Abyssinia Law Abyssinia Law
  • Home
  • Laws
    • Search Federal Laws
    • Regional Laws
    • Constitutions
    • Audio Legal Resources
  • Decisions
    • Cassation Decisions by Volume
    • Cassation Decisions Database
    • FFI Court Commercial Bench Decisions
  • Blog
  • Resources
    • Researches Papers
    • Policies and Strategies
    • Codes, Commentaries and Explanatory notes
    • Legal Forms
    • Bench Books
    • Human Right Documents
    • Modules and Materials
    • About Our Laws
    • Quick links
  • Study On-line
  • know your rights
  • Lawyers
  • About Us
    • Who Are We
    • Our Partners
    • Advertise with Us
    • Privacy Policy
    • Contact us
    • Professional Advice?
    • How to submit a blog post
  • login
Abyssinia Law Abyssinia Law
  • Home
  • Laws
    • Search Federal Laws
    • Regional Laws
    • Constitutions
    • Audio Legal Resources
  • Decisions
    • Cassation Decisions by Volume
    • Cassation Decisions Database
    • FFI Court Commercial Bench Decisions
  • Blog
  • Resources
    • Researches Papers
    • Policies and Strategies
    • Codes, Commentaries and Explanatory notes
    • Legal Forms
    • Bench Books
    • Human Right Documents
    • Modules and Materials
    • About Our Laws
    • Quick links
  • Study On-line
  • know your rights
  • Lawyers
  • About Us
    • Who Are We
    • Our Partners
    • Advertise with Us
    • Privacy Policy
    • Contact us
    • Professional Advice?
    • How to submit a blog post
  • login
Details
Category: Non-Contractual Liability (Tort Law)
18.Feb
Hits: 8588

ከውል ውጪ ስላለኃላፊነት

ከውል ውጪ ያለ አላፊነት ሕግ ማለት  ሕግ  መንግስቱ ጥበቃ ባደረገላቸው የሰዎች  የንብረት እና  የሰውነት መብቶች  ላይ ጉዳት ሲደርስ ጉዳቱን  ያደረሱ ሰዎች  ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች እንዲክሱ  የሚያስገድድ  ሕግ ነው፡፡

 

ጥበቃው  በሶስት መንገድ  ሊደረግ ይችላል፡፡ አንዱ ጉዳቱን  ያደረሱ ሰዎች ጉዳቱን ለደረሰባቸው  ሰዎች  በገንዘብ  መልክ ካሣ  እንዲከፈሉ በማድረግ ሊሆን ይችላል፡፡ እንዲሁም  ከአድራጐታቸው  እንዲቆጠቡ ፍ/ቤት  ትዕዛዛ በመስጠት  ሊሆን  ደችላል፡፡ በእንግሊዝኛው injunction የምንለው ነው እና በሶስተኛ  ደረጃ  ጉዳቱን  በዓይነት እንዲክሱ በማድረግ ሊሆን ይችላል፡፡  በእንግሊዝኛው  /Restitution/ የምንለው ማለት ነው፡፡ ሕግ  እነዚህን  ጥበቃዎች  በሙሉ የሚያደርገው  በፍርድ ቤቶች  አማካኝነት  መሆኑ ሊጤን  ይገባል፡፡ በእርግጥ አንዳንድ ጊዜ  ባለመብቶቹ  በራሳቸው  መብታቸውን እንዲያስከብሩ ስልጣን ሊሰጣቸው ይችላል፡፡  ለምሳሌ  በፍትጠብሔር ሕግ  ቁጥር  1149 ስር  እንደ ተደነገገው፡፡

 

መርህዎች

 

