ባለአንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበር በአዲሱ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013

 

1. አጭር መግቢያ

ባሳለፍነው ዓመት ኢትዮጵያ ላለፉት ስድስት አስር አመታት ስትጠቀምበት የነበረውን የንግድ ሕግ በማሻሻል በአዲሱ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 ተክታለች፡፡ ለቀድሞ ንግድ ህግ መሻሻል የተለያዩ ምክንያቶች ቢጠቀሱም በሌላው ዓለም የተለመዱ እና ለንግዱ ማህበረሰቡ አስፈላጊ የሆኑ አዳዲስ የንግድ ማህበራትን ማካተት አንዱ እና ዋነኛው ነው፡፡ በቀድሞ የንግድ ህግ አንድ ነጋዴ ሊመሠርት የሚችለው የንግድ ማህበር ወይም ድርጅት ስድስት ዓይነት ሲሆን እነዚህም ተራ የሽርክና ማህበር (ordinary partnership)፣ የህብረት ሽርክና ማህበር (general partnership)፣ ሁለት ዓይነት ኃላፊነት ያለበት የሽርክና ማኅበር (limited Partnership)፣ የእሽሙር ሽርክና ማህበር (joint venture) ፣ የአክሲዮን ማህበር (share compary) እና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል (private limited company) ማህበር ናቸው፡፡   

በአዲሱ የንግድ ሕግ ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (One person private limited Company) እና ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበር (Limited Liability Partnership) አዲስ የተጨመሩ ማህበራት ሲሆኑ ተራ የሽርክና ማህበር ደግሞ ከአማራጭ ማህበርነት ተቀንሷል፡፡ የዚህ አጭር ፅሁፍ ዓላማ አዳዲስ የተጨመሩትን እንግዳ የንግድ ማህበራት በመመርመር ማስተዋወቅ ነው፡፡

Continue reading
  9885 Hits