- Details
- Category: Non-Contractual Liability (Tort Law)
- Hits: 7524
ልዩ ልዩ
ውል ከማድረግ በፊት የተደረገ ድርድር ቁጥር 2055
አንድ ተዋዋይ ውል ገብቶ በውሉ መሠረት ግደታውን ሳይወጣ ከቀረ በውሉ መሠረትና በውል ድንጋጌዎች መሠረት አላፊ ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን ውል ከመግባቱ በፊት አንደ ሰው ሌላኛውን ወገን ውል እንዲገባ ሊያግባባውና ውሉንና ከውሉ የሚያገኘውን በማሰብ ለወጪ ሊዳርገው ይችላል፡፡ ይህን ወጪ ከወጣ በኃላ ግን አግባቢው ውል ውስጥ ላይገባ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ አግባቢው በቁጥር 2055 መሠረት ጥፋተኛ ይሆናል፡፡
በውል የገባውን የግዴታ ቃል ስላለማክበር ቁጥር /2056/
የዚህ ርዕስ ቁጥር ትክክል አይመለስንም ምክንያቱም አንድ ሰው በውል የገባውን የግዴታ ቃል ያለማክበሩ ጉዳይ የሚዳኘው ከውል ውጨ ሕግ አላፊነት ሳይሆን የሚዳኘው ቁጥር 2047/2/ ስር እንደተመለከተው በውል አለመፈፀም ድንጋጌዎች መሠረት ነው፡፡
ሁለተኛ ደግሞ ቀጥለን እንደምንመለከተው ሁለት ሌሎች ተዋዋዩች የመሠረቱትን ውል ነው እንዳይተገበር መሰናክል የሚሆነው ፡፡ ስለዚህ ርዕሱ መሆን ያለበት በተዋዋይ ወገኖች መሃል ጣልቃ መግባት ነው፡፡
በቁጥር 2056 /1/ መሠረት ሁለት ቀድሞ ውል የተዋዋሉ ይኖራሉ፡፡ ሌላ ሶስተኛ ወገን ደግሞ ይህ ሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች የገቡት ውል እንዳይተገበር ከአንደኛው ተዋዋይ ጋር ሌላ ውል ያደርጋል ፡፡ ሁለት ነጥቦች ግልፅ መሆን አለባቸው፡፡ መጀመሪያ ሶስተኛው ወገን በሁለቱ ሰዎች መሃል ውል መኖሩን ማወቅ አለበት፡፡ የዚህ እውቀት ከሌለው በዚህ ቁጥር መሠረት ተጠያቂ አይሆንም ሁለተኛ ነገር ሶስተኛው ወገን በዚህ ድርጊቱ ቀድሞ በሁለት ወገኖች መሃል የተደረገ ውል እንዳይተገበር ማድረግ አለበት፡፡ እነዚህ ሁለቱ ሁኔታዎች ካሉ ነው ጥፋተኛ የሚባለው፡፡ ውል እንዳይተገበር ሆኗል በዚህም ጉዳት ደርሶብኛል የሚል ወገን ይህን እንዳይሆን አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ይህን አስፈላጊውን ጥንቃቄ በቸልተኝነት ሳያደርግ ከቀረ በቁጥር 2056 /2/ መሠረት የኃለኛው ተዋዋይ ጥፋተኛ አይሆንም፡፡
የማይገባ ውድድር ቁጥር /2057/
የማይገባ ውድድርን ለማወቅ ጤናማ ውድድርን /fair competition/ ብናውቅ አይከፋም፡፡ ጤናማ ውድድር ሁለት ወይም ከሁለት የሚበልጥ በተመሳሳይ ሥራ የተሰማሩ ወገኖች /ነጋዴዎች/ ለደንበኖቻቸው የተሻለ አገልግሎት ወይም ሸቀጥ /Services or goods / ለመስጠት ወይም ለመሸጥ የሚደረግ ውድድር ማለት ነው፡፡ ይህም በሚከተለው መንገድ ይገለፃል፡፡
- የሸቀጦችን ዋጋ በመቀነስ
- ደረጃውን የጠበቀ ሸቀጥ በማምረት
- ደንበኛን ሊያረካ የሚችል ግልጋሎት
