14324 Hits