ከውል ውጪ ያለ አላፊነት ሕግ  መርሆዎችን  በሚቀጥለው  ክፍል በሰፊው  እንመለከታለን፡፡ በአሁኑ  ግን አጠር ባለ መልኩ  ለመግቢያ  የሚሆኑንን እንወያይ፡፡  አንድን  ሰው በዚህ  ሕግ ሥር  አላፊ ለማድረግ አራት  ዋና ዋና   ነገሮች ያስፈልጋሉ፡፡  የመጀመሪያው አንድን  ድርጊት  ማከናወን በእንግሊዝኛው /Act/ የምንለው ሲሆን  ሌላው ያለ ማከናወን በእንግሊዝኛው  / omission / የምንለው ነው በሁለተኛ ደረጃ  ይህ ማከናወን ወይም ያለማከናወን  ጉዳት በእንግሊዝኛው   /Damage / የምንለውን ማድረስ አለበት፡፡  በሶስተኛ  ደረጃ በደረሰው ጉዳትና በድርጊቱ  መሃል  ምክንያታዊ  ግንኙነት / Casual relationship/   ሊኖር  ይገባል፡፡  በአራተኛ  ደረጃ ይህ  የደረሰው ጉዳት በሕግ  እውቅና ያገኘ  መሆን  አለበት፡፡  /A kind  of harm recognized as attracting legal liability / የምንለው ነው፡፡

 

ከላይ  ያስቀመጥነውን በምሳሌ  እናስረዳ፡፡  አቶ ጫላ  ጥንቃቄ  በጉደለው መልኩ  መኪና እየነዳ ከዋናው መንገድ ወጥቶ  እግረኞች  በሚንቀሳቀሱበት  ላይ በመውጣት  አቶ መሐመድ  ላይ ጉዳት አደረሰ እንበል፡፡   ድርጊቱ የአቶ ጫላ መኪና ያለጥንቃቄ መንዳት ሲሆን  ጉዳቱ  በአቶ መሐመድ  የጉን አጥንት  መሰበር ነው፡፡  ለዚህ ጉዳት ምክንያት ደግሞ  የአቶ ጫላ መኪናውን በጥንቃቄ  አለመንዳት ነው፡፡  ማለትም የአቶ ጫላ ጥፋት /fault/ ነው፡፡ ስለሆነም  አቶ ጫላ አቶ  መሐመድን  ሊከስ አላፊነት  አለበት ማለት ነው፡፡

 

በአንዳንድ ሁኔታዎች  ስር ግን  ጉዳትም ደርሶ ጉዳት አድራሹ ተጠያቄ  የማይሆንበት ብሎም ጉዳት የደረሰበትን የማይካስበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡  በምሳሌ እናስርዳ፡፡ አንድ  የጫማ  ችርቻሮ  ንግድ  የሚነግድ  ነጋዲ ሃይሊ ገብረሥላሴ  መንገድ ላይ አለ እንበል፡፡  ሚደቅሳ  አጠገቡ  ተመሳሳይ  ጫማ ንግድ  ከፍቶ  ጫማዎቹን  በርካሽ  ሸጠ እንበል   በዚሁ  ምክንያት  የመጀመሪያው ነጋዴ ከስረ እንበል፡፡

 

በዚህ ምሳሌ  ጉዳት አለ፡፡  ጉዳቱም የጫማ ቤቱ ንግድ መዘጋት  ነው፡፡  ለጉዳቱም  ምክንያት  የሚደቅሳ አጠገቡ ሌላ  ተመሳሳይ  ጫማ ቤት መክፈትና  ጫማዎችን  በርካሽ  መሸጥ ነው፡፡  ለደረሰው ጉዳት  /ኪሣራ/ ግን ጫላ ተጠያቂ አይደለም፡፡ ምክንያቱም  ጉዳቱ  በሕግ  እውቅና ያገኘ  አይደለም እና ነው፡፡  ይህ  በላቲን  /damnum sine injuria / ይባላል፡፡

 

በሌላ በኩል  ደግሞ  ጉዳት  ሳይደርስ  ካሣ  የሚከፍልበት  ሁኔታ  ሊኖር  ይችላል፡፡  ለምሳሌ  ኡከን ኡከች  ጣሂር ሳይፈቅድለት  የጣሂርን መሬት  ቢያቋርጥ  ኡከን ኡከች መሬት  ላይ  ምንም ጉዳት  ሳይደርስ ጣሂር ተጠያቂ ሊሆን ይችላል፡፡  ይህ በላቲን  / injuria sine damno/ ይባላል፡፡  ጉዳት  መኖሩን  ማስረዳት  ሳያስፈልግ  አንድን ሰው ተጠያቂ ማድረግ እንደ ማለት ነው፡፡