በመስጠት እና በሌሎችም፡፡ ሆኖም ግን ስለሌላኛው ተወዳዳሪ ነጋዴ ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ ማሳተም፣እንዲሁም ሀሰተኛ ወሬ መንዛት፣ የሌላኛውን ተወዳዳሪ የንግድ ምልክት ወይም አርማ /Trade name or trade mark/ ወይም ተመሳሳይ መያዥ /container/ መጠቀም የማይገባ ወይም ጤናማ ያለሆነ ውድድር ስለሆነ ይህን አደርጊ በቁጥር 2057 መሠርት ጥፋተኛ ይሆናል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዚ ፍ/ቤት ለተጉጂው ካሣ እንዲከፈል ከማዘዙም በተጨማሪ በቁጥር 2122 መሠረት ድርጊቱ እንዲቆም ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡
የሌላውን አስመስሎ ማስራት ቁጥር /2058/
በእግሊዝኛው /simulation/ የሚባለው ነው፡፡ በአጭሩ ማስመሰል በዚህም ሌላውን ለጉዳት መዳረግ ነው፡፡ በከተማው አባባል ቁጭ ይበሉ የሚባለው ነው፡፡ ይህን በምሳሌ እናስረዳ፡፡
አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ መሄጃ መንገድ ላይ የኢትዩጵያ አየር መንገድ አይሮኘላንን በሚመስል መልክ የተሰራ ካፍቴሪያ ይገኛል፡፡ ስሙም ለንደን ካፌ ይባላል፡፡ አንድ ቀን አንድ የከተማ ጮሌ ወደ ሐጂ ለመጓዝ የሚፈልጉ የገጠር ሰዎችን አገኘ እንበል ጉዳያቸውን ከጠየቃቸው በኃላ ወደ ሐጂ መጓዝ እንደሚፈልጉ ገለፁለት እንበል፡፡ ይህ የከተማ ጮሌ ሰዎቹን ወደ ተባለው የአይሮኘላን ምስል ወስዶ ካፍቴሪያው ውሰጥ ካስገባቸው በኃላ ብሩን አምጡ እኔ ከፍዬ እስክመጣ ድረስ አይሮኘላኑ ሞተሩን ያግላል አሁንም እንደሚታዩት እየጋለ ነው በማለት የሻይና ቡና መስሪያ ማሸኑ ሲሰራ ያሳያቸዋል እንበል፡፡ የገጠሩ ሰዎችም አመነውት ብራቸውን ይሰጡታል፣ ጮሌውም “መጣሁ” ጠብቁኝ በማለት እዛው ጥሏቸው ሄደ እንበል፡፡ ቢጠብቁት አይመለስም፣ አስተናጋጅ ትመጣና ምን ልታዘዝ ትላለች፡፡ ወደ ሐጂ ለመብረር እዚህ “አይሮኘላን” ውስጥ አንደገቡ ቲኬታቸውንም እየተጠባበቁ መሆናቸውን ይነግሯታል፡፡ አስተናጋ²ም እውነተኛውን ትነግራቸዋለች፡፡ ማስመሰል በዚህም ሌላውን መጉዳት ይህ ነው፡፡
ያልተስተካከለ ወሬ ቁጥር /2059
በዚህ ቁጥር መሠረት አንድ ሰው ያልተስተካከለ ወሬ /መረጃ/ በማሰተላለፍ ተጠያቂ አይሆንም፡፡ ተጠያቂ ለመሆን ሁለት ነገሮችን ማሟላት አለበት፡፡ የመጀመሪያ ሆን ተብሎ ወይም በቸልተኝነት የተላለፈውን መረጃ / information / የተቀበለው ሰው ወይም ሌላ ሰው በመረጃው መሠርት እንደሚተገብርና /act/ ሁለተኛ ደግሞ በመረጃው መሠረት /act/ ያደረገው ሰው ላይ ጉዳት እንደሚደርስበት ማወቅ አለበት፡፡ ለምሳሌ ሰዎች በአንድ አዳራሽ ውስጥ ፊልም ወይም ትያትር እየተመለከቱ እያለ አንድ ተመልካች እሳት ሳይነሳ ወይም ሳይኖር እሳት! እሳት! እያለ ቢጮህና ይህንንም በማድረጉ ሰዎች ትርምስመሳቸው እንደሚወጣና አንዱ በአንዱ ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ እያወቀ ይህን ያደረገ እንደሆነ በቁጥር 2059/1/ መሠረት ጥፋተኛ ይህናል፡፡
