- Details
- Category: የንግድ ችሎት ውሳኔዎች
- Abyssinia Law | Making Law Accessible! By
- Hits: 3997
መ/ቁ 179485
ጥቅምት 11 ቀን 2011 ዓ/ም
ዳኛ፡- አሸናፊ ለሜቻ
ከሳሽ፡- ወ/ሪት እቴነሽ ፀጋዬ ወልዴ ፡- ቀረቡ
ተከሳሽ፡- አቶ ሳሙኤል መንግስቴ ጠበቃ ራሄል ነቃጥበብ ቀረቡ
መዝገቡ ለዛሬ የተቀጠረዉ ለምርመራ ተብሎ ሲሆን ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡
ፍርድ
በዚህ መዝገብ በግራ ቀኙ መካከል የነበረዉን ክርክር ፍርድ ቤቱ ተመልክቶ የካቲት 12 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት ዉሳኔ የሰጠ ቢሆንም ተከሳሽ በሌለሁበት የተሰጠዉ ዉሳኔ ተነስቶ ክርክሩ በድጋሚ ይሰማ በማለት መጋቢት 11 ቀን 2011 ዓ/ም በተጻፈ በቃለ መሕላ የተደገፈ አቤቱታ አቅርበዉ ያቀረቡት አቤቱታ ላይም ከሳሽ አስተያዬት እንዲሰጡ ተደርጎ ፍርድ ቤቱም ተከሳሽ በሌለሁበት የተሰጠዉ ዉሳኔ ይነሳልኝ በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ መርምሮ የፍርድ ቤቱ መጥሪያ ለተከሳሽ በህጉ አግባብ ያልደረሳቸዉ መሆኑን ስለተገነዘበ ቀደም ሲል በዚህ መዝገብ የተሰጠዉ ዉሳኔ እንዲነሳ ሰኔ 10 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ከሳሽ ህዳር 21 ቀን 2011 ዓ/ም በተጻፈ ያቀረቡት የክስ አቤቱታ ሲሆን ይዘቱም ተከሳሽ በወኪላቸዉ አማካኝነት ጥር 5 ቀን 2011 ዓ/ም በተጻፈ የብድር ውል ብር 150,000.00(አንድ መቶ ሃመሳ ሺህ) የተበደሩ መሆኑን ተከሳሽ ለዚህ ለተበደሩት ገንዘብ አከፋፈል ዋስትና ይሆን ዘንድ በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 09/10 የብሎክ ቁጥር B6 የቤት ቁጥር B6/25 የካርታ ቁጥሩ 007/10199/00/10232 የሆነ ኮንዶሚኒዬም ቤት ያስያዙ መሆኑን ተከሳሽ ከከሳሽ በብድር የወሰዱትንም የገንዘብ መጠን በ6 ወር ዉስጥ ማለትም እስከ ሐምሌ 5 ቀን 2010 ዓ/ም ለመከፈል ግዴታ የገቡ መሆኑን ይሁን እንጂ ተከሳሽ በብድር ዉሉ ላይ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ የተበደሩትን ገንዘብ ያልከፈሉ መሆኑን ለመከፈልም ፈቃደኛ አለመሆናቸዉን ገልጸዉ ተከሳሽ በብድር የወሰዱትን ብር 150,000.00(አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) ከሐምሌ 5 ቀን 2010 ዓ/ም ጀምሮ ከሚታስብ ህጋዊ ወለድ ጋር እንዲከፍሏቸዉ እንዲወሰንላቸዉ እንዲሁም በዚህ ክስ ምክንያት የደረሰባቸዉ ወጪና ኪሳራ እንዲተካላቸዉ ዳኝነት ጠይቋል፡፡
ተከሳሽ የቀረበባቸዉን ክስ እንዲከላከሉ እንዲፈቀድላቸዉ የመከላከያ ማስፈቀጃ አቅርበዉ ፍርድ ቤቱም በከሳሽ የቀረበባቸዉን ክስ እንዲከላከሉ ፈቅዶላቸዉ ሐምሌ 8 ቀን 2011 ዓ/ም የተጻፈ የመከላከያ መልስ አቅርቧል፤ባቀረቡት መከላከያ መልስም ከሳሽ በማስረጃነት ባቀረቡት የብድር ውል በራሳቸዉም ሆነ በወኪላቸዉ አማካኝነት ያልተዋዋሉ መሆኑን ገንዘብ ተበዳሪም ሆነ ተዋዋይ አለመሆናቸዉን በብድር ዉሉ ላይ የተጠቀሰዉንም ገንዘብ ተበድረዉ ያልወሰዱ መሆኑን በማስረጃነት የቀረበዉ የውክልና ስልጣን ማስረጃም በእራሳቸዉ ያልተሰጠ መሆኑን በብድር ዉሉ ላይ ወ/ሮ ነጻነት መንግስቱ የወ/ሮ ላቀች ተክሉ ህጋዊ ወኪል የሚል መሆኑን ብድሩን የተበደሩት እርሳቸዉን ወክለዉ የተበደሩ ስለመሆናቸዉ የሚያመልክተዉ ነገር የሌለ መሆኑን በዉሉ ላይ ወ/ሮ ነጻነተ መንግሰቱ ብድሩን የተበደሩት ለስራ ማስኬጃ እንደሆነ የብድር ውሉ የሚያመለክት ስለሆነ በብድር ዉሉ ላይ ለተገለጸዉ የገንዘብ መጠን ወ/ሮ ነጻነት መንግስቱ በግላቸዉ ከሚጠየቁ በቀር ኃላፊ የሚሆኑበት የህግ አግባብ የሌለ መሆኑን ገልጸዉ ከሳሽ ያቀረቡት ክስ ውድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት የመከላከያ መልሳቸዉን አቅርቧል፡፡
ፍርድ ቤቱ ሐምሌ 19 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት ክስ የሰማ ሲሆን በዚህም መሰረት ከሳሽ ባቀረቡት ክርክር ወ/ሮ ላቀች ተክሌ ለወ/ሪት ነጻት ውክልና የሰጡት አንድ ተከሳሽ ሆነዉ እንዲሰሩ መሆኑን ወ/ሮ ላቀች ከተከሳሽ የተሰጠ የውክልና ስልጣን ያላቸዉ መሆኑን ተከሳሽ ለወ/ሮ ላቀች በሰጡት ውክልና ወ/ሮ ላቀች ሌላ ሰዉ እንዲወክሉ ስልጣን የሰጧቸዉ መሆኑን ወ/ሮ ነጻነትም በወ/ሮ ላቀች በተሰጣቸዉ ውክልና መሰረት ተከሳሽን ወክለዉ በብድር ውሉ ላይ የተጠቀሰዉን ገንዘብ የተበደሩ መሆኑን በመግልጽ ሲከራከሩ ተከሳሽ በበኩላቸዉ ባቀረቡት ክርክር ወ/ሮ ነጻነት ብድሩን የተበደሩት ወ/ሮ ላቀችን ወክለዉ መሆኑን በብድር ውሉ ላይም ስማቸዉ ያልተጠቀሰ መሆኑን ገንዘቡን ያልተበደሩ መሆኑን በብድር ውሉ ላይ ተዋዋይ ወገን አለመሆናቸዉን ገልጸዉ ክርክራቸዉን አቅርቧል፡፡
የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተዉን ሲመስል ፍርድ ቤቱም ተከሳሽ በብድር ውሉ ላይ የተጠቀሰዉን የገንዘብ መጠን ለከሳሽ ሊከፍሉ ይገባል ወይስ አይገባም የሚለዉን ነጥብ እንደሚከተወሉ መርምሮታል፡፡
እንደመረመረዉም ውሎች ዉጤት ያላቸዉ በተዋዋሏቸዉ ወገኖች መካካል መሆኑን የፍ/ሕ/ቁ 1952(1) ስር ተደነግጓል፡፡ ይሁን እንጂ ሰዎች ህጋዊ ዉጤት ያላቸዉን ትግባራት እራሳቸዉ በቅጥታ ሊያከናዉኗቸዉ ግድ አይደለም ይልቁንም በወኪሎቻቸዉ አማካኝነት ሊያከናውኑ እንደሚችሉ ከፍ/ሕ/ቁ 2179 ጀምሮ ካሉት ድንጋጌዎች መረዳት ይቻላል፡፡
የሌላ ሰዉ ወኪል በመሆን ስራዎችን የመፈጸም ስልጣን ከህግ ወይም ከውል ሊመነጭ እንደሚችል የፍ/ሕ/ቁ 2179 ይደነግጋል፡፡ ውክልና ማለት ተወካይ የተባለ አንድ ሰዉ ወካይ ለተባለዉ እንደራሴ ሆኖ አንድ ወይም ብዙ ህጋዊ ስራዎች በወካዩ ስም ለማከናወን ግዴታ የሚገባባት ውል መሆኑን ውክላናም በግልጽ ወይም በዝምታ ሊሰጥ የሚችል መሆኑን ፤ተወካዩ የተሰጠዉ የውክልና ስልጣን የሚፈቀድ ከሆነ ተወካዩ በራሱ ምትክ ሌላ ሰዉ ስራዉን እንዲሰራ መተካት የሚችል መሆኑን (delegation of authority) በዚህ መልኩ በምትክ ወኪል የተሰራ ስራም ወካዩን ሊያስገድድ የሚችል መሆኑን ከፍ/ሕ/ቁ 2199፤2200፤2215 እና 2217 መራዳት ይቻላል፡፡
ወደ ተያዘዉ ጉዳይ ሰንመለስ ተከሳሽ የሚከራከሩት በብድር ዉሉ ላይ ስሜ አልተጠቀስም በማስረጃነት የቀረበዉን ውክልና እኔ አልሰጠሁም ወ/ሮ ነጻነት መንግስቱ ብድሩን የወሰደቺዉ ለስራ ማስኬጃ ስለሆነ ኃላፊነት የለብኝም ወ/ሮ ነጻነተ መንግስቱ የወ/ሮ ላቀች ህጋዊ ወኪል ናቸዉ እንጂ የተከሳሽ ወኪል አይደሉም በማለት ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ ተከሳሽ ለወ/ሮ ላቀች የሰጡት ውክልና የሌለ መሆኑን በመግለጽ ያቀረቡት ክርክር የለም ይልቁንም ወ/ሮ ላቀች ተክሌ ከተከሳሽ በቁጥር 20001/10/2000 በቀን 26/5/2000 ዓ/ም የተሰጣቸዉ የውክልና ስልጣን ያላቸዉ መሆኑን የቀረበዉ ማስረጃ ያስረዳል፤ለክርክሩ መነሻ ከሆነዉ የብድር ውል ለመመልከት እንደሚቻለዉ ወ/ሮ ነጻነት መንግስቱ በብድር ዉሉ ላይ የተጠቀሰዉን ገንዘብ የተበደሩት ከወ/ሮ ላቀች ተክሉ በቁጥር ቅ8/15969/1/08 በቀን 9/6/08 ዓ/ም የተሰጣቸዉን ውክላና መሰረት በማድረግ ነዉ በዚህ ውክልናም ወ/ሮ ነጻነት መንግስቴ እንድ አቶ ሳሙኤል መንግሰቱ ሆነዉ ከግለሰብ ብድር እንዲበደሩ የተከሳሽ ወኪል ከሆኑት ከወ/ሮ ላቀች ተክሉ የውክልና ስልጣን ተሰጥቷቸዋል ወ/ሮ ላቀች ተክሉ በተከሳሽ በተሰጣቸዉ የውክልና ስልጣን ተተኪ ወኪል እንዳይውክሉ የተከለከሉ መሆኑን በመግለጽ በተከሳሽ በኩል የቀረበ ክርክር የለም ይህ ከሆነ ደግሞ በፍ/ሕ/ቁ 2217(1) ስር በግልጽ እንደተደነገገዉ ወ/ሮ ነጻነት መንግሰቱ የተከሳሽ ወኪል በሆኑት በወ/ሮ ላቀች ትክሉ በተሰጣቸዉ የውክልና ስልጣን የብድሩን ዉሉን የፈጸሙ መሆኑን መረዳት የሚቻል በመሆኑ ተከሳሽ በብደር ዉሉ ይገደዳሉ፡፡ በመሆኑም ተከሳሽ በብድር ዉሉ ላይ የተገለጸዉን ብር 150,000.00( አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) ለከሳሽ የመከፈል ሃላፊነት አለበቸዉ በማለት ፍርድ ቤቱ ፍርድ ሰጥቷል፡፡
ዉሳኔ
- ተከሳሽ ብር 150,000.00(አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) ገንዘቡ መከፈል ከነበረበት ከሐምሌ 5 ቀን 2010 ዓ/ም ጀምሮ ከሚታስብ 9% ወልድ ጋር ለተካሳሽ ይክፈሉ፡፡
- ወጪና ኪሳራ ከሳሽ ለዳኝነት የከፈሉትን ብር 4,100፤ለቴምብር ቀረጥ ብር 15 እንዲሁም ለልዩ ልዩ ወጪዎች በቁርጥ ብር 6,000 ተከሳሽ ለከሳሽ ይክፈሉ፡፡
ትዕዛዝ
ይግባኝ ለጠየቀ ግልባጭ ይሰጥ፡፡
መዝገቡ ተዝግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
- Details
