መግቢያ
በሀገራችን ከ20 ሚሊዮን በላይ የአካል ጉዳት ያለባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደማንኛውም ሰው የተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት አገልግሎቶችን ለመጠቀም የተለያዩ መሰናክሎች ይገጥሟቸዋል፡፡ በዚህ ጽሑፍ አካል-ጉዳተኞች በኢትዮጵያ የብር ኖቶች አጠቃቀም እና በባንክ አገልግሎት አሰጣጥ ረገድ የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች ከሕግ እና ከአሰራር አንጻር እንዳስሳለን፡፡