አስገዳጁ የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስ የሕንጻ መደርመስን ይከላከለው ይሆን?

መግቢያ

ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነው ጉዳይ ልክ የዛሬ አመት ገደማ በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ ልዩ ስሙ ሰሚት በሚባል ስፍራ የተደረመሰውን ህንጻ እና እሱን ተከትሎ የከተማ አስተዳደሩ ባወጣው ደብዳቤ (circular) መሰረት አስገዳጅ የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስ በድጋሜ እንዲኖር መደረጉን በማስመልከት ነው፡፡

እንደሚታወቀው ኢንሹራንስ (መድን) የሚለው ቃል ሲነሳ ምንግዜም ቢሆን ሊዘነጋ የማይችለውጉዳይ የአደጋ (risk) መኖር ነው፡፡ የአደጋ መከሰት ለመድን ቅድመ ሁኔታ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

ስለ መድን ታሪክ በአጭሩ ለመናገር ስነሳ አባይን በጭልፋ ኢንዲሉ! በጥቅቱ ጠቆም ለማድረግ ያህል የሚከተለውን ዐረፍተ ነገር እጽፋለሁ፡፡ በአለማችን ጥንታዊ የሚባለው መድንበ3ሺህ ዓ.ዓ ቻይናዊያን የጀመሩት ሲሆኑ በወቅቱም ነጋዲያን በሸቀጦቻቸው ላይ በአንድ ማጓጓዢያ እቃ መጫን እና መጠቀም የሚደርሰውን አደጋ ብሎም የሚመጡ የጎርፋ እና መሰል አደጋወችን ለመከላከል በርካታ የማጓጓዣ አማራጮች በወሰዱ ማግስት ነበር፡፡ ከዚያም በሜሶፖታሚያ (ሳምራዊያን) ስልጣኔ ወቅት እየተስፋፋ መመጣቱ በድርሳናት ላይ ሰፍሯል፡፡ በተለይም እኤአ በ1750 ዓ.ዓ በሰፈረው የንጉስ ሐሙራቢ ሕግ እንደተመለከተው ነጋድያን በባህር በሚነግዱበት ወቅት እቃውን በጥሩ ሁኔታ እንዲደርስ አስቀድመው በብድር ያስጭናሉ፤እቃውም በጥሩ ሁኔታ ከደረሰ ለአበዳሪው ተጨማሪ ገንዘብ ጭምር እንደሚከፍል ይናገራል፡፡ ዳሩ ግን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ዕቃው ቢጠፋ ወይም ቢዘረፍ የአበዳሪው ዋስትና ሙሉ ኃላፊነት ነው፡፡ (ቫውግሃን፡1997፡3) ከዚያም በኋላ በሜዲትራንያን ባህር የሚደረጉ የንግድ እንቅስቃሴወች ከነጋዲያን አስቀድሞ በተሰበሰበ አረቦን/Premium/ ለሚደርሱ የባህር ላይ ንግድ አደጋወች ማካካሻ ተደርገው ሲሰራባቸው ቆይቷል፡፡

በመካከለኛው ዘመንም በጥናታዊቷ የጣሊያን ዋጀንዋ ከተማ እኤአ በ1347 የመጀመሪያው ዘመናዊ የመድን ውል በሥራ ላይ ዋለ፡፡ ከዚህም የተነሳ መድን ከሌሎች ዓይነት የፍትሃብሄር ድርጊቶች ለመለየት ተሞክሯል፡፡ (ፍራንክሊን፡2001፡274)

ስለ መድን ውል በጠቅላላው ሲታሰብ ከትልቀቱ እና ስፋቱ የተነሳ በርካታ ተግዳሮቶች እንደሚኖሩ የታመነ ነው፡፡ በኢትዮጵያ መድን ሕግ እና ውሎች ዙሪያ በርካታ አሳሳቢ ችግሮች አሉ ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ እንኳንስ በሁለቱም ማለትም በሕግ እና በውሎች ዙሪያ ቀርቶ ከውሎች ውስጥ ጥቂቶችን በሚገባ ተመርጠው በአግባቡ ቢፈተሹ ብዙ አሳሳቢ ችግሮች እንደሚገኙባቸው የሚያከራክር አይደለም፡፡ (ዘካሪያስ ቀንዓ፡1998፡1)

Continue reading
  13828 Hits