- Category: የንግድ ችሎት ውሳኔዎች
- Abyssinia Law | Making Law Accessible! By
- Hits: 4031
መ/ቁ 179287
ጥቅምት 24 ቀን 2012 ዓ/ም
ዳኛ፡- አሸናፊ ለሜቻ
ከሳሽ፡- አቶ ዳንኤል አበጀ ተካልኝ ጠበቃ ብሩክ ደረጀ፡ ቀረቡ
ተከሳሾች፡- 1ኛ) አቶ አዳነ ደርብ ማሙዬ፡- አልቀረቡም
2ኛ) ኤም ኤ ፕሪንቲንግ እና አድቨርታይዚንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፡- ም/ስራ አስኪያጅ መልካሙ በላቸዉ ፡- ቀረቡ
መዝገቡ ለዛሬ የተቀጠረዉ ለምርመራ ተብሎ ሲሆን ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡
ፍርድ
ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነዉ ከሳሽ ሕዳር 12 ቀን 2011 ዓ/ም በተጻፈ ያቀረቡት የክስ አቤቱታ ሲሆን ይዘቱም ከሳሽ የመኪና አስመጪነት ስራ ላይ የተሰማራ መሆኑን የ2ኛ ተከሳሽ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ መኪና እንዲመጣለት ባዘዘዉ መሰረት በሰሌዳ ቁጥር 2ኤ96731 የሚታወቀዉን እና በ1ኛ ተከሳሽ ስም የተመዘገበዉን ቶዮታ ያሪስ ተሽከርካሪ ያስመጡላቸዉ መሆኑን 1ኛ ተከሳሽም ቀሪ ክፍያ መክፈያ እንዲሆን በ2ኛ ተከሳሽ ስም የተመዘገበ ብር 175,000.00( አንድ መቶ ሰባ አምስት ሺህ) የያዘ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚመነዘር ቼክ የሰጧዋቸዉ መሆኑን ይሁን እንጂ ቼኩን ለክፍያ ለባንኩ ባቀረቡ ጊዜ የ2ኛ ተከሳሽ ሂሳብ በቂ ስንቅ የለዉም በሚል ቼኩ ተመላሽ የተደረገላቸዉ መሆኑን ገልጸዉ ተከሳሾች ብር 175,000.00(አንድ መቶ ሰባ አምስት ሺህ) በእንድነት እና በነጠላ እንዲከፈላቸዉ እንዲወሰንላቸዉ እንዲሁም በዚህ ክስ ምክንያት የደረሰባቸዉ ወጪና ኪሳራ እንዲተካላቸዉ ዳኝነት ጠይቋል፡፡
ከሳሽ ክሱን ያስረዱልኛል ያሉትን የሰነድ ማስረጃዎች አቅርቧል የሰዉ ምስክሮች ቆጥሯል፡፡
ከሳሽ ያቀረቡት የክስ አቤታታ ከነ አባሪዎቹ ለተከሳሾች ድርሶ የበኩላቸዉን መከላከያ እንዲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ 1ኛ ተከሳሽ የፍርድ ቤቱ መጥሪያ የደረሳቸዉ ቢሆንም ያቀረቡት የመከላከያ ማስፈቀጃ ባለመኖሩ ታህሳስ 24 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት የመከላከል መብታቸዉን ፍርድ ቤቱ ያለፈ ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ በበኩላቸዉ በቀን 25/4/2011 ዓ/ም የተጻፈ የመከላከያ ማስፈቀጃ አቅርበዉ ፍርድ ቤቱም የቀረበባቸዉን ክስ እንዲከላከሉ ፈቅዶ ጥር 14 ቀን 2011 ዓ/ም በተጻፈ የመከላከያ መልሳቸዉን ያቀረቡ ሲሆን ይዘቱም 1ኛ ተከሳሽ ለብቻዉ በ2ኛ ተከሳሽ ላይ ኃላፊነት የሚያስከትል ተግባራትን ለማከናወን ስልጣን ያልተሰጠዉ መሆኑን 1ኛ ተከሳሽ ስልጣን እንደሌለዉ እያወቀ እንዲሁም ከሳሽ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቼክ የ2ኛ ተከሳሽ መሆኑን እያወቀ ቼኩን መቀበሉ በገዛ ፈቃዱ ሃላፊነት የወሰዱ መሆኑን የሚያስረዳ መሆኑን በከሳሽ እና በ1ኛ ተከሳሽ መካከል ያለዉ ግኑኘነት የመኪና ሽያጭ ውል መሆኑን የመኪናዉ ሽያጭ ውልም በመካከላቸዉ የተቋቋመ በመሆኑ 2ኛ ተከሳሽንም ወደዚህ ያስገቡት ሆን ብሎ ሃላፊነትን ለማሰከተል ስለሆነ ከሳሽ የመኪና ሽያጭ ዉሉን መሰረት አድርገዉ 1ኛ ተከሳሽ ከሚጠይቁ በቀር ቼኩን መሰረት አድርገዉ ዳኝነት ሊጠይቁ የማይገባ መሆኑን በ2ኛ ተከሳሽ ማህበር መተዳደሪያ ደንብ እና መመሰረቻ ጽሁፍ መሰረት የ2ኛ ተከሳሽ ስራ ሊከናወን የሚችለዉ በ1ኛ ተከሳሽ እና በ2ኛ ተከሳሽ ምክትል ስራ አስኪያጅ በሆኑት በአቶ መልካሙ በላቸዉ ጣምራ ዉሳኔ መሆኑ እየታወቀ 1ኛ ተከሳሽ ለብቻቸዉ ከስልጠናቸዉ ወጭ ለሰጡት ቼክ 2ኛ ተከሳሽ ሃላፊነት የሌለባቸዉ መሆኑን በመግለጽ የመከላከያ መልሳቸዉን አቅርቧል፡፡
ፍርድ ቤቱ ሰኔ 12 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት ክስ የሰማ ሲሆን በዚህም መሰረት ከሳሽ ባቀረቡት ክርክር ቼኩን የሰጠዉ ባንክ አስፈላጊዉ ፎርማሊቲ ባይሟላ የ2ኛ ተከሳሽን ሂሳብ የማይከፍት መሆኑን የ2ኛ ተከሳሽ ስራ አስኪያጅ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቼክ ለብቻዉ መፈረም የሚችል መሆኑን ቀደም ሲል የነበረዉ መመስረቻ ጽሁፍ በቃለ ጉባኤ የተሻሻለ መሆኑን ከሳሽ ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር የፈጸመዉ የመኪና ሽያጭ ውል በጽሁፍ የተደረገ ሳይሆን በቃል የተደረገ መሆኑን 1ኛ ተከሳሽ ቀደም ሲል ክፍያ የፈጸመዉ በ2ኛ ተከሳሽ ቼክ መሆኑን
1ኛ ተከሳሽ ውል የተዋዋለዉ በ2ኛ ተከሳሽ ስም መሆኑን ግምት ሊወስድ የሚገባ መሆኑን 1ኛ ተከሳሽ መኪናዉ ወደ ሀገር ዉስጥ ከገባ በኃላ ስመ ሀብቱን በስሙ ያዞረ መሆኑን ይሁን እንጂ ይህ የ1ኛ ተከሳሽ ተግባር የ2ኛ ተከሳሽ ሃላፊነትን የማያስቀር መሆኑን በመግለጽ ሲከራከሩ 2ኛ ተከሳሽ በበኩላቸዉ ባቀረቡት ክርክር ስለመኪናዉ የሚያውቁት ነገር የሌለ መሆኑን ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቼክ በ2ኛ ተከሳሽ ሃላፊነት የሚያስከትል አለመሆኑን ቼኩንም 1ኛ ተከሳሽ ለግል ጥቅሙ ያዋለዉ መሆኑን ለድርጅቱ ጥቅም ቢሆን 1ኛ ተከሳሽ በድርጅቱ ስም የሚዋዋል መሆኑን በመግለጽ ክርክራቸዉን አቅርቧል፡፡
የግራ ቀኙ ጠቅላላ ክርክር ከላይ የተመለከተዉን ሲመሰል ፍርድ ቤቱም ተከሳሾች በእንደነት እና በነጠላ በክሱ ላይ የተመለከተዉን የገንዘብ መጠን ለከሳሽ ሊከፍሉ ይገባል ወይስ አይገባም የሚለዉን ነጥብ እንደሚከተለዉ መርምሯል፡፡
እንደመረመረዉም ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቼክ በ1ኛ ተከሳሽ የተፈረመ መሆኑን 1ኛ ተከሳሽ የ2ኛ ተከሳሽ ስራ አስኪያጅ መሆኑን ከሳሽ እና 1ኛ ተከሳሽ የመኪና ሽያጭ ውል የፈጸሙ መሆኑን በመኪና ሽያጭ ዉሉም ላይ የተገለጸቺዉ ተሽከርካሪም በ1ኛ ተከሳሽ ስም ተመዝገባ የምትገኝ መሆኑ ከግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃዎች መረጋገጥ የተቻሉ ፍሬ ነገሮች ናቸዉ፡፡
1ኛ ተከሳሽ የፍርድ ቤቱ መጥሪያ ደረሶት ያቀረበዉ መከላከያ የለም፡፡በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 285(2) በመጥሪያዉ ላይ በተወሰነዉ ጊዜ ዉስጥ ተከሳሽ ቀርቦ መከላከያ ለማቅርብ እንዲፈቀድለት ለፍርድ በቱ ያላመለከተ እንደሆነ ከሳሽ የጠየቀዉ ገንዘብ ከነ ወለዱ እንዲከፍል ፍርድ ሊሰጥ እንደሚገባ ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም 1ኛ ተከሳሽ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ሊከፍል ይገባል ተብሎ ተወስኗል፡፡
2ኛ ተከሳሽን በተመለከተ በንግድ ህጉ አንቀጽ 35 እንደተመለከተዉ ከሶስተኛ ወገኖች ጋራ በሚያገናኙት ጉዳዮች ሁሉ ስልጣን ያለዉ ስራ አስኪያጅ ከነጋዴዉ ስራ ጋራ ነክነት ያላቸዉን ማናቸዉንም ግዴታዎች ለመፈረምና የሚተላላፉ የንግድ ሰነዶችን ጭምር ለመፈረም ሙሉ ስልጣን እንዳለዉ ሆኖ የሚቆጠር መሆኑ ተመልከተዋል፡፡ ከዚህ ድንጋጌ መረዳት የሚቻለዉ
የአንድ ማህበር ስራ አስኪያጅ በማህበር ህጋዊ ዉጤት ያለዉ ተግባር ለመፈጸም እና ማህበሩም በስራ አስኪያጁ ተግባር ሊገደድ የሚገባዉ ስራ አስኪያጁ ያከናወነዉ ተግባር ከማህበሩ የንግድ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የፈጸመዉ ተግባር እንደሆነ መሆኑን እንዲሁም ከማህበሩ የንግድ እንቅሰቃሴ ጋር የማይገናኝ ከሆነ ስራ አስኪያጁ በማህበሩ ላይ ግዴታ ሊያስከትል የሚችል ተግባር ሊፈጽም እንደማይችል መገንዘብ አያዳግትም፡፡ ወደ ተያዘዉ ጉዳይ ስንመለስ ከሳሽ በክስ አቤቱታዉ ላይ በግልጽ የማለከተዉ ከ1ኛ ተከሳሸ ጋር የመኪና ሽያጭ የፈጸመ መሆኑን በከፊል ከፍያም የፈጸመለት1ኛ ተከሳሽ መሆኑን የቀረበዉ ክስ ይዘት ያስረዳል ከዚህም መረዳት የሚቻለዉ ከሳሽ ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር የፈጸመዉ የመኪና ሽያጭ ውል ከ2ኛ ተከሳሽ ጋር የንግድ ስራ ጋር የሚገናኝ አይደለም በዚህ መልኩ ከሳሽ ያቀረበዉም ክርክር የለም፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ 1ኛ ተከሳሽ በንግድ ህጉ አንቀጽ 35(1) መሰረት 2ኛ ተከሳሽን ሊያስገድድ የሚችል ህጋዊ ተግባር ያልፈጸመ መሆኑን መረዳት የሚቻል ከመሆኑም በላይ 1ኛ ተከሳሽ ከከሳሽ ጋር የመኪና ሽያጭ ዉሉን የፈጸመዉ ለግሉ ጥቅም መሆኑን ተሽከርካሪዉ በአሁኑ ጊዜም በ1ኛ ተከሳሽ ስም ተመዝገቦ የሚገኝ መሆኑ አስረጂ ነዉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 8 መሰረት ቼክን የመሰሉ የሚተላላፉ ሰነዶች ለሶስተኛ ወገን ሊሰጡ የሚችሉት በ1ኛ ተከሳሽ እና በ2ኛ ተከሳሽ ምክትል ስራ አስኪጅ የጋራ ፊርማ መሆኑን የሚያመለክት ሲሆን 1ኛ ተከሳሽ በ2ኛ ተከሳሽ ማህበር መተዳደሪያ ደንብ ከተሰጠዉ ስልጣን በማለፍ ቼክ ፈርሞ ለከሳሽ መስጠቱ ጥፋት የፈጸመ መሆኑን የሚያስረዳ ሲሆን ስራ አስኪያጅ ሙሉ ስልጣን ያለዉ እና በማህበሩ ላይ ህጋዊ ዉጤት ሊያሰከትል የሚችል ተግባር ሊፈጽም የሚችለዉ የማህበሩን አላማ ለማሳካት ብቻ እንጂ የግል ጥቅሙን በአሰቀደመ ጊዜ አለመሆኑን የንግድ ህጉ አንቀጽ 528 ያስረዳል፡፡
