ሰላማዊ ሰልፍ፣ ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ የማድረግ መብትና ግዴታዎ አንዳንድ የሕግ ነጥቦች
ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ የአቢሲኒያሎው ድኅረገጽ ተከታታዮች! ዛሬ ስለሰላማዊ ሰልፍ እና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ የማድረግ መብትዎ አንዳንድ የሕግ ድንጋጌዎችን ልንነግራችሁ ወደድን፡፡ መሰብሰብና ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን አስመልክቶ በሀገራችን የሚጠቀሱ የሕግ መሠረቶች የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 30 ድንጋጌዎች እና የሰላማዊ ሰልፍና የፖለቲካ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 3/1983) ናቸው፡፡