ጸሐፊው በሕግ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ድግሪ ያላቸው ሲሆን በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ እና በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህጻናት ፍትሕ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ናቸው። 

ፍቺ ከፍርድ ቤት ውጭ - የሰበር ሰሚ ችሎት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔዎች አጭር ዳሰሳ
ተክለኃይማኖት ዳኜ በላይ
Family Law Blog
ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነው ጸሐፊው በሥራ ምክንያት በሚያያቸው መዝገቦች ስር ሲገጥሙት የነበሩ ክርክሮች እንዲሁም በተለያዩ አጋጣሚዎች ከሥራ ባልደረቦቹ ጋር ጋብቻ ከፍርድ ቤት ውሳኔ ውጭ በሁኔታዎች ስለሚፈርስበት አግባብ ያደረጋቸው ውይይቶች ሲሆኑ በዋነኛነት ግን የቅርብ ምክንያቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ የሰጠው ውሳኔ ነው። በፌደራሉ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 75 ሥር እንደተመለከተው ጋብቻ የሚፈርስባቸው ብቸኛ ሦስት ምክንያቶች ሞት ወይም የመጥፋት ውሳኔ፤ ጋብቻ ለመፈጸም መሟላት ካለባቸው ሁኔታዎች አንዱ በመጣሱ ምክንያት ጋብቻው እንዲፈርስ ሲወሰን እንዲሁም ፍቺ መሆናቸው የተመለከተ ሲሆን በአንቀጽ 117 ሥር እንደተመለከተው ደግሞ ጋብቻን በፍቺ ለማፍረስ ሥልጣን የተሰጠው ለፍርድ ቤቶች ብቻ ነው። 
Continue reading