 

ሕግ  ጥበቃ  የሚያደርግላቸው ጥቅሞች /መብቶች/  / Interests /

 

ሕግ  ጥበቃ  የሚያደግላቸው  መብቶችን  ከላይ ሕግ መንግስቱ  ጥበቃ  ያደረገላቸው ብለን  ካስቀመጥናቸው መብቶች  አንፃር በሶስት ዋና ዋና  ክፍሎች  ልንከፍላቸው እንችላለን፡፡  የመጀመሪያዎቹ  ከአንድ ሰው ሰውነት ጋር  የተያያዙ መብቶች  ሲሆኑ ሁለተኛ ከንብረት   ከምጣኔ  ሀብት  ጋር  የተያያዙ  መብቶች ናቸው፡፡  በእንግሊዝኛው / Personal property / እና  / economic interest/ የሚባሉት ናቸው፡፡ ሶስተኛ  ደግሞ  ሌሎች  ብለን  መመደብ እንችላለን፡፡

 

ከሰውነት ጋር ተያያዥነት ያላቸው መብቶች

 

ከላይ  በክፍል አንድ ስር  የኢፊዲሪ  ሕገ መንግስት  እውቅና  የሰጣቸውና  ጥበቃ  ያደረገላቸውን  መብቶችን  አይተናል፡፡  ከእነሱም መሃል  ከሰውነት ጋር  ተያያዥነት  ያላቸው  መብቶች  አንዱን ክፍል ይይዛሎ፡፡  ሕግ መንግስቱን መነሻ  በማድረግ  ከውል ውጨ አላፊነት  ሕግ እነዚህን  መብቶች ይዘረዝራል፡፡

 

እነዚህ ከሰውነት ጋር ተያያዥነት   ያላቸው መብቶች  በተለያየ መንገድ  ክልከላና ጥበቃ  ተደርጉላቸዋል፡፡  አንድ  ሰው  የሌላን  ሰው  ሰውነት  ያለተነኪው  ፈቃድ  መንካት  አይችልም፡፡  ቢነካ ተጠያቂ ይሆናል፡፡  እንዲሁም በሌላ ሰው ሰውነት ላይ ጥቃት መፈፀም አይችልም፡፡  ከላይ ማንም ሰው  ከቦታ ቦታ  መዘዋወር ሕገ መንግስታዊ መብቱ  እንደሆነ ተመልክተናል፡፡  ከሕግ  አግባባ ውጨ አንድ ሰው የሌላውን  ሰው  የመዘዋወር  ነፃነት  ቢገደብ ገዳቢው  ተጠያቂነት አለበት  እንዲሁም  አንድ ሰው ስብዕናውና መልካም ስሙ  ያለመነካት መብት አለው፡፡  ስብእናው  እና መልካም ስሙ  ሲነካ ይህን  ፈፃሚውን  በስም  ማጥፋት /defamation/ ሊጠይቀው ይችላል፡፡

 

የንብረት እና  የምጣኔ ሀብት መብቶች

 

ይህ መብት  በሌላ ሰው  ይዞታ ላይ ሁከት መፍጠርን፣ተንቀሳቃሽ  የሆነ  ንብረትን  ያለ አግባብ  መያዝን  ያካትታሉ፡፡  እንዲሁም ሕገ ወጥ የሆኑ የንግድ  ተግባራትን  / Un law ful business practice/ እዚሁ ክፍል ስር  ይመደባሉ፡፡  ለምሳሌ ሕገ ወጥ የሆነ  የንግድ  ውድድር /Unfair competition/ እንደ ማለት ነው፡፡

  