ከሳሽ ባቀረቡት ክርክር 1ኛ ተከሳሽ የመኪና ሽያጭ ውል የፈጸመዉ ለ2ኛ ተከሳሽ ማህበር ጥቅም ብሎም የማህበሩ ዓለማ ከግብ ለማድረስ ስለመሆኑ ያቀረቡት ክርክር የለም የማህበር ስራ አስኪያጅ ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ተግባራት ወጪ ሌሎች ህገወጥ ተግባራትን የፈጸመ እንደሆነ ደግሞ በንግድ ህጉ አንቀጽ 530 መሰረት ሶስተኛ ወገኖች ላይ ለደረሰ ጉዳት ሃላፊነት
ያለባቸዉ መሆኑ የተመለከተ ስለሆነ በቼኩ ላይ ለተመለከተዉ የገንዘብ መጠን 1ኛ ተከሳሽ ሃላፊ ከሚባል በስተቀር 2ኛ ተከሳሽ ከከሳሽ ጋር ምንም አይነት ግኑኝነት ሳይኖረዉ እና ለክርክሩ መነሻ የሆነዉም ቼክ ለከሳሽ የተሰጠዉ ከእርሱ ጋር ባለ የንግድ ግኑኝነት ባለመሆኑ ፍርድ ቤቱ 2ኛ ተከሳሽ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቼክ ላይ የተገለጸዉን የገንዘብ መጠን የመክፈል ሃላፊነት የለበትም በማለት ፍርድ ሰጥቷል፡፡
ውሣኔ
- 1ኛ ተከሳሽ ብር 175,000.00(አንድ መቶ ሰባ አምስት ሺህ) ከ9/1/2011 ዓ/ም ጀምሮ ከሚታሠብ 9% ወለድ ጋር ለከሣሽ ይክፈሉ ተብሎ ተወስኗል፡፡
- 1ኛ ተከሳሽ ከሳሽ ለዳኝነት የከፈለዉን ብር 4,475፤ለቴምብር ቀረጥ የተከፈለዉን ብር 25 እንዲሁም ለጠበቃ አበል ብር 17,000 እንዲከፍል ተወስኗል፡፡
ትዕዛዝ
ይግባኝ ለጠየቀ ግልባጭ ይሰጥ ፡፡
መዝገቡ ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
- Details
- Category: የንግድ ችሎት ውሳኔዎች
- Abyssinia Law | Making Law Accessible! By
- Hits: 4796
የኮ/መ/ቁ፡- 179280
ቀን፡- 30/04/2012
ዳኛ፡ አሸናፊ ለሜቻ
ከሳሾች፡- 1ኛ) ዶ/ር ጌተሁን ይትባረክ ከጠበቃ ኢሳያስ ከልሌ፡- ቀረቡ
2ኛ) ሲሣይ አበበ
ተከሳሾች፡- 1ኛ) ዶ/ር አከዛ ጠዓመ፡- ጠበቃ ግርማ ሀይሌ፡- ቀረቡ
2ኛ) ቅዱስ ያሬድ ኃ/የተ/የግል/ማህበር ፡- አልቀረቡም
መዝገቡ ለዛሬ የተቀጠረው ለምርመራ ተብሎ ሲሆን ተመርምሮ ተከታዩን ፍርድ ተሰጥቷል፡፡
ፍርድ
ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው ከሳሾች ጥቅምት12/2011ዓ.ም ያቀረቡት የክስ አቤቱታ ሲሆን ይዘቱም ከሳሾች የ2ኛ ተከሳሽ ማህበር ባለአክሲዩኖች መሆናቸዉን 1ኛተከሳሽ ከከሳሾች እውቅና ውጪ፤ያለ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ ለብቻው ቃለጉባኤ በመያዝ ከማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ እና ከሕግ ውጪ ለ2ኛ ተከሳሽ ማህበር ሥራ አስኪያጂ የሾመ መሆኑን 1ኛ ተከሳሽ ከ2ኛ ተከሳሽ ጋር ተመሳሳይ ሥራ የሚሰራ ተቋም ከባለቤታቸው ጋር ከፍተው የ2ኛ ተከሳሽን ደንበኞችና አሰራሮች ወደራሳቸው ተቋም አየወሰዱ መሆኑን፤በ2ኛ ተከሳሽ ሥም ከአምቦ እና ኢኳተርያል የህክምና ዕቃ አቅርቢዎች ወስደዉ እራሳቸዉ በመሰረቱት የህክምና ተቋም ዉስጥ የህክምና መሳሪያዎች እየተገለገሉበት የሚገኙ መሆኑን፤የ2ኛ ተከሳሽ አካል የሆነው ሴንቸሪ ፓርማሲ እንዲዘጋ በማድረግ ከዱሹስ በሚል ስም ፓርማሲ የከፈቱ መሆኑን፤የ2ኛ ተከሳሽ ማህበርን መኪና ለግል ጥቅማቸው የሚገለገሉበት መሆኑን፤ስራ ለማህበሩ ሳይሰሩ በወር ብር 159,230.09( አንድ መቶ ሀምሳ ዘጠኝ ሺ ሁለት መቶ ሰላሳ 09/100) የሚከፈላቸዉ መሆኑን በተመሳሳይ ባለቤታቸዉ ወ/ሮ ሜላት አባተ ሌላ ቦታ ሥራ እያላቸዉ ከ2ኛ ተከሳሽ ማህበር ሥራ አስኪያጅ በሚል ስም ወራዊ ደሞዝ ብር 27,615.38(ሃያ ሰባት ሺ ስድስት መቶ አስራ አምስት 38/100 )እንዲሁም ብር 5000.00( አምስት ሺ) የነዳጅ አበል እንዲከፈላቸዉ ያደረጉ መሆኑ፤የ1ኛ ተከሳሽ ወንድም የ2ኛ ተካሳሽ ሒሳብ ክፍል ኃላፊ በመሆን በወር ብር 14,690.00(አስራ አራት ሺ ስድስት መቶ ዘጠና) የሚከፈላቸዉ መሆኑን የ2ኛ ተከሳሽ ማህበር የውጭ ኦዲተር በመሆን በዓመት 162,800.00( አንድ መቶ ስልሳ ሁለትሺ ሰምንት መቶ ብር) እንዲከፈላቸዉ 1ኛ ተከሳሽ ያደረጉ መሆኑን ማህበሩ አለአግባብር 12,000,000.00( አስራ ሁለት ሚሊዮን) ግብር እንዲከፍል ያደረጉ መሆኑን በቂ እዉቀት ሳይኖረዉ የአጎታቸዉን ልጅ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ በማድረግ በወር ብር 66,258.62( ስልሳ ስድስት ሺ ሁለት መቶ ሀምሳ ስምንት 62/100) የተጋነነ ክፍያ እንዲከፈል ያደረጉ መሆኑን ከ2ኛ ተከሳሽ ማህበር ብር 2,727,030.00( ሁለት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሃያሰባት ሺ ሰላሳ) አለ አግባብ ወጪ ያደረጉ መሆኑን እንዲሁም 2ኛ ተከሳሽ የህንድ ሆስፒታል እና የኢንተርናሽል ላብራቶሪ ዕዳ ሳይኖርበት ዕዳ አለበት በማለት በድምሩ ብር 4,875,200.00( አራት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰባ አምስት ሺ ሁለት መቶ) ወጪ አድርገዉ የወሰዱ መሆኑን እንዲሁም ማህበሩ ትርፍ ቢያተርፍም የትርፍ ክፍፍል ተድርጎ የማያወቅ መሆኑን ገልጸዉ 1ኛ ተከሳሽ 01/13/2010ዓ.ም በውልና ማስረጃ ያፀደቁትን ቃለጉባኤ የከሣሾችን መብት እና ጥቅም የሚጎዳ ስለሆነ ቃለ ጉባኤዉ እንዲሻር እንዲወሰንላቸዉ፤1ኛ ተከሳሽ ከ2ኛ ተከሳሽ ማህበር ጋር ተመሳሳይ ሥራ በግል በመክፍት እየሰሩ ስለሆነ እና ማህበሩ ላይ ጉዳት እያደረሱ ስለሆነ ድርሻቸው ተከፍሏቸው ከማህበሩ እንዲወጡ እንዲወሰንላቸዉ እንዲሁም በዚህ ክስ ምክንያት የደረሰባቸዉን ወጩና ኪሳራ እንዲተከላቸዉ እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት ጠይቋል፡፡
ከሳሽ ክሱን ያስረዱልኛል ያሉዋቸውን የሠነድ ማስረጃ አያይዘው አቅርበዋል እንዲሁም የሰው ምስክር ቆጥረዋል፡፡
ከሳሾች ያቀረቡት የክስ አቤቱታ ከነ አባሪዎች ለተከሳሾች ደርሶቸው መልስ የሰጡ ሲሆን ተከሳሾች በሰጡት የመከላከያ መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የፍሬ ነገር መልስ ሰጥቷል፡፡ ተከሳሾች ያቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በተመለከተ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር በቀረበዉ መቃወሚያ ላይ ካደመጠ በኃላ ጥቅምት 20 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት በተከሳሾች የቀረበዉን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ወድቅ ያደረገዉ በመሆኑ ከዚህ ማስፈር ሳይፈልግ ታልፏል፡፡ ተከሳሾች በፍሬ ነገሩ ላይ በሰጡት መልስ 1ኛ ተከሳሽ እና 1ኛ ከሳሽ የህክምና ባለሙያዎች በመሆናቸዉ በጠቅላላ ጉባኤ ዉሳኔ መሰረት 2ኛ ተከሳሽ በየወሩ ደሞዝ ይከፈላቸው የነበር መሆኑን ነገር ግን ከሰኔ 10 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የደሞዝ ክፍያዉ እንዲቀር የተደረገ መሆኑን በተመሳሳይ ለ2ኛ ከሳሽም በኃላፊነታቸው ልክ በጉባኤው ውሳኔ መሠረት ደመዉዝ ሲከፈላቸዉ የነበረ መሆኑን ለ2ኛ ተከሳሽ ማህበር ሥራ አስኪያጅ ለመቅጠር ከሳሾች ተስማምተው መረጣ ከተካሄደ በኃላ በባለአክሲዩኖች ስብሰባ ላይ ከሣሾች እንዲገኙ ጥሪ ቢደረግም ከሳሾች ሊገኙ ያልቻሉ መሆኑን በዚህም ምክንያት የ2ኛ ተከሳሽ ማህበር የስራ አስኪያጅ ቅጥር ላይ ውሳኔ ማሳለፍ ያልተቻለ መሆኑን ለከሳሾች በተለመደው የማህበሩ የስብሰባ አጠራር በ14/10/2010 በስብሰባ እንዲገኙ በ1ኛ ተከሳሽ በደብዳቤ እና ኤሚል ጥሪ ቢደረግላቸውም ባለመገኘታቸው እና ለመገኘት እንደማይፈልጉ ለ2ተኛ ተከሳሽ በመሳወቃቸዉ 1ኛ ተከሳሽ ከ2ኛ ተከሳሽ ማህበር የህግ አማካሪ ጋር በመሆን በማህበሩ መተዳደሪ ደንብ መሠረት 2ኛ ተከሳሽ ያለ ሥራ አስኪያጅ መቆየት ስለማይገባው የተሻለ የተባለው ሰው በሥራ አስኪጂነት እንዲቀጠር የወሰኑ መሆኑን ዉሳኔዉ የተላለፈበት ቃለጉባኤም የተመዘገበ መሆኑን የ1ኛ ተከሳሽ ወንድም የ2ኛ ተከሳሽ ማህበርን ኦዲት ያልሰራ መሆኑን ነገር ግን ለማህበሩ ለሰጠዉ አግልግሎት ህጋዊ ክፍያ የተከፈለዉ መሆኑን 2ኛ ተከሳሽ በውጪ ኦዲተሮች በየጊዜው ኦዲት የሚደረግ መሆኑን የኦዲት ሪፖርትም ለባለአክሲዮች