የኢትዮጵያ ዜግነትን መልሶ ስለማግኘት - የኢትዮጵያ ዜግነትን ያለባለሥልጣኑ (ኤጀንሲው) ውሳኔ መልሶ ማግኘት የማይቻል ስለመሆኑ

ሰሞኑን የአቶ ጀዋር መሐመድን ኢትዮጵያዊ ዜግነት መልሶ የማግኘት ጉዳይ በኦፌኮ እና በምርጫ ቦርድ መካከል ክርክሮችን ማስነሳቱን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየሰማን እንገኛለን፡፡ በመሆኑም የዜግነት ሕጉ ኢትዮጵያዊ ዜግነት መልሶ ስለማግኘት ስላሰቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች እና ዜግነት መልሶ ማግኘት ስለሚረጋገጥበት መንገድ ያለኝን መረዳት ለማካፈል ወደድኩኝ፡፡

  12954 Hits

የዜግነት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸውን ማረጋገጥ የቅድመ ሁኔታዎቹ ቅድመ ሁኔታ ስለመሆኑ:- ለአቶ ግዛው ለገሰ የተሰጠ ምላሽ

ስለ ዜግነት አዎጁ በፃፍኩት ጽሑፍ ላይ አቶ ግዛዉ ለገሰ የተባሉ የሕግ ባለሙያ የፃፉት ምላሽ ደርሶኝ ተመለከትኩት፡፡ (የአቶ ግዛው ለገሰ ጽሑፍን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ፡፡ ) በመጀመሪያ ጸሐፊው የሕግ ባለሙያ እንደመሆናቸውም ብሎም ጽሑፉን ያወጡት እሳቸው ስላልተስማሙበት የሕግ ጽሑፍ ምላሽ ለመስጠት እንደ መሆኑ አቶ ጀዋር መሐመድን ለመደገፍ አልፃፍኩትም ለማለት አቶ ጀዋር የራሱ ጉዳይ ብለው ጽሑፉን መጀመራቸው፤ በጽሑፉ ውስጥ ለተነሱ እያንዳንዱ ክርክሮች ተገቢውን የሕግ ክርክር ከማንሳት ይልቅ በአመዛኙ በተራ የአዋቃለሁ ባይነት ጉራ ተሞልተው እኩይ ሴራ የሚሉ ያልተገቡ ቃላቶች መጠቀማቸው ብሎም በጽሑፉ ውስጥ  ለድምዳሜቸው ማስረጃ አድርገው ስላቀረቡት የሕግ ግምት (presumption of law) ምንነት ያሉት ነገር አለመኖሩ እና ሃሳባቸው ልክ ስለመሆኑ የሚደግፍ የሕግ አስተምሮ ሳይጠቅሱ በደፈናው የሕግ ግምት ያልገባው የሚል የወረደ ምላሽ መስጠታቸው ከሙያ ሥነ-ምግባር የወጣ ተራ ብሽሽቅ የመሰለ መውረድ ሆኖ አግንቼዋለሁ፡፡ በተለይ ደግሞ የመጀመሪየው ጽሑፍ በግልፅ ዜግነትን መልሶ ስለማግኘት ላይ ብቻ አተኮሮ እንደተፃፈ በተገለፀበት ሁኔታ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ስለሌላቸው እንደ በሕግ ዜግነት ስለማግኘት የመሳሰሉ ለምላሹ ፋይዳ በሌላቸው ዝርዝሮች ላይ ማተኮራቸውም አስቀድመው ላልተስማሙበት ጽሑፍ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት በቂ እድል ነፍጓቸዋል ጊዜያቸው አጥንቱን በመጋጥ ላይ መዋል ሲገባው መረቅ ለመጠጣት ውሏል፡፡

  9698 Hits