ሀ. ወደኋላ ሄዶ ተግባራዊ የሚያደርጉ የታክስና ጉምሩክ ሕግ ድንጋጌዎች ሕገ መንግሥታዊነት
የታክስና የጉምሩክ ሕጎች ስንል ምን ማለታችን ነው? ከሕገ መንግሥቱ ጋር ያላቸው ዝምድናስ ምን ይመስላል ?
በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/08 አንቀጽ 2(36) መሠረት የታክስ ሕግ ማለት የጉምሩክ ሕግን ሳይጨምር የታክስ አስተዳደር አዋጅ፣ የፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ፣ የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ፣ የቴምብርና የተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ፣ ታክስ/ቀረጥ/ክፍያ ለመጣል የሚወጣ ሕግ እንድሁም እነዚህን አዋጆች መሠረት በማድረግ የሚወጡ ደንብና መመሪያዎችን ያካትታል፡፡ የጉምሩክ ሕግ ማለት ደግሞ በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 አንቀጽ 2(39) መሠረት የጉምሩክ አዋጁን፣ አዋጁን ተከትለው የሚወጡ የጉምሩክ ደንብና መመሪያዎችን እንድሁም የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን /የአሁኑ ገቢዎች ሚኒሰቴር/ የሚያስፈፀማቸውን ሌሎች ሕጎች ያካትታል፡፡