በዋቢ ሸበሌ ሆቴል በተደረገ ጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ የጸደቀ መሆኑን የማህበሩ የ2018 ኦዲት ሪፖርት እንዲሰራ ትዕዛዝ የተላለፈ መሆኑን 2ኛ ተከሰሽ 12,000,000.00( አስራ ሁለት ሚሊዮን) የግብር ዕዳ እንዲከፍል ተደርጓል የተባለው በማስረጃ ሀሰት መሆኑን 1ኛ ተከሳሽ ተፎካካሪ ድርጅት አቋቋመዋል የተባለው 2ተኛ ተካሳሾችን ለመፎካከር ተብሎ የተቋቋመ ድርጅት ስለመኖሩ የማያውቁ መሆኑን 1ኛ ተከሳሽ አቋቋሟል የተባለው ድርጅት 2ኛ ተከሳሽ ካለበት ክ/ከተማ ውጪ የሚገኝ መሆኑን 1ኛ ተካሳሽ ከህግ አግባብ ውጪ ገንዘብ ወስዷል የተባለው ሐሰት መሆኑን የ1ኛ ተከሳሽ አጎት የ2ኛ ሥራአስኪያጅ ሆነው ሰራተዋል የተባለዉ ሀሰት መሆኑን 1ኛ ተከሳሽ ትዕግስት ደጀኔ የምትባል ዘመድ የሌላቸዉ መሆኑን ከአምቦ እና ኢኳተርያል የህክምና ዕቃ አቅርቢዎች የህክምና ዕቃ ግዢ በግል ባቋቋመዉ ድርጅት እየተገለገለበት ይገኛል የተባለዉን በተመለከተ ከእነዚህ ተቋማት የተገዛ የህክምና መገልገያ የሌለ መሆኑን የአሁኑ ሥራ አስኪያጅ የደመዉዝ ክፍያ ቀድሞ ከነበሩት የሥራ አስኪያጂዎች ክፍያ በእጅጉ የሚያንስ መሆኑን አፖሎ ሆስፒታል ከ2ኛ ተከሳሽ ብር 551,000.00( አምስት መቶ ሃምሳ አንድ ሺህ)የሚፈልግ መሆኑን ይህ ዕዳ ሳይከፍል የቀረዉ በውጭ ምንዛሬ እጥረት መሆኑን 2ኛ ተከሳሽ የኢንተርናሽል ላብራቶሪ እንዲሁም የሌሎች መድሐኒት አቅራቢዎች ዕዳ ያለበት መሆኑን የትርፍ ድርሻን በተመለከተ የማህበሩ ካፒታል እንዲያድግ የተደረገበት መሆኑን ገልጸዉ የመካለከያ መልሳቸዉን አቅርበዋል፡፡
ተከሳሾች ክሱን ይከላከሉልኛል ያሏዋቸውን የሠነድ ማስረጃ አቅርቧል የሰው ምስክርም ቆጥረዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ ግንቦት 16 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት ክስ የሰማ ሲሆን በዚህም መሰረት ከሳሾች ባቀረቡት ክርክር 1ኛ ተከሳሽ ለከሳሾች የሰብሰባ ጥሪ ሳያደርጉ ለብቻቸዉ ቃለ ጉባኤ በመያዝ የማህበሩን ስራ አስኪያጅ የሾሙ መሆኑን ስራ አስኪያጅ የመሾም ስልጣን የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ መሆኑን በ1ኛ ተከሳሽ ብቻ ተይዞ የጸደቀዉ ቃለ ጉባኤ መብትና ጥቅማቸዉን የሚናካ በመሆኑ ሊሻር የሚገባዉ መሆኑን 1ኛ ተከሳሽ የማህበሩ ስራ አስፈጻሚ ሆነዉ ሳለ የራሳቸዉን ጥቅም በማስቀደም ከማህበሩ ጋር ተመሳሳይ ስራ የሚሰሩ ሶስት የህክምና ተቋም ከፍተዉ የሚሰሩ መሆኑን የ2ኛ ተከሳሽ ማህበርን ደንበኞች በመወስድ በእራሳቸዉ ተቋም አገለግሎት እየሰጡ የሚገኙ መሆኑን የማህበሩ የዉስጥም ሆነ ውጭ ኦዲትር የ1ኛ ተከሳሽ ወንድም መሆናቸዉን የማህበሩን ተሽከርካሪ ለግል ጥቅማቸዉ የሚገለገሉበት መሆኑን ከማህበሩም 4 ሚሊዮን ብር በብድር የወሰዱ መሆኑን የማህበሩ ፈርማሲ እንዲዘጋ አድርገዉ እራሳቸዉ ፋርማሲ ከፍተዉ ይህ ፋርማሲ ለ2ኛ ተከሳሽ መድሃኒት እንዲያቀርብ በማድረግ የ የማህበሩን ገንዘብ አለ አገባብ ወደ ራሳቸዉ እየወሰዱ የሚገኙ መሆኑን፤አፖሎ እና አንተርናሽናል ሆስፒታል ከ2ኛ ተከሳሽ የሚፈለጉት ክፍያ ተከፍሏቸዉ እያለ 1ኛ ተከሳሽ ዕዳዉ እንዳልተከፈለ እንዲመዘገቡ ያደረጉ መሆኑን የማህበሩንም ሰራተኞች እየወሰዱ በግል ባቋቋሙት የህክምና ተቋም እያሰሩ የሚገኙ መሆኑን በመገልጽ ያቀረቡትን ክርክር አጠናክረዉ የተከራከሩ ሲሆን ተከሳሾች በበኩላቸዉ ባቀረቡት ክርክር 1ኛ ተከሳሽ በከሳሾች ላይ ያደረሰዉ ጉዳት የሌለ መሆኑን በ1ኛ ተከሳሽ ተፈጽሟል ተብለዉ የተገለጹት በማስረጃ ያልተደገፉ መሆኑን የ1ኛ ተከሳሽ ወንድም የማህበሩን ሂሳብ ሰርቶ ለውጭ ኦዲትር ከሚያቀርብ በቀር የማህበሩ የውጭ ኦዲተር አለመሆኑን ቀደም ሲል ሁሉም የማህበሩ አባላት ደመዉዝ ሲከፈላቸዉ የነበረ መሆኑን አሁን ግን እንዲቀር የተወሰነ መሆኑን 1ኛ ተከሳሽ በግላቸዉ የከፈቱት የህክምና ተቋማት በ2ኛ ተከሳሽ ማህበር አለመሆኑን በዚህ ረገድም የቀረበ ማስረጃ የሌለ መሆኑን ከሳሾች ስበሰባ ሲጠሩ የማይገኙ መሆኑን የማህበሩ ዕዳ ተከፍሎ እያለ እንዳልተከፈለ ተመዝገቧል የተባለዉ ሀሰት መሆኑን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርን አባል የንግድ ህጉን አንቀጽ 261ን መሰረት በማድረግ ማሰናበት የማይቻል መሆኑን በማህበሩ የመተዳደሪያ ደንብና መመሰረቻ ጽሁፍ የማህበሩ አባል እንዲሰናበት የተደነገገ ድንጋጌ የሌለ መሆኑን 1ኛ ተከሳሽ ለማህበሩ ስራ አሰኪያጅ የሾሙት በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ መሆኑን ስራ አሰኪያጅ ለመሾም በማህበሩ የጋራ ስራ አሰኪያጅ እና በ1ኛ ተከሳሽ የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ የተደረገ መሆኑን ለከሳሾች በደብዳቤ እና በኢሜል ጥሪ ተደርጎላቸዉ ያልቀረቡ መሆኑን በመግለጽ የመከላከያ መልሳቸቸዉን አጠናክረዉ ተከራክረዋል፡፡
በመዝገቡ ላይ የቀረበዉ ጠቅላላ ክርክር ከላይ የተመለከተዉን ሲመስል ፍርድ ቤቱም 01/13/2010ዓ.ም በውልናማስረጃ የጸደቀዉ የ2ኛ ተከሳሽ ማህበር ቃለ ጉባኤ ሊሻር ይገባል ወይስ አይገባም እንዲሁም 1ኛ ተከሳሽ ከ2ኛ ተከሳሽ ማህበር አባልነት ሊሰናበቱ ይገባል ወይስ አይገባም የሚሉትን ነጥቦች በጭብጥነት በመያዝ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምረናል፡፡
የመጀመሪያዉን ነጥብ በተመለከተ 2ኛ ተከሳሽ ማህበር ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እንደመሆኑ መጠን ተፈጻሚነት ያላቸዉ የንግድ ህጉ ደንጋጌዎች ከአንቀጽ 510-543 ድርስ ያሉት መሆናቸዉ ገልጽ ነዉ፡፡ በንግድ ህጉ አንቀጽ 525(1) ስር አንደተመለከተዉ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በአንድ ወይንም ከአንድ በላይ በሆኑ ስራ አስኪያጆች ሊተዳደር እና ሊመራ እንደሚችል የተመለከተ ሲሆን ነገር ግን የማህበሩ አባላት ከ20 በላይ በሆኑ ጊዜ ዉሳኔዎች በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ሊወሰኑ አንደሚገባ በንግድ ህጉ አንቀጽ 525(2) ስር ተመልክቷል፡፡የማህበሩ አባላት ከ20 በሚበልጡ ጊዜ በማህበሩ የመተዳዳሪያ ደንብ በተወሰነዉ ቀን በየዓመቱ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ መካሄድ ያለበት መሆኑን የንግድ ህጉ አንቀጽ 532(1) የሚደንገግ ሲሆን ከጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባዎች ወጭ ሌሎች ስብሰባዎች በማህበሩ ስራ አስኪያጅ፤የማህበሩ ስራ አስኪያጅ በሌለበት ጊዜ በማህበሩ ኦዲተር፤ኦዲትር በሌለ ጊዜ በማህበሩ ላይ ከግማሽ በላይ ድርሻ ያለዉ አባል ጥሪ ሊደረግ እንደሚችል በንግድ ህጉ አንቀጽ 532(2) ተድንግጓል፡፡ በሌላ በኩል ማህበሩ በህግም በማህበሩ የመተዳደሪያ ደንብ ስብሰባ እንዲያካሂድ የማይገደድ ከሆነ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ሊወሰኑ የታሰቡትን ዉሳኔዎች ለአባላቱ በመላክ የማህበሩ አባላት ድምጽ እንዲሰጡበት ሊደረግ የሚገባ ስለመሆኑ በንግድ ህጉ አንቀጽ 533 ስር ተደንግጓል፡፡ የማህበሩ አባላት በስብሰባ ላይ የመገኝት እና በማህበሩ ላይ ባላቸዉ ድርሻ ልክም ድምጽ የመስጠት መብት ያላቸዉ መሆኑም የንግድ ህጉ አንቀጽ 537 ስር ተደንግጓል፡፡
በንግድ ህጉ ስለ ሃላፊነቱ የግል ማህበር በሚደነገግገዉ ክፍል በንግድ ህጉ አንቀጽ 535 መሰረት ማለትም ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ የሚገደድ ከሆነ ጠቅላላ ጉባኤ በማድረግ የሚወሰናቸዉ ዉሳኔዎች እንዲሁም የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ሊተላላፍ የታሰባዉን ዉሳኔ ለማህበሩ አባላት በመላክ የሚወሰኑ ዉሳኔዎች ዉጤታቸዉ ምን እንደሆነ የተመለከተ ባይሆን የንግድ ህጉ ስለ አክሲዮን ማህበር በተደነገገዉ ክፍል ዉስጥ የተመለከተዉን አንቀጽ 388 በማመሳሰል መጠቅም አሰፋላጊ ሲሆን በዚህ ደንጋጌ መሰረት በህግ አግባብ የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ ተድርጎ የተላላፉ ዉሳኔዎች ሁሉንም የማህበሩ አባላት ሊያስገደዱ እንደሚችሉ የተመለከተ ሲሆን ባለአክስዮኖች የማህበሩ ባለአክሲዮን በመሆናቸዉ የተገናጸፉትን መብቶች ማለትም በጠቅላላ ጉባኤ ላይ በሚተላላፉ ዉሳኔዎች ላይ ድምጽ የመስጠት መብታቸዉን ሊነፈጉ የማይገባ ስለመሆኑ የንግድ ህጉ አንቀጽ 534/389 ያስገነዝባል፡፡
ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርን ጠቅላላ ጉባኤ መጥራት አስፈላጊ ሲሆን ጥሪ የሚደረገዉ ለአባላቱ የተመዘገበ ደብዳቤ በመላክ መሆኑን ከንግድ ህጉ አንቀጽ 535(2) መረዳት የሚቻል ሲሆን ነገር ግን ለማህበሩ አባላት ጥሪ የሚላክላቸዉ ጉባኤዉ ወይንም ዉሳኔ ከሚወሰንበት ስንት ቀናት ቀደም ብሎ እንደሆነ የተመለከተ ነገር የለም እንዲሁም የጥሪ ደብዳበው ምን ምን ማካተት እንዳለበት የተመለከተ ነገር የለም፡፡በመሆኑም ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከአክሲዮን ማህር በጋራ የሚጋራዉ ባህሪ ያለዉ በመሆኑ እና ከዓላማቸዉ አንጻር በአክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ለመጥራት የተቀመጡትን ቅደመ ሁኔታዎች መጠቀም አሰፈላጊ ነዉ፡፡ በዚህም መሰረት ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አባላት በንግድ ህጉ አንቀጽ 535(1) በተመለከተዉ መሰረት ዉሳኔ ለመስተላላፍ የሰብሰባ የጥሪ ማስታወቂያ ከ15 ቀናት በፊት ቀድሞ ብሎ ሊደረሳቸዉ የሚገባ መሆኑ እንዲሁም በሰብሰባ ላይ ወይይት የሚደረግባቸዉ አጀንዳዎች በጥሪ ማስታወቂያ ላይ መገለጽ ያለባቸዉ ስለመሆኑ ከንግድ ህጉ አንቀጽ 395፤396 እና 397 መረዳት የሚቻል ሲሆን አንድ ስበሰባዉ አይነት ምለዓት ጉባኤ ካልተሟለ እና አሰፈላጊዉ ደምጽ ካላተገኘ በአጀንዳ ላይ የተገለጹትን የዉሳኔ ሀሳቦች ለማጽደቅ የማይቻል ስለመሆኑ ከንግድ ህጉ 399(1) መረዳት ይቻላል፡፡
ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂድ በህግ ወይም በማህበሩ መመሰረቻ ጽሁፍ ግዴት የተጣለበትም ሆነ ጠቅላላ ጉባኤ የማድርግ በህግም ሆነ በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ ግዴታ ያልተጣለበት ማህበር ዉሳኔዎች ማስተላላፍ ያለበት ከማህበሩ ካፒታል ላይ ከግማሽ በላይ ድርሻ ባላቸዉ አባላት ድጋፍ ሲያገኝ መሆኑ በመርህ ደራጃ በንግድ ህጉ አንቀጽ 535 የተደነገገ ሲሆን በልዩ ሁኔታ ደግሞ የማህበሩን ዜግነት ለመቀየር የማህበሩን አባላት ሙሉ ደምጽ የሚልግ መሆኑን እንዲሁም ሌሎች ማሻሻዎችን በማህበሩ መተዳዳሪያ ደንብ ለማድረግ በማህበሩ ላይ የሶስተኛ አራተኛ ድርሻ ባላቸዉ አባላት ዳግፍ ሊያገኝ የሚገባ መሆኑ በንግድ ህጉ አንቀጽ 536 ስር ተመልክቷል፡፡ ወደ ተያዘዉ ጉዳይ ሰንመለስ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቃለ ጉባኤ የጸደቀዉ በቀን 1/13/2010 ዓ/ም ሲሆን ተከሳሾች ለከሻሾች የሰብሰባ ጥሪ ተደርጎ ከሳሾች ባለመገኘታቸዉ 1ኛ ተከሳሽ ከማህበሩ ካፒታል ላይ ከግማሽ በላይ ድርሻ ያላቸዉ በመሆኑ በቃለ ጉባኤዉ ስራ አስኪያጅ በመሾም ዉሳኔ አስተላልፏል ዉሳኔዉም በማህበሩ መመሰረቻ ጽሁፍም ሆነ በንግድ ህጉ የተደገፈ ነዉ፡፡ በመሆኑም ቃለ ጉባኤ ሊሻር አይገባም በማለት ተከሳሾች ተክርክረዋል፡፡
ቃለ ጉባኤዉ ሊሻር ይገባል አይገባም የሚለዉን ነጥብ ለመመለሰ ቃለ ጉባኤዉን ለማጸደቅ የተጠራዉ ጠቅላላ ጉባኤ አጣራሩን እና አካሄዱን መመርመር አሰፈላጊ ነዉ፡፡ ከዚህ አንጻር የ2ኛ ተከሳሽ ማህበር አባላት ሶስት በመሆናቸዉ ጠቅላላ ጉባኤ ለማድርግ ግዴታ የሌለባቸዉ መሆኑን ከንግድ ህጉ አንቀጽ 532(1) መረዳት የሚቻል ቢሆንም የ2ኛ ተከሳሽ ማህበር መተዳደሪያ ደንብ ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ የሚያድርግ መሆኑን የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤም የማህበሩ የበላይ አካል መሆኑን እንዲሁም የማህበሩን ዋና ስራ አስኪያጅ የሚሾመዉም ሆነ የሚሸረዉ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ መሆኑ በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ 5.2.1 ስር ሰፍሯል፡፡ 2ኛ ተከሳሽ ማህበር ስራ አስኪያጅ ለመሾም ጠቅላላ ጉባኤ እንዲደርግ በመተዳዳሪያ ደንቡ ላይ በአስገዳጅ ሁኔታ አስቀምጧል ከተባለ ደግሞ ከሳሾች በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንዲሳተፉ በህጉ አግባብ ጥሪ ተድርጎላቸዋል ወይ የሚለዉን መመልከቱ ጠቀሚ ነዉ፡፡ ተከሳሾች ለከሳሾች በህጉ አግባብ ጥሪ ተድርጎላቸዋል በማለት የሚከራከሩ እንደመሆኑ መጠን ይህን ፍሬ ነገር የማስረዳት ሽከም አለባቸዉ፡፡
2ኛ ተከሳሽ ማህበር ጳጉሜ 1/13/2010 ዓ/ም በአካሄደዉ ጠቅላላ ጉባኤ የተገኙት የማህበሩ አባል 1ኛ ተከሳሽ ሲሆኑ 1ኛ ተከሳሽ ከማህበሩ ካፒታል ላይ ከግማሽ በላይ ድርሻ ማለትም 54% ድርሻ ያላቸዉ በመሆኑ ምንም እንኳን ሌሎች የማህበሩ አባላት በጠቅላላ ጉባኤ ላይ ያልተገኙ ቢሆንም የማህበሩ ስራ አስኪያጅ በማድረግ አቶ መዘምር ከተማን በስራ አስኪያጅነት የሾሙ መሆኑን የቀረበዉ ቃለ ጉባኤ ያስረዳል፡፡
በ2ኛ ተከሳሽ ማህበር መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 5(1) የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ የማህበሩ የበላይ አካል መሆኑን የማህበሩን ዋና ስራ አስኪያጅ የሚሾመዉም ሆነ የሚሻረዉ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ መሆኑ በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ 5.2.1 ስር ተመልክቷል፡፡
2ኛ ተከሳሽ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲደረግ ጥሪ አድርጊያለሁ ይበል እንጂ እራሱ በማስረጃት ያያዘዉ በቀን 13/10/2010 ዓ/ም በቁጥር ኤስዋይጂኤች/1013/18 የተጻፈ ደብዳቤ ቋሚ ዋና ስራ አስኪያጅ እና ሌሎች አጀንዳዎች ዉሳኔ ለማሰለፍ የማህበሩ አባለት በቀን 14/10/2010 ዓ/ም እንዲያገኙ የሚያሳስብ ድብዳቤ ሲሆን በዚህ ዕለት 1ኛ ተከሳሽ እና ሌሎች የማህበሩ አባላት ያልሆኑ የማህበሩ ጠበቆች ተገኝተዉ 1ኛ ተከሳሽ ስራ አስኪያጅ እንዲሾሙ ለ1ኛ ተከሳሽ ስልጣን መስጠቱ የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ የማሻሻል ዉጤት ያለዉ ነዉ፡፡
የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 5 መሰረት ስራ አስኪያጅ የመመረጥ ስልጣን የጠቅላላ ጉባኤዉ እንደመሆኑ መጠን የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ ለመሻሻል ¾ ድምጽ የሚያስፈልግ ከመሆኑ አንጻር 1ኛ ተከሳሽ ስራ አስኪያጁን እንዲመርጡ መወሰኑ ህገወጥ እና አስገዳነት የሌለዉ ነዉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቃለ ጉባኤ የተያዘዉ በ1/13/2010 ዓ/ም ሆኖ ሳለ ለከሳሾች በቀን 13/10/2010 ዓ/ም የተጻፈዉ ደብዳቤ በቀን 14/10/2010 ዓ/ም ለሚደረገዉ ስብሰባ እንደመሆኑ መጠን ተከሳሾች ይህኑኑ ደብዳቤ በማስረጃነት በማቅርብ ቃለ ጉባኤዉ ከመያዙ በፊት ለከሳሾች ጥሪ አድርገናል በማለት ያቀረቡት ክርክር ተገቢነት ያለዉ ካለመሆኑም በላይ ከ15 ቀናት በፊት የሰብሰባ ጥሪዉ ለከሳሾች ያልደረሰ በመሆኑ ተቀባይነት ያለዉ አይደለም፡፡ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የተላኩት ደብዳቤዎቹ ለከሳሾች የደረሱ መሆኑን የተከሳሽ 2ኛ ምስክር የገለጹ ቢሆንም ምስክሯ ደብዳቤዉ ለከሳሾች ሲሰጥ በቦታዉ ላይ ያልነበሩ እና ደብዳቤዉ ለከሳሾች የደረሳቸዉ መሆኑን ከሌላ ሰዉ የሰሙ መሆኑ፤ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር የስጋ ዝምድና ያላቸዉ መሆኑ ሲታይ እንዲሁም በቀን 1/13/2010 ዓ/ም ለተደረገዉ ስብሰባ ቀደም ብሎ በህጉ አግባብ ለከሳሾች ጥሪ የተደረገላቸዉ መሆኑን አለማስረዳታቸዉ ሲታይ ምስክሯ የሰጡት ምስክርነት እምነት የሚጣልበት ካለመሆኑም በላይ ምስክሯ ለከሳሾች ጥሪ ድርሷል የሚሉት ለሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ/ም የተጠረዉን ስብሰባ ሲሆን ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቃለ ጉባኤ የጸደቀዉ በዚህ ዕለት ባለመሆኑ እና ስራ አስኪያጁም የተሾሙት በዚህ ዕለት በተያዘ ቃለ ጉባኤ ባለመሆኑ በዚህ መልኩ በተከሳሾች የቀረበዉ ክርክር ተቀባይነት ያለዉ አይደለም፡፡
