የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅን ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3(1) ድንጋጌ ዙሪያ የቀረበ መነሻ የሆነ አጭር የሕግ ማስታወሻ
ጠበቃ ዘርአይ ወልደሰንበት
Criminal Law Blog
"In Claris non fit interpretation." (When the text is clear, no interpretation is needed.") መግቢያበዚህ አጭር መነሻ የሆነ የሕግ ማስታወሻ ላይ በተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅን ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3(1) ድንጋጌ ዙርያ የቀረበ ሲሆን፤ በተለይም በዚህ ድንጋጌ ስር ስለተመለከተው የዋስትና መብት እና የዋስትና ክልከላ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ያልተያዙ ሰዎችና የተያዙ ሰዎች ላይ የሚተገበርበትን ሁኔታ የመጀመሪያ ምልከታ ለማድረግ ተሞክሯል። ይህንን የሕግ ማስታወሻ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ዋና ጉዳይ አንድ ደንበኛዬ የሆነ ሰው በሙስና ወንጀል ክስ የቀረበበት መሆኑን ከሌላ ሰው ከሰማ በኋላ ጉዳዩን አጣርቶ የሙስና ወንጀል ክሱ የቀረበበት የሙስና ወንጀል ችሎት ዘንድ ባልተያዘበት ሁኔታ በገዛ ፍቃዱ በቀረበ ጊዜ ችሎቱ የአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3(1) ድንጋጌን መሠረት በማድረግ በቂሊንጦ ማረፍያ ቤት ሆኖ ጉዳዩን እንዲከታተል ሲል በቅርቡ የሰጠው ትእዛዝ ነው።
Continue reading
የወልቃይት ሕዝብ የማንነት ጥያቄና ሕገ መንግሥቱ
ጠበቃ ዘርአይ ወልደሰንበት
Constitutional Law Blog
የማንነት ጥያቄ ምንድን ነው? የድንበር አከላለል ለውጥ (የድንበር ውዝግብ) ጥያቄስ ምንድን ነው? የኢትዮጵያ ሕግስ እንዴት ነው የሚጠብቃቸው? የዚህ ማስታወሻ ዓላማ እነዚህን ጉዳዩች ስለሚመለከቱት የሕግ ክፍሎች በማጥናትና ስለአተረጓጎማቸው አስተያየት በማቅረብ እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ ነው፡፡ ከእነዚህ ባሻገር ይህ ማስታወሻ ስለ ትግራይ ሕዝብ መልክዓ ምድራዊ አሰፋፈር ታሪካዊ ዳሰሳ ባጭሩ አድርጓል፡፡
Continue reading