- Details
- Category: Non-Contractual Liability (Tort Law)
- Hits: 7618
በሌላ ሰው ቤት ወይም መሬት መግባት ቁጥር /2053/ እና ንብረት ስለመደፈር ቁጥር /2054/
የኢፊድሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 40 ስር የግል ንብረት ምን ማለት እንደሆነ ዘርዝሮ ማንኛውም የኢትዩጵያ ዜጋ የግል ንብረት ባለቤት መሆኑ /መሆኗ እንደተከበረ የሕግ ጥበቃም እንዳለው ደንግጓል፡፡ ይህ መብት የመሸጥ፣ የመለወጥ፣ የማውረስ፣ ባለቤትነት የማዘወር ወይም የካሣ ክፍያ የመጠየቅ መብትን ይጨምራል እንዲሁም መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ ቢሆንም በይዞታ የመያዝና የመጠቀም መብት መኖሩን በዚሁ አንቀፅ ስር ተደንግጓል፡፡
ስለሆነም በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2053 መሠረት አንድ ሰው በሕግ ሳይፈቀድለትና የቤቱ ባለቤት ወይም ባለይዞታ እንዲሁም የመሬቱ ባለይዞታ ሳይፈቅድለትና ያለመፍቀዱንም በግልፅ እየተናገረ እላይ በተጠቀሰው የቤት ሀብት ወይም የመሬት ይዞታ ከገባ የገባው ሰው ጥፋተኛ ነው፡፡
አንድ ሁለት ነጥቦችን እናንሳ የመጀመሪያው በሕግ ሳይፈቀድለት እንግሊዝኛው /without due legal authority/ የሚለው ነው፡፡
ለምሳሌ አንድ ፖሊስ ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ ይዞ ቢመጣና ለመበርበር ቤቱ ውስጥ ቢገባ አግባቡ በሕግ ሳይፈቅድለት አይባልም ፡፡ እንዲሁም አንድ ሰው የወንጀል ድርጊት ፈፀሞ ወደ አንድ ቤት ወይም መሬት ቢገባና ሌላ ሰው ወይም ፖሊስ ተከትሎት እዛ ቤት ወይም መሬት ቢገባ አግባቡ በሕግ ሳይፈቅድለት ነው አይባልም፡፡ በዚህ ሁኔታ ወደ ቤት ወይም መሬት የገባ ሰው የባለቤቱ ወይም የበላይዞታው ፍቃድ ባይኖር እንኳን ጥፋተኛ አይባልም፡፡
ሁለተኛው ነጥብ የማይፈቀድ መሆኑን በግልፅ እየተናገረ የሚለው ነው፡፡ ይህ ተቃውሞ በቃል ወይም በፅሑፍ ሊሆን ይችላል፡፡ በማጠረስ ሊሆን ይችላል? በሌላ በኩል ደግሞ ወደ መሬት ወይም ቤት መግባቱ የግድ በገቢው በራሱ መፈፀም አለበት? በቤት እንሰሳ አማካኝነት ቢሆንስ?ግዑዝ በሆነ ነገርስ ሊሆን ይችላል ? ለምሳሌ እኔ ቤት የበቀለ ዛፍ ቅርንጫፍ ወደ ጉረቤቴ ቢያልፍስ? ቆሻሻ ወደ ሌላ ሰው ቤት ቢጣልስ? ዛሬ ቴክኖሎጂው በሪሞት ኮንትሮል በሚንቀሳቀስ አንስተኛ አሸንጉሊት መኪና ወደ ሌላ ሰው ቤት ወይም መሬት ቢገባስ? ሰልጣኖች እስቲ በእነዚህ ጥያቄዎች ላይ ተወያዩባቸው፡፡
ንብረት ስለመደፈር ቁጥር /2054/
እላይ የተመለከትነው የማይንቀሰቀስ ንብረት ነው በዚህ ክፍል ደግሞ የምንቀሳቀስ ንብረትን አስመልክቶ ሕጉ ምን እንደሚል እንመለከታለን፡፡ እንደህ ዓይነት ንብረትንም አስመልክቶ ቁጥር 2054 በሕግ ሰይፈቀድለት የሚለውን ሐረግ ይጠቀማል፡፡ ስለሆነም ከላይ ለማስቀመጥ አንደሞከርነው አንድ ፖሊስ አንድን የሚንቀሳቀስ ንብረት በእግዚቢትነት ለመያዝ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይዞ ቢመጣና ንብረቱን ቢወስድ ሕገ ሳይፈቅድለት ወሰደ አያስኘውም፡፡ የግል ንብረቱ ወይም የባለይዞታው ፍቃድ እንኳን ሳይኖር ቢወሰድ ጥፋተኛ አያስብለውም፡፡
ሌላው ነጥብ አለመፍቀዱንም በመግለፅ ሲናገር የሚለውን በሌላ የፍትሐብሔር ቁጥር ለማስረዳት ቁጥር 1148/2/ መሠረት አንድ ሰው እጅ ያደረገው ነገር በንጥቂያ ከተወሰደበት የተወሰደበትን ነገር መመለስ እንደሚችል ይደነግጋል፡፡ ስለዚህ እንዳይነጥቅ የሚያደርገው ትግል ነገሩ እንዳይወሰድበት አለመፍቀዱን መግለጫ ነው ስለሆነም አንድ ሰው የሌላን ሰው ተንቀሳቃሽ ንብረት ሕግም ሳይፈቅድለት ወይም ባለቤቱ ወይም ባለይዞታው ሳይፈቅደለት የወሰደ እንደሆነ በቁጥር 2050 መሠረት ጥፋተኛ ነው፡፡