በቀን 14/10/2010 ዓ/ም ለሚደረገዉ ጠቅላላ ጉባኤ ከሳሾች የጥሪ ማስታወቂያ ደርሷቸዋል እንኳን ቢባል በተያዘዉ አጀንዳ መሰረት ስራ አስኪያጅ በመምረጥ ጉባኤዉ ያልተጠናቀቀ በመሆኑ በንግድ ህጉ አንቀጽ 535(2) መሰረት ሌላ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ ዉሳኔ ከሚሰጥ በቀር በቀን 14/10/2010 ዓ/ም ለሚደረግ ጠቅላላ ጉባኤ ቀደም ሲል ለከሳሾች ጥሪ ተድርጎላቸዋል በሚል ሌላ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ ሳይደረግ 1ኛ ተከሳሽ ለብቻቸዉ ቃለ ጉባኤ በመያዝ ስራ አስኪያጅ ሊሾሙ የሚችሉበት የህግ አግባብ የለም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሚያዚያ 1 ቀን 2010 ዓ/ም የ2ኛ ተከሳሽ ማህበር የጋራ ስራ አስኪያጅ የነበሩት በወ/ሮ ሕይወት ትርፍነህ ጥሪ የተደረገዉ የጠቅላላ ጉባኤ ጉባኤዉ አንደሚከናወን የሚገልጸዉ እ.ኤ.አ አፕሪል 12 በመሆኑ በቀን 1/13/2010 ዓ/ም ለተካዴዉ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ ሊያገልግልበት የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት የለም፡፡ስለሆነም በቀን 1/13/2010 ዓ/ም በውልና ማስረጃ መዝገባ ጽ/ቤት የተመዘገበዉ ቃለ ጉባኤ ለከሳሾች በንግድ ህጉ እና በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ እና ተካሂዶ ያልተወሰነ ዉሳኔ በመሆኑ በከሳሾች ላይ አሰገዳጀነት ሊኖረዉ ሰለማይገባ በንግድ ህጉ አንቀጽ 416(5) መሰረት ተሽሯል፡፡
2ኛዉን ነጥብ በተመለከተ 2ኛ ተከሳሽ ማህበር ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሲሆን ይህን ማህበር የሚገዛዉ የንግድ ህጉ ክፍል ከአንቀጽ 510-543 ስር የተገለጹት ድንጋጌዎች ናቸዉ፡፡ እነዚህ ደንጋጌዎች ደግሞ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አባል የሆነ ሰዉ ከማህበሩ ሊሰናበት የሚችልበትን አግባብ አያስቀምጡም፡፡በርግጥ ሃላፊነቱ የተወሰነ ማህበር የሽርክና ማህበር እና የአክሲዮን ማህበራት የተቀላቀለ ባህሪ ያለዉ ማህበር መሆኑን ከላይ ከተጠቀሱት ድንጋጌዎች መረዳት ይቻላል፡፡
በሽርክና ማህበራት ዉስጥ የአባሉቱ ማንነት እና ባህሪ (personality of members) ለማህበሩ ቀጣይነት ዋሳኝ ነዉ ይህም የሆነዉ የሽርክና ማህበራት የሰዎች ስብስብ (association of persons) ስለሆነ ሲሆን የአክሲዮን ማህበር ዉስጥ ደግሞ የአባላቱ ማንንትም ሆነ ባህሪ ለማህበሩ ቀጣይነት ጠቃሚ አይደለም ይህም የሆነበት ምክንያት የአክሲዮን ማህበራት የካፒታል ስብስብ(association of capital) በመሆናቸዉ ነዉ፡፡ ከዚህ አንጻር ተከሳሽ ከማህበሩ ሊሰናበት ይገባል ወይስ አይገባም የሚለዉን ነጥብ ሃላፊነቱ የተወሰነ ግል ማህበር ያለዉን የተቀላቀለ ባህሪ መሰረት በማድረግ መመርመር ያስፈልጋል፡፡
ከሳሾች ተከሳሽ ከማህበሩ እንዲሰናበት መሰረት አድርገዉ የሚከራክሩት የንግድ ህጉን አንቀጽ 261 እና 279 ሲሆን እነዚህም ድንጋጌዎች እንደየቅደመተከተላቸዉ የሚገኙት በንግድ ህጉ ስለ ተራ ሽርክና እና ስለ እሽሙር ማህበር በሚደነግገዉ የህግ ክፍል ነዉ፡፡ የነዚህንም ድንጋጌዎች ይዘት ስንመለከተ ፍርድ ቤት በቂ ምክንያት ሲኖር እንዱን ማህበርተኛ ከማህበሩ እንዲወጣ ሊፈርድ እንደሚችል ያስቀምጣል፡፡እነዚህ ድንጋጌዎችም የሚገኙት ስለ ተራ የሽርክና ማህበር እና ስለ እሽሙር ማህበር በሚደነግገዉ የህግ ክፍል እንደመሆኑ መጠን እና ስለ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በሚደነግገዉ የንግድ ህጉ ክፍል ተጠቃሾቹ ድንጌዎች አገልግሎት ላይ ሊውል እንደሚችል የተመለከተ ገልጽ ነገር ባለመኖሩ ደንጋጌዉ በሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ላይ ተፈጻሚነት የሌለዉ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡በመሆኑም በንግድ ህጉ አንቀጽ 261 የተራ ሽርክና ማህብርተኞችን እና በአንቀጽ 279(1) ላይ የእሽሙር የሽርክና ማህበር አባልን በፍርድ ቤት ከሽርክና ማህበር እንዲወጣ ለመወሰን የሚያስችል በግልጽ ተደንግጎ እያለ ስለ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አባልን ፍርድ ቤት ከአባልነት እንዲሰርዝ ለመወሰን እንደሚቻል ያለመደነገጉ ተጠቃሾቹ ደንጋጌዎች በሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ላይ ተፈጻሚነት የሌላቸዉ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ከዚህም በተጨማሪ በ1ኛ ከሳሽ ማህበር የመመሰረቻ ጽሁፍም ሆነ የመተዳደሪያ ደንብ የማህበሩ አባል ከማህበሩ አባል ሊሰናበት የሚችልበትን አግባብ አልተቀመጠም፡፡ እንዲሁም ተራ የሽርክና ማህበር በንግድ ህጉ አንቀጽ 5 ስር በተዘረዘሩት የንግድ ስራዎች ላይ መሳተፍ እንደማይችል እንዲሁም ተራ የሽርክና ማህበር የንግድ ማህበራት ባህሪ የሌለዉ መሆኑን ከንግድ ህጉ አንቀጽ 213 እና 227 መረዳት የሚቻል ሲሆን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዓላማዉ ምንም ቢሆን የንግድ ማህበር መሆኑ በንግድ ህጉ አንቀጽ 10(2) ስር የተቀመጠ በመሆኑ እና ሁሌም የንግድ ስራ የሚስራ ከመሆኑ አንጻር እና ተራ የሽርክና ማህበር እንደ ንግድ ድርጅት የማይቆጠረ ከመሆኑ አንጻር በተራ የሽርክና ማህበር ስር የተደነገገን ደንጋጌ አመሳሰሎ(analogy) በግልጽ የንግድ ማህበር መሆኑ የተቀመጠ የንግድ ማህበር ላይ ተፈጻሚ ማድረግ አግባብነት የለዉም፡፡ ስለሆነም ተከሳሽ ከ1ኛ ከሳሽ ማህበር ሊሰናበት የሚችልበት የህግ አግባብ የሌለ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ የከሳሾች በዚህ ረገድ የጠየቁትን ዳኝነት ውድቅ አድርጓል፡፡
ውሳኔ
1ኛ) በቀን 1/13/2010 ዓ/ም በ2ኛ ተከሳሽ ማህበር ተይዞ የጸደቀዉ ቃለ ጉባኤ ተሽራል፡፡
2ኛ) ወጪና ኪሳራ ከሳሾች ለዳኝነት የከፈሉትን ብር 90፤የጠበቃ አበል ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺህ) እንዲሁም ለቀረጥ ቴምብር የተከፈለ ብር 45(አርባ አምስት) ተከሳሾች ለከሳሽ ይክፈሉ፡፡
ትዕዛዝ
ይግባኝ መጠየቅ መብት ነው፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
- Details
- Category: የንግድ ችሎት ውሳኔዎች
- Abyssinia Law | Making Law Accessible! By
- Hits: 4136
የመ/ቁጥር 172869
ታህሳስ 20 ቀን 2012 ዓ/ም
ዳኛ፡- አሸናፊ ለሜቻ
ከሳሽ፡- አቶ በረከት ታደገኝ ፡-ወኪል ማንያህልሻል ንቦ፡- ቀረቡ
ተከሳሾች፡- 1ኛ) አቶ ሳሙኤል አርከበ፡- ቀረቡ
2ኛ) ቢም አይቲ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግ/ማ ጠበቃ ማቲያስ ግርማ፡- ቀረቡ
መዝገቡ ለዛሬ የተቀጠረው ለምርመራ ተብሎ ሲሆን ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡
ፍርድ
ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው ከሳሽ ሰኔ 25 ቀን 2010 አሻሽለው ያቀረቡት የክስ አቤቱታ ሲሆን ይዘቱም ከሳሽና 1ኛ ተከሳሽ እያንዳንዳቸዉ 50/100 የሆነ ድርሻ በመያዝ ዋናው ሥራው በዌብሳይት አማካኝነት የጨረታ መረጃዎች የሚሰጠዉን 2ኛ ተከሳሽ ማህበር ቢም አይቲ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግ/ማ የመሰረቱ መሆኑን፤በማህበሩ መመስረቻ ደንብ እንዲሁም ህደር 13 ቀን 2001 ዓ/ም እና ታህሳስ 10 ቀን 2001 ዓ/ም በተደረገዉ የባለአክሲዮኖች ስብሰባ ከሳሽ እና 1ኛ ተከሳሽ ማህበሩን በጣምራ ሥራ አስኪያጅነት ለመምራት በሙሉ ድምጽ የወሰኑ መሆኑን በዚህም መሰረት የማህበሩን የባንክ ሂሳብ መክፈት ማንቀሳቀስ፤መዝጋት እንዲሁም የማህበሩን ንብረት አስይዞ የመበደር ስልጣን የከሳሽ እና የ1ኛ ተከሳሽ የጋራ ስልጣን መሆኑን ስራቸዉንም በጋራ ሲሰሩ የቆዩ መሆኑን፡፡ ነገር ግን ከመስከረም 2009 ዓ.ን ጀምሮ በከሳሽ እና በ1ኛ ተከሳሽ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ከሳሽ በ2ኛ ተከሳሽ ማህበር ዉስጥ ያላቸዉን ተሳትፎ ያቆሙ መሆኑን 1ኛ ተከሳሽ አለመግባባቱ ከተከሰተ ጀምሮ ማስጠንቀቂ በመስጠት እና በማስፈራራት ተጽእኖ ሲያሳድሩባቸዉ የነበረ መሆኑን፤1ኛ ተከሳሽ 2ኛ ተከሳሽ ማህበር አግልግሎት በመስጠት የሚገኘዉን የአገልግሎት ክፍያ በቼክ እየሰበሰቡ በማህበሩ ስም ወደተከፈተ የባንክ የሂሰብ /Account/ ገቢ ማድረግ ሲገባቸዉ ከአሰራር ውጪ በጥሬ ገንዘብ እየተቀበሉ በካዝና ሲያስቀምጡ የቆዩ መሆኑን ከዚህም በላይ ያለከሳሽ ፈቃድ በጣምራ ሊንቀሳቀሱ የሚገባውን ገንዘብ ያለከሳሽ እውቅና 1ኛ ተከሳሽ አላግባብ በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ያባከኑ ከመሆኑም በላይ ከሳሽ ሊከፈላቸዉ የሚገባዉን የወር ደሞዝ እና የትርፍ ድርሻ ለመከፈል ፈቃደኛ ሊሆኑ ያልቻሉ መሆኑን፤1ኛ ተከሳሽ ከመደበኛው የማህበሩ ሂሳብ አሰራር ውጪ የማህበሩን ገንዘብ ሲያንቀሳቅሱ የነበረ መሆኑን በዚህም ምክንያት የማህበሩ ሂሳብ በገለልተኛ የሂሳብ ባለሙያ እንዲመረመር ጠይቀዉ 1ኛ ተከሳሽ ፈቃደኛ ሳይሆኑ የቀሩ መሆኑን እንዲሁም 1ኛ ተከሳሽ ከሳሽ የማህበሩን ዌብሳይት እንዳይጠቀሙ ፓስዋርድና ዩዘር ኔም የቀየሩ መሆኑን ገልጸዉ 