ቅድመ ሳንሱር በማንኛውም ቅርፅ በማንኛውም አካል ክልል ነው።
ሰሞኑን ዎልታ ቴሌቪዥን ለማሰራጨት ያዘጋጃቸውን ፕሮግራሞች እንዳያሰራጭ የፍርድ ቤት ትእዛዝ እንደተሰጠ አድምጠናል።
የመናገር ነፃነትና የሚዲያ ነፃነት የሕግ እና የአሰራር ገደቦች የትላንት ከትላንት ወዲያ የጭቆና አርእስቶች ነበሩ።
ምንም አስብ፣ ምንም አቅድ መናገርና ሀሳብህን በስእል፣ በፅሁፍ፣ በሙዚቃ እና በየትኛውም ራስን የመግለፅ ጥበብ መግለጽ ተፈጥሮአዊ እና ህገመንግስታዊ መብት ነው።