ይህ ንዑስ ቁጥር ለተራ ሰው ነው፡፡ ባለሞያ ከሆነ ግን ከሞያው ጋር በተያያዘ መስጠት የሚገባው መረጃ ትክክለኛ መሆን አለበት፡፡ በሰጠው መረጃ ሰዎች /act/ ማድረግና ጉዳት ሊደርስባቸው አይጠበቅም፡፡ ሞያው ጋር በተያያዘ አንድ ባለሞያ ትክክለኛ መረጃ አለመስጠት ብቻውን ጥፋተኛ ያደርገዋል 2059/2/
ሆኖም ግን አንድ ሰው መልሶ ገንዘብ መክፈል ስለሚችል ገንዘብ እንደሰጠው ለማድረግ ሥራ ለማስገኘት ስለችሎታው መናገር የንግድ ዕቃ እንዲሰጠው ስለዚህ ሰው ችሎታ ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ መስጠት በፅሑፍ ተደርጐ ተፈርሞ ካልተሰጠ በሰተቀር በቁጥር 2060 መሠረት ተጠያቂ አይደለም፡፡ ይህን አንድ ምሳሌ በመውሰድ ለማስረዳት እንሞክር የአንድ ሰው ዘመድ የሆነችን አንዲት ልጅ በቤት ሠራተኝነት ለማስቀጠር የተለያዩ ምግቦችን የመስራት ችሎታ አላት በማለት ሥራ ቢያስገኝላት ይህ ሰው ይህን ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ የሰጠው ለልጅቷ ሥራ ለማስገኘት ብቻ ከሆነ ጥፋተኛ አይባልም፡፡ ግን እነዚህን ትክክለኛ መርጃዎች የሰጠ ሰው ቃሉን በፅሑፍ አድርጐ ፊርማውን ካኖረ በቁጥር 2060/2/ መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡
ምስክሮች ቁጥር /2061/
ምስክሮች አንድ ነገር መፈፀሙን ወይም አለመፈፀሙን /occurrence or non occurrence/ ወይም አንድ አድራጉት መኖሩን ወይም አለመኖሩን /the existence or the non existence/ ሊመሰክሩ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ የጋብቻ ስርዓት መፈፀሙን ወይም አለመፈፀሙን ወይም ጋብቻ መኖሩን ወይም አለመኖሩን ሊመሰክሩ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም ይህ የሰጡት የምስክርነት ቃል እርግጠኛ /accuracy/ ስለመሆኑ አለፊዎች ናቸው፡፡
ሰዎች ይህን በምስክሮች የተሰጠውን ቃል በመንተራስ አንድ ነገር ሊፈፅሙ ይችላሉ፡፡ለምሳሌ አንዲት ሴት ባለትዳር ከሆነ ሰው ጋር ምስክሮች ትዳር የለውም በማለታቸው ትዳር ልትመሰርት ትችላለች፡፡ በዚህ አድራጉታቸው ለሴትየዋ ኃላፊ ይሆናሉ በሌላ በኩል ደግሞ እነዚሁ ሰዎች ይህን የምስክርንት ቃል የሰጡት በቅን ልቦና ከሆነና በሌላ ሰው ተሳስተው መሆኑን ካረጋገጡ በዛ ባሳሳቻቸው ሰው ላይ ክስ መመስረት ይችላሉ ፡፡ 2061/3/፡፡
ምክር ወይም የአደራ ቃል /advice or recommendation/ ቁጥር /2062/
አንድ ሰው ለሌላ ሰው አንድ ነገር እንዲያከናውን ወይም እንዳያከናውን ምክር ሊሰጠው ይችላል፡፡ ለምሳሌ ጠንቋይ ዘንድ ቢሂድ ከበሽታው እንደሚድን ሊመክረው ይችላል፡፡ መካሪው በዚህ ብቻ ከተወሰነ በቁጥር 2062 መሠረት ጥፋተኛ አይደለም ሆኖም ግን ከዚህ ምክር አልፎ ጠንቋዩ ዘንድ ይዞት ብሄድና በዚህ ምክንያት ምክር ተቀባዩ ጉዳት ቢደርስበት መካሪውና መሪው ጥፋተኛ ይሆናል፡፡