1ኛ ተከሳሽ ከማህበሩ ሥራ አስኪያጅነት ተሽረው ከማህበሩ ባለአክሲዮኖች ውጪ የሆነ ገለልተኛ ስራ አስኪያጅ እንዲሾም እንዲወሰንላቸዉ፤1ኛ ተከሳሽ የማህበሩን ዌብሳይት ዩዘር ኔምና ፓስዋርድ መቀየራቸው ተገቢ አይደም ተብሎ እንዲወሰንላቸዉ፣ የ2ኛ ተከሳሽ ማህበር ገቢ በቼክ እየተሰበሰበ በባንክ መቀመጥ ሲገባው በጥሬ ገንዘብ እየተሰበሰበ በቀጥታ ወጪ መደረጉ ተገቢ አይደለም ተብሎ እንዲወሰንላቸዉ፣ያለ ከሳሽ ተሳትፎ በተናጠል በ1ኛ ተከሳሽ አማካኝነት የተፈፀሙ ክፍያዎች በሙሉ ሕገወጥ ናቸው ተብሎ እንዲወሰንላቸዉ፣ከመስከረም 2009 ጀምሮ ያለዉ የማህበሩ ሂሳብ በገለልተኛ ባለሙያ እንዲመረመር እንዲወሰንላቸዉ፤1ኛ ተከሳሽ በተናጠል የኢተዮጵያ ንግድ ባንክ፣ህብረት ባንክ እና ከወጋገን ባንክ ገንዘብ ማውጣት ተገቢ ያልሆነ ተግባር ነው ተብሎ እንዲወሰንላቸዉ እንዲሁም ከሳሽ በ1ኛ ተከሳሽ ጥፋት ምክንያት በማህበሩ ላይም ሆነ በከሳሽ ላይ የደረሰዉን ጉዳት፤ያልተከፈላቸዉውን ደሞዝ እንዲሁም ያልተከፈላቸውን የትርፍ ደርሻ አስመልክቶ ክስ የማቅረብ መብታቸዉ እንዲጠበቅላቸዉ እንዲሁም በዚህ ክስ ምክንያት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ ተከሳሾች እንዲተኩ እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት ጠይቋል፡፡
ከሳሽ ክሱን ያስረዱልኛል ያላቸውን የሰነድ ማስጃዎች አቅርቧል የሰዉ ምስከሮች ቆጥሯል፡፡ ተከሳሾች የከሳሽ ክስ ከነ አባሪዎቹ ደርሷቸዉ ጥር 20 ቀን 2011 ዓ/ም በተጻፈ የመከላከያ መልሳቸዉን ያቀረቡ ሲሆን ባቀረቡት መከላከያ መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የፍሬ ነገር መልስ ሰጥቷል፡፡ ተከሳሾች ያቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በተመለከተ ፍርድ ቤቱ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዉ ላይ ግራ ቀኙን ከከራከረ በኃላ ሐምሌ 15 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት ውድቅ ያደረጋቸዉ በመሆኑ እና ዝርዝሩም ከመዝቡ ሰፍሮ የሚገኝ ስለሆነ ከዚህ ማሰፈር ሳያስፈልግ ታልፏል፡፡
ተከሳሾች በፍሬ ነገሩ ላይ በሰጡት መልስ 1ኛ ተከሳሽ በከሳሽ ላይ ዛቻና ማስፈራራት ያልፈጸሙ መሆኑን ከሳሽ ስራቸዉን የለቀቁት በገዛ ፈቃዳቸዉ መሆኑን ከከሳሽ ጋር አለመግባባት የተፈጠረበት ምክንያት ከሳሽ ሰኔ 16 ቀን 2008 ዓ/ም ግብርን ለመሰወር ያቀረቡትን ሀሳብ ባለመቀበላቸዉ መሆኑን ከሳሽ ከሰኔ 20-26 2008 ዓ/ም ባለው ግዜ የማህበሩን ድህረገጽ ኮድ ቀይረው 1ኛ ተከሳሽ እንዳይከፍተው እና እንዳይቆጣጠረው ያደረጉ መሆኑን እንዲሁም 1ኛ ተከሳሽ ከደንበኞቹ የኢሜል መልዕክት እንዳይደርሰው ጠልፎ በማስቀረት ህገወጥ ድርጊቶችን የፈጸሙ መሆኑን ከሳሽ አስከ 2009 ዓ/ም ሲያስተዳድረው ከነበረው 2ኛ ተከሳሽ ማህበር ጋር ተመሳሳይ ስራ የሚሰራ ቢቲኤ ቴክኖሎጂ የተባለ ድርጅት አቋቁሞ የጥቅም ግጭት የፈጠረ መሆኑን ከሳሽ እና 1ኛ ተከሳሽ ማናቸዉንም ስራ በእንደነት ለማከናወን ተስማምቷል በማለት ከሳሽ የገለጹት ሀሰት መሆኑን ህዳር 13 ቀን 2001 ዓ/ም የተደረገው የባለአክሲዮኖች ስብሰባ አላማ ስራ አስኪያጆችን ለመሰየም ብቻ ሲሆን ይህ ማለት ደግሞ ሁለቱም ስራ አስኪያጆች በየራሳቸው የስራ ድርሻ እንዲወጡ መሆኑን፣ከሳሽ እና 1ኛ ተከሳሽ በጋራ የሚያከናውኑትን ስራ በተመለከተ ታህሳስ 10 ቀን 2001 ዓ/ም በተጻፈ ቃለ ጉባዔ ላይ በገልጽ የሰፈረ መሆኑን 1ኛ ተከሳሽ የ2ኛ ተከሳሽን የዕለት ተዕለት ተግባር በቅንነት ከማከናውን በስተቀር የማህበሩን ገንዘብ ብቻውን ያላንቀሳቀሰ መሆኑን 1ኛ ተከሳሽ ህግን ተላልፎ ያከናወነው ሕገወጥ ተግባር የሌለ መሆኑን ከስራ አስኪያጅነት ለመሻር የሚያበቃ ጥፋት ያልፈጸመ መሆኑን ከሳሽ ማህበሩ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ እስከ 2006 ዓ/ም ድርስ በየዓመቱ የትርፍ ክፍፍል እየወሰደ የነበረ መሆኑን ከሳሽ በተደጋጋሚ ስበሰባ ተጠርተዉ ሳይመጡ የቀሩ መሆኑን የማህበሩ የአገልግሎት ክፍያ በቼክም ሆነ በጥሬ ገንዘብ ሲሰበሰብ የነበረ መሆኑን የተሰበሰበዉንም ገንዘብ 1ኛ ተከሳሽ ለማህበሩ ስራ ሲያውል የነበረ መሆኑን ከባንክ ገንዘብ ወጪ የተደረገዉ ከሳሽም ራሳቸው ፈርመው በነበሩት ሲፒዮች መሆኑን እንዲሁም ማህበሩ ኦዲት ሊደረግ የሚገባዉ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ እንጂ ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ መሆን የሌለበት መሆኑን ፍርድ ቤቱ በሚመድበው ሰብሳቢ አማካኝነት ባለአክሲዮኖቹ ሥራአስኪያጅ አንዲመርጡ የቀረበው ጥያቄም የሕግ መሠረት የሌለዉ ስለሆነ ውድቅ ሊደረግ የሚገባዉ መሆኑን ከሳሽ ወደፊት ክስ ለማቅርብ እንዲፈቀድላቸዉ የጠየቁትም ከሥነሥርዓት ውጭ ስለሆነ ውድቅ ሊደረግ የሚገባዉ መሆኑን በመግለጽ የመከላከያ መልሳቸዉን አቅርቧል፡፡
ፍርድ ቤቱም ጥቅምት 5/2012 ዓ.ም ክስ የሰማ ሲሆን በዚህም መሰረት ከሣሽ ባቀረቡት ክርክር ከሳሽ እና 1ኛ ተከሳሽ የማህበሩን መመስረቻ ጽሁፍ በማሻሻል የጋራ ስራ አስኪያጅ ሆነዉ እንዲሰሩ የተወሰነ መሆኑን 1ኛ ተከሳሽ ከሳሽ ስራ እንዲያቆም በማድረግ የማበሩን ስራ ለብቻዉ እየሰራ መሆኑን የማህበሩ ሂሳብም በከሳሽ እና 1ኛ ተከሳሽ በጋራ እንዲንቃሳቀስ በቃለ ጉባኤ የተወሰነ መሆኑን ገንዘብ ወጪ ሲደረግበት የነበረዉ ሲፒዮ ላይ ያረፈዉ ፊርማ የከሳሽ አለመሆኑን ይህ ክስ በቀረበበት ጊዜ በማህበሩ ሂሳብ ላይ የሚገኘዉ ገንዘብ ብር 552,979(አምስት ሀምሳ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ ዘጠኝ ) ብቻ መሆኑን ይሁን እንጂ በማህበሩ ሂሳብ ላይ ብር 3.4 ሚሊዮን መገኘት የነበረበት መሆኑን ከ2009 ዓ/ም ጅመሮ የማህበሩ ትርፍ ክፍፍል ተፈጸሞ የማያውቅ መሆኑን የከሳሽ ደመዉዝም ተከፍሎ የማያውቅ መሆኑን ከሳሽ እና 1ኛ ተከሳሽ የስራ አስኪያጅነቱን ስራ ተግባብተዉ መስራት የማይችሉ መሆኑን በዚህም ምክንያት የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ከውጭ ሊሰየም የሚገባዉ መሆኑን የማህበሩ ሂሳብ ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ በገለልተኛ የሂሳብ ባለሙያ ያልተሰራ መሆኑን የተሰራዉም በማህበሩ የሂሳብ ሰራተኛ መሆኑን ከሳሽ ስራ ካቆመ በኃላ የማህበሩ ገንዘብ በሲፒዮ ወጪ ሲደረግ የነበረ መሆኑን በዚህ ሲፒዮ ላይ ያረፈዉ ፊርማ የከሳሽ አለመሆኑን ገልጸዉ ያቀረቡትን ክስ አጠናክረዉ ክርክራቸዉን ሲያቀርቡ ተከሳሾች በበኩላቸዉ ከሳሽ ስራ ያቆሙት ከ2ኛ ተከሳሽ ማህበር ጋር ተመሳሳይ ስራ የሚሰራ ቢቲኤን የተባለ ድርጅት ስለቋቋሙ መሆኑን የ2ኛ ተከሳሽን ደንበኞችም አዲስ ወደ አቋቋሙት ማህበር ወስደዉ ስራ የሰሩ መሆኑን ከሳሽ ገንዘብ ወጪ የተደረገባቸዉን ሲፒዮች ፈርመዉ የነበረ መሆኑን ሲፒዮም አገልግሎቱ ለመንግስት ክፍያ መፈጸሚያ መንግድ መሆኑን ከሳሽ ከመስከረም 2009 ዓ/ም ጀምሮ ስራ ላይ ያልነበሩ በመሆኑ ደመዉዝ ሊከፈላቸዉ የማይገባ መሆኑን ከከሳሽ ጋር አብረዉ የማህበሩን ስራ መስራት የማይችሉ መሆኑን ከማህበሩ አባላት ወጪ የሆነ ሰዉ የማህበሩን ጥቅም የሚያስከብር እስከሆነ ድረስ በስራ አሰኪያጅነት ቢሾም ተቃውሞ የሌላቸዉ መሆኑን ለማህበሩ የውጭ ኦዲተር ተሰይሞ የማያውቅ መሆኑን የማህበሩ ሂሳብ ይጠራ ከተባለ መጣራት ያለበት ከ2001 ዓ/ም ጀምሮ መሆኑን የተፈጸሙት ክፍያዎች አግባብነት ያላቸዉ በመሆኑ ህግ ወጥ ሊባሉ የማይገባ መሆኑን ከሳሽ እስከ 2009 ዓ/ም ድረስ ማህበሩን ለብቻቸዉ ሲመሩ የነበረ ስለሆነ 1ኛ ተከሳሽ ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ ማህበሩን ለብቻቸዉ መምራታቸዉ ህገ ወጥ ሊባል የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት የሌለ መሆኑን ማህበሩ ግልጽ የሆነ የሂሳብ መመሪያ የሌለዉ መሆኑን ገንዘብ ወጪ የተደረገዉ በሲፒዮ ላይ ያለዉ ፊርማ የከሳሽ ፊርማ መሆኑ ተረጋግጦ መሆኑን ከሳሽ በሲፒዮ ላይ ያረፈዉ ፊርማ የተጨበረበረ ነዉ በሚል ያቀረቡት ክስ የሌለ መሆኑን ይህም የሚያሳየዉ በሲፒዮ ላይ ያረፈዉ ፊርማ የከሳሽ ስለመሆኑ መሆኑን ከሳሽ ማህበሩ ጠቅላላ የሰበሰበዉ ገንዘብ በሂሳብ ላይ መታየት አለበት ያሉት አግባብነት የሌለዉ መሆኑን ማህበሩ ገቢ ብቻ ሳይሆን ወጪም የሚያወጣ መሆኑንበመግለጽ የመከላከያ መልሳቸዉን አጠናክረው ተከራክረዋል፡፡
የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተዉን ሲመስል ፍርድ ቤቱም ቀጥሎ የተመለከቱትን ጭብጦች በመያዝ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሯል፡፡
1ኛ) 1ኛ ተከሳሽ ከጋራ ስራ እሰኪያጅነት ሊሻር ይገባል ወይስ አይገባም ?
