ተገዶ የመያዝን ሕጋዊነት ለማጣራት የሚቀርብ ክስ (Habeas corpus) እና የፍትሐብሔር እንድምታው

የአካል ነጻነት መብት በኢፌዲሪ ህገ መንግስት እውቅና ከተሰጣቸው የሰብአዊ መብቶች መካከል አንዱ እና ዋነኛው መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ይኸውም የሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 17 ድንጋጌ በግልጽ ማንም ሰው በህግ ከተደነገገው ስርአት ውጪ ሊያዝ እንዲሁም ክስ ሳይቀርብበት እና ሳይፈረድበት ሊታሰር የማይችል ስለመሆኑ ያስቀምጣል፡፡ በእርግጥ ይህ መብት በዚሁ ሕገ መንግስት መሰረት የሀገሪቱ የህግ አካል የሆኑ አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነነት ሰነዶችም ቢሆን እውቅና ከተሰጧቸው የሰብአዊ መብቶች መካከል አንዱ ስለመሆኑ እሙን ነው፡፡ 

  9890 Hits