- Details
- Category: Know Your Legal Rights - መብትና ግዴታዎን ይወቁ
ፖሊስ ካስቆምዎ
- ፖሊሱን ማናገር አይጠበቅቦትም፡፡ ሁሉጊዜም ቢሆን ያለመናገር ወይም ዝም የማለት መብት አለዎት፡፡ ያለመናገር ወይም ዝም የማለት መብት ማለት በተጠረጠሩበት ወንጀል ምንም ዓይነት መግለጫ ያለመስጠት መብት ማለት ሲሆን ስምና አድራሻዎትን ወይም ስለማንነትዎ መናገር ግን {tip የወንጀል ሕግ አንቀጽ 807 (ትዕዛዝን አለመፈፀም):: ማንም ስሙን ወይም ማንነቱን እንዲነግር፣ ሥራዎን/ሙያውን፣ መኖሪያ ሥፍራውን፣ አድራሻውን ወይም የግል ሁኔታውን የሚመለከት ማናቸውንም ሌላ ዝርዝር ጉዳይ እንዲገልጽ የሥራ ግዴታውን በሚያከናውን አንድ የመንግሥት ሠራተኛ በአግባቡ ሲጠየቅ ወይም ሲታዘዝ እንቢተኛ የሆነ እንደሆነ ከአንድ መቶ በር በማይበልጥ መቀጮ ወይም ከአንድ ወር በማይበልጥ የማረፊያ ቤት እሥራት ይቀጣል፡፡}ግዴታዎ{/tip} መሆኑን ያስታውሱ፡፡
- Liku Worku By
- Hits: 10396
Page 4 of 4