የአእምሮ  ሁኔታ ከውል ውጨ  በሚደረስ  አላፊነት  ስር  /The  Mental  Element In  Tort/

   

ከውል ውጪ ኃላፊነት  ምንጨች ሶስት ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ጥፋት ነው፡፡  ሁለተኛው  በይዞታ ስር ወይም የራስ የሆነ ንብረት ወይም አንድ ሰው  ከሚያከናውነው ምጣኔ  ሐብታዊ እንቅስቅሴ  የሚመነጭ በእንግሊዝኛው  /Strict liability/ የምንለው  ነው፡፡  ሶስተኛ  ደግሞ  ለሌሎች ተጠያቂ ከመሆን የሚመነጭ ኃላፊነት ነው፡፡  በእንግሊዝኛው /Vicarious liability/ የምንለው ነው፡፡ ከሶስቱ አላፊነቶች /the mental element/  አስፈላጊ  የሚሆነው በጥፋት ላይ ለተመሠረተ ብቻ ነው፡፡ ለተቀሩት  ሁለቱ  የአእምሮ  ሁኔታን ማስረዳት አስፈላጊ አይሆንም፡፡

 

 በጥፋት ላይ የተመሠረተ አላፊነት ታሪክ እንደሚያስረዳው ይህ ተጠያቂነት /Develop/  የተደረገው   አዳጊ ኢንዱስትሪዎችን ለማገዝ  ሰዎች  የእነዚህን ኢንዱስትሪ ባለቤቶች  ለደረሰው ጉዳት  አላፊ ለማድረግ ጥፋትን ማስርዳት የግድ  እንዲል ሆነ፡፡ በተጨማሪም  ጥፋተኞች  እንዲቀጡ  የግድ አስፈላጊ ሆነ፡፡ በእነዚህ ሁለት  ምክንያቶች  በጥፋት ላይ የተመሠረተ አላስፈላጊ ተቃውሞ  በሌላ  በኩል ደግሞ  አንድን  ባለ ኢንዲስትሪ  ተጠያቂ ለማድረግ  ጥፋትን  ማስረዳት የግድ  ማለቱ  በኢንዱስትሪ ውስጥ  የሚሰሩ  ሠራተኞች  በሥራ ላይ ጉዳት ሲደርስባው  ካሣ  እንዳይከፈላቸው አደረገ፡፡  ለዚህ ደግሞ ጥፋትን ማረጋገጥ ሳያስፈልግ  አላፊነት እንዲኖር ተደረገ፡፡ ይህም /Strict liability / የሚባለው ነው፡፡ አሁን /State of mind/  ዓይነቶችን እንመለከታለን፡፡  ከውል ውጨ ላለ አላፊነት ሁለት  ዓይነት /State of mind/  አሉ እነሱም  /intention and negligence ናቸው፡፡

 

 Intention

  

Intention/ አንድ ነገር  ሆነ ብሎ አስቦ ማድረግ /አለማድረግ/ ነው፡፡ ይህን  Intention  ቀጥሎ  ባለው  ሁኔታ ማየት እንችላለን፡፡

 

የመጀመሪያው አንድ  ሰው  በሕግ  የተከለከለን ውጤት   ለማምጣት ፍላጉት ሲኖረውና  ውጤቱ ምንም  ይሁን ምን ይህንኑ  ውጤት /For see/ ሲያደርግ  ማለት ነው፡፡  ስለሆነም  በዚህ ሥር  ሶስት  መሟላት ያለባቸው  ነጥቦች አሉ ለማለት ነው፡፡  የመጀመሪያው  ውጤቱ  በሕግ የተከለከለ መሆን አለበት ሁለተኛ ይህን  ውጤት ለማምጣት  ፍላጉት መኖር አለበት ሶስተኛ ውጤቱን አስቀድሞ ማየት መቻል / for see it/ አለበት፡፡ 

  

Negligence

 

