የቀን ገቢ ግምት መመሪያ ቁጥር 123/2009 በማስፈጸም ረገድ የሚታዩ ችግሮችና የመፍትሔ ሐሳብ

አንድ ግብር ከፋይ በንግድ እንቅስቃሴው ያመነበትን ወስኖ ያቀረበውን የሂሣብ መግለጫዎችን የታክስ ባለስልጣኑ የግብር ኦዲት በመስራት ግብር ከፋዩ ሊከፍል የሚገባውን ግብር ይወስናል፡፡ በአገራችን የግብር አወሳሰን ዘዴዎች ሁለት ናቸው፡፡ እነዚህም በሂሳብ መዝገብ ወይም በግምት መሠረት ናቸው፡፡

ግብር ከፋዩ ለግብር አወሳሰን ያቀረበው የሂሳብ መዝገብ ሰነዶች ከተጣራ /ከተመረመረ/ በኋላ በመዝገቡ መሠረት ሊከፈል የሚገባው ግብር የሚወሰን ሲሆን፤ በሌላ በኩል የታክስ ባለሥልጣኑ ግብር ከፋዩ ሊከፍል የሚገባውን ግብር በግምት ሊወስን ይችላል፡፡

  15413 Hits