ስለ መያዝ /Distraint/ ቁጥር 2063
አንድ ባለዕዳ ዕዳውን በጊዜ ላይከፍል ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ አበዳሪው ባለዕዳው ዕዳውን እንዲከፍል ለማስገደድ የባለዕደውን ንብረት ሊይዝ ይችላል፡፡ ለምሳሌ የአንድ ሰው ከብት ወደ ሌላ ሰው ማሳ ገብቶ አዝዕርቱን ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ባለእርሻው ባለከብቱ ከብቶቹ ያደረሱትን ጉዳት እንዲከፍለው ለማድረግ ከብቶችን ሊይዝ ይችላል ይህ ጥፋት አይደለም፡፡
ይህ መያዝ ጥፋት የሚሆነው ባለዕዳው ሊቀበል ከሚገባው ገንዘብ ጋር የተያዘው ንብረት ከዕዳው ሲበልጥ ነው በተጨማሪም መያዙ አስፈላጊ ሳይሆን ሲቀር ለምሳሌ ከብቶቹ ላጠÕት ባለከብቱ እንደሚከፍል ዋስ ቢጠራ መያዙ ያለአስፈላጊ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ያዡ ጥፋተኛ ይሆናል፡፡
የፍርድ ትዕዛዝ ስለመፈፀም ቁጥር /2064/
ሆኖም ንብረት በፍርድ አስፈፃሚ ሊያዝ ይችላል፡፡ የተያዘው ንብረት ከዕዳው ሊበልጥ ይችላል፡፡ ሆኖም የፍርድ አስፈፃሚው ጥፋተኛ አይሆንም ነገር ግን የሚከተሉት መሟላታቸውን እርግጠኛ መሆን አለብን፡፡
የፍርድ አስፈፃሚው ንብረቱን የያዘው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለማስፈፀም መሆን አለበት፡፡ በሌላ አካል የሚሰጥ ትዕዛዝ ለማስፈፀም መሆን የለበትም ማለት ነው፡፡
ትዕዛዙ ትክክለኛ አሰራሩን የያዘ ፎርም መሆን አለበት፡፡ ትዕዛዙ ትክክለኛ ነው ለማለት ትዕዛዙ የዳኛ ፊርማና የፍርድ ቤቱ ማህተም ሊኖረው ይገባል ትዕዛዙ በፅሑፍ መሆን አለበት፡፡
ስለሆነም ትዕዛዙ የዳኛውን ፊርማ ያልያዘ ከሆነ ወይም የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ያልያዘ ሆኖ እያለ ንብረቱን ከያዘ ፍርድ አስፈፃሚው ጥፋተኛ ይህናል 2064/2/ በተጨማሪ ፍርድ አስፈፃሚው ከተሰጠው ትዕዛዝ ውጭ ከሆነ ለምሳሌ በትዕዛዙ ላይ የተባለውን ንብረት ሳይሆን ሌላ ንብረት ከያዘ ወይም ተጨማሪ ንብረት ከያዘ ወይም ትዕዛዙን ሕግን ባለማክበር የፊፀመ እንደሆነ ለምሳሌ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ መሠረት ሊያዙ የማይችሎትን ንብረቶች ከያዘ ጥፋተኛ ይሆናል፡፡ 2064/2/
ስለ ይርጋ ቁጥር /2065/
አንድ ሰው በአንድ ጉዳይ ላይ ክስ ለመመስረት የሚችለው የይርጋ ጊዜው ሳያልፍበት ነው፡፡ ለምሳሌ በውል የይርጋ ጊዜው 10 ዓመት ነው፡፡ ስለሆነም ባለገንዘቡ በባለዕዳው ላይ በ10 ዓመት ጊዜ ውስጥ ክስ መመስረት አለበት፡፡ ይህን ከላደረገ ክሱ በይርጋ ይታገድበታል፡፡ በሌላ በኩል ባለዕዳው ዕዳውን ባለመክፈሉ በቁጥር 2030 መሠረት ጥፋተኛ ነው፡፡ ይህ ቁጥር ተጠቀሱ ክስ ቢመሠረትበት ባለዕዳው ቁጥር 2065ን በመጥቀስ በይርጋ ደንብ መክሰሰ ቀርቶልኛል ብሎ ቢከራከር ጥፋተኛ አይሆንም፡፡