 Negligence  ብዙ ትርጉሞች ሊኖሩት ይችላሉ ፡፡  አንዱ  /Careless behavior/ የምንለው ነው፡፡  በዚህ ስር  ፍ/ቤት ግንዛቤ  የሚወሰደው የአድራጊውን ድርጊት /Conduct/ ነው፡፡ ለአንድ ሰው የሌሎች ሰዎች  ደህንነት  ምንም ቁም  ላይሰጠው  ይችላል፡፡  ሆኖም ምንም ጉዳት እስካላደረሰ  ድረስ ተጠያቂ ላይሆን ይችላል፡፡  በሌላ በኩል ደግሞ ሌሎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ  የተቻለውን  ያህል ጥረት አድርጉም /ጉደቱ ቢደርስ ተጠያቂ  ይሆናል፡፡  እዚህጋ መመዘኛው  ነባራዊ መመዘኛ  / Objective Standard/ የምንለው ነው፡፡  ፍ/ቤቱ  በዚሁ ሁኔታ  ስር አንድ / reasonable  man  / የተጠያቂው  ቦታ ላይ  ቢሆን  ኖሮ  የሚያደርገውን ነው  እግምት ውስጥ የሚከተው፡፡  ስለሆነም የእያንዳንዱ ግለሰብ አለመቻል አይደለም እግምት ውስጥ የሚገባው፡፡

  

ይህን  በምሳሌ  እናስረዳ፡፡  ለይኩን  ለማጅ  አሽከርካሪ ነው እንበል፡፡ መምህሩ  ደግሞ  ደርበው ይባላል እንበል፡፡  ለይኩን  በልምምድ ላይ አያለ በቸልተኝነት  ደርበው ላይ ጉዳት ቢያደርስ ለይኩን ላደረሰው  ጉዳት  ተጠያቂ ይሆናል፡፡  ለይኩን የሚመዘነው  በለማጅነቱ  ሳይሆን  ብቃት ባለው በአማካይ አሽከርካሪ /Average Competent Driver/ ሚዛን ነው፡፡

 

Read Next

  • Annual Leave in Ethiopia: Your Rights Under Labour Proclamation 1156/2019
    14.May
  • Ethiopia's Forex Bureau Requirements
    Ethiopia's Forex Bureau Requirements
    28.Aug
  • Administrative Law (30)
  • African Human Rights Law (18)
  • African Union Law (6)
  • Alternative Dispute Resolution (33)
  • Agency (6)
  • Bankruptcy Law (4)
  • Civil Procedure (12)
  • Conflict Laws (3)
  • Constitutional Law (5)
  • Construction Law (3)
  • Contract Law (7)
  • Criminal Law (10)
  • Criminal Procedure (6)
  • Criminology (4)
  • Customary Law (4)
  • Employment and Labor Law (17)
  • Environmental Law (5)
  • Evidence Law (6)
  • Family Law (5)
  • Gender and the law (4)
  • Human Right Law (5)
  • Humanitarian Law (7)
  • Insurance, Banking and Negotiable Instrument Law (6)
  • Intellectual Property Law (4)
  • International Organizations (4)
  • Introduction to law and Law of Persons (4)
  • Investment Law (10)
  • Islamic Law (2)
  • Judgment writing (0)
  • Jurisprudence (1)
  • Land Law (10)
  • Law and Development (0)
  • Legal History (0)
  • Legal Profession (0)
  • Legal Research Methods (0)
  • Legal Writing (0)
  • Legislative Drafting (0)
  • Maritime Law (3)
  • Non-Contractual Liability (Tort Law) (10)
  • Pre-Trial Skills and Trial Advocacy (0)
  • Property Law (27)
  • Public Enterprises and Cooperatives (0)
  • Public International Law (0)
  • Refugee Law (0)
  • Sales and Security Devices (0)
  • Sentencing and Execution (4)
  • Succession Law (6)
  • Taxation Law (4)
  • Trade and Business Organizations (2)
  • Administrative Contract (16)
  • Federalism (3)
Copyright © 2025 Abyssinia Law | Making Law Accessible! . All Rights Reserved.
Maintained by Liku Worku Legal Services!
Learn More ×