2ኛ) ከ1ኛ ተከሳሽ ማህበር አባላት ወጪ የሆነ ሰዉ በስራ አስኪያጅነት ሊሾም ይገባል ወይስ አይገባም ?
3ኛ) የ2ኛ ተከሳሽ ማህበር ሂሳብ ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ በገለልተኛ የሂሳብ ባለሙያ አዲት ሊደረግ ይገባል ወይስ አይገባም ?
4ኛ) በ2ኛ ተከሳሽ ማህበር ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ የወጡ ወጪዎች እና የተፈጸሙ ክፍያዎች ህግ ወጥ ሊባሉ ይገባል ወይስ አይገባም ?
5ኛ) 1ኛ ተከሳሽ ማህበር የአገልግሎት ክፍያ በጥሬ ገንዘብ ሰብስቦ በቀጥታ ወጪ አድርጓል አላደረግም አድጓል የሚባል ከሆነ አግባብነት አለዉ ወይስ የለዉም
1ኛዉን ነጥብ በተመለከተ ኃ/የተ/ግ/ማህበር በአንድ ወይም ብዙ ሥራ አስኪያጆች ሊተዳደር አንደሚችል እንዲሁም ሥራ አስኪያጅ ከማህበሩ አባላት ወይም ከማኅበረተኞች ውጭ ሊምረጥ እንደሚችሉ የንግድ ሕጉ አንቀጽ 525 እና 526 ይደነግጋል፡፡በዚሁ ድንጋጌ አግባብ 1ኛ ተከሳሽ የ2ኛ ተከሳሽ ማህበር ጣምራ ስራ አስኪያጅ ሆነዉ የተሰየሙ መሆኑን ማህበሩ ህዳር 13 ቀን 2001 ዓ/ም የያዘዉ ቃለ ጉባኤ ያስረዳል፡፡ይህ ቃለ ጉባኤም የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ አካል እንደሆነ በቃለ ጉባኤዉ ላይ ተመልክቷል፡፡ይህ ከሆነ ደግሞ 1ኛ ተከሳሽ በማህበሩ መመሰረቻ ጽሁፍ የጣምራ ስራ አስኪያጅ ሆነዉ የተሾሙ መሆኑን መገንዘብ የሚቻል ሲሆን በማህበሩ የመመስረቻ ጽሁፍ የተሾመ ሥራ አስኪያጅ ከሥራ አስኪያጅ ስልጣኑ ሊሻር የሚችለዉ በንግድ ህጉ 527(1) እና 536(2) መሰረት ከማህበሩ ባለአክሲዮኖች መካከል በሶስተኛ አራተኛ ድምጽ ባላቸዉ ባለአክሲዮኖች ስር አስኪያጁ እንዲሻር ድጋፍ ሲያገኝ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ ይህ ድንጋጌም ተፈጻሚነት ያለዉ የማህበሩን ሥራ አስኪያጅ በጠቅላላ ጉባኤ ለመሻር በቀረበ ጊዜ ሲሆን በሌላ በኩል እንድ ስራ አስኪያጅ በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ የተሾመ ቢሆንም ስራ አስኪያጁ ከስልጣኑ እንዲነሳ ሊያደረጉ የሚችሉ ጥፋቶች እስካሉ የማህበሩ አባላት ስራ አስኪያጁ በፍርድ ቤት ዉሳኔ እንዲሻር መጠየቅ እንደሚቻሉ በንግድ ህጉ አንቀጽ 527(5) ተመልክቷል፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት የማህበር አባል የሚገባ ምክንያት(good cause) እስካለ ድረስ ስራ አስኪያጁ እንዲሻር ክስ ሊያቅርብ እንደሚችል ተመልክቷል፡፡ ተጠቃሹ ደንጋጌ የሚገባ ምክንያት (good cause) ምን ምን እንደሆነ በዝርዝር የሚያስቀምጠዉ ነገር የለም በንግዱ ህጉ አንቀጽ 528(1) የሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ የማህበሩን ዓላማ ወሰን ሳያልፍ በማናቸዉም ሁኔታዎች ሁሉ በማህበሩ ስም ለመስራት ስልጣን ያለዉ መሆኑ የተመለከተ ሲሆን የአንድ ማህበር ዓለማ እና ግብ የሚታወቀዉ ከማህበሩ መመሰረቻ ጽሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ነዉ፡፡ በመሆኑም ስራ አስኪያጅ የማህበሩን ዓላማ ለማሳካት የማህበሩን መመስረቻ ጽሁፍ፤መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም ህግን መሰረት አድርጎ የመስራት ግዴታ እና ሃላፊነት አለበት፡፡ከእነዚህ ማዕቆፎች ወጭ በስራ አስኪያጅ የተፈጸመ ተግባርም የማህበሩን ዓላማ ለማሳካት ተድርጎ የማይወሰድ ጥፋት መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡
ከሳሽ 1ኛ ተከሳሽ ከጣምራ ስራ አስኪያጅነቱ ሊሻር ይገባል በማለት በዋንኝነት የሚከራክሩት የማህበሩን ሂሳብ ለብቻዉ አንቀሳቅሷል የትርፍ ክፍፍል እንዳይፈጸም አድርጓል፤በማህበሩ ሂሳብ ላይ መገኘነት የነበረበት የገንዘብ መጠን እንዳይገኝ አድርጓል የማህበሩ ዌበሳይት ዩዘር ኔምን ቀይሯል እንዲሁም የማህበሩን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸዉ አውለዋል በማለት ሲሆን 1ኛ ተከሳሽ ከሳሽ ከጋራ ስራ አስኪያጅነት ስራዉ ሳይሻር ከሳሽ ወደ ቢሮቸዉ እንዳይገቡ የ2ኛ ተከሳሽ ማህበርን ቁልፍ እና የማህበሩን ዌብሳይት ፓስዋርድ መቀየራቸዉ የተመሰከረ መሆኑ ሲታይ ከሳሽ የማበሩን ሰነዶች መመለከት በንግድ ህጉ አንቀጽ 537 የተጠበቀለት መብት ሆኖ እያለ 1ኛ ተከሳሽ ይህን በመተላላፍ ክልከላ ማድረጋቸዉ፤የማህበሩ መመሰረቻ ጽሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ በሚደነግገዉ መሰረት በየአመቱ እንደ ስራ አስኪያጅነታቸዉ እና በተግባር ማህበሩን ከ2009 ዓ/ም እንደመምራቸዉ የትርፍ ክፍፍል እንዲደርግ ያለማድረጋቸዉ፤ሰብሰባ እንዲጣራ ከሳሽ ጠይቀዉ 1ኛ ተከሳሽ ምላሽ አለመስጠታቸዉ መመስከሩ ሲታይ እንዲሁም የማህበሩ የሂሳብ ሪፖርት በ2009 እና በ2010 ዓ/ም ካሽ ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ያለዉ መሆኑን የሚያሳይ መሆኑን ነገር ግን በተግባር በማህበሩ የባንክ ሂሳብ ዉስጥ የሚገኘዉ አራት መቶ አርባ ሺህ ብቻ መሆኑ የተመሰከረ ከመሆኑ አንጻር 1ኛ ተከሳሽ በንግድ ህጉ አንቀጽ 528 መሰረት እንዲሁም በማህበሩ መመስረቻ እና መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ለማህበሩ ጥቅም እየሰራ አለመሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ሲጠቃለልም በከሳሽ በኩል የቀረቡት ማስረጃዎች 1ኛ ተከሳሽ ከስራ አስኪያጅነት ስልጣን ሊያሰነሳቸዉ የሚችል በቂ ምክንያት መኖሩን፤የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ፤መመሰረቻ ጽሁፍ እና የንግድ ህጉን በመተላላፍ ጥፋት የፈጸሙ መሆኑን በአግባቡ ያስረዱ ሲሆን በ1ኛ ተከሳሽ በኩል የቀረቡት ማስረጃዎች 1ኛ ተከሳሽ የፈጸሙትን ጥፋቶች የሚያስተባብሉ አይደሉም፡፡ ስለሆነም 1ኛ ከ2ኛ ተከሳሽ ማህበር የጋራ ስራ አስኪያጅነት እንዲሻር ተወስኗል፡፡ ይሁን እንጂ የማህበር ሥራ አስኪያጆች እንደ ማህበሩ ወኪል የሚቆጠሩ መሆኑን የንግድ ህጉ አንቀጽ 33 የሚደነግግ በመሆኑ፤የንግድ ህጉ ከአንድ በላይ የሆኑ ሥራ አስኪያጆች ማህበሩን የሚመሩ እና የተሰጣቸዉም ስልጣን በጋራ አንድ አይነት ጉዳይ ለመከናወን እንዲችሉ ከሆነ የአንዱ ሥራ አስኪያጅ ከሥራ አሰኪያጅነት መሻር ያላዉን ዉጤት የማያሰቀምጥ ስለሆነ በንግድ ህጉ አንቀጽ 1 በተደነገገዉ መሰረት የፍ/ህ/ቁ 2231ን መጠቀም አሰፈላጊ ነዉ፡፡ከዚህ አንጻር ከሳሽ እና 1ኛ ተከሳሽ የማህበሩን የባንክ ሂሳብ በጋራ ለመከፈት፤ለማንቀሳቀስ፤ለመዘጋት የማህበሩን ንብረት በዋስትና ለማሲያዝ ከባንክም ሆነ ከድርጅት ገንዘብ በብድር ለመውሰድ በጣምራ እንዲሰሩ የተሰየሙ መሆኑን ማህበሩ ታህሳስ 10 ቀን 2001 ዓ/ም እና ህዳር 13 ቀን 2001 ዓ/ም ከያዘዉ ቃለ ጉባኤ መረዳት የሚቻል ሲሆን በፍ/ሕ/ቁ 2231(1) ድግሞ ከአንድ በላይ የሆኑ ተወካዮች ተመሳሳይ ጉዳይ በጋራ እንዲያከናውኑ ስልጣን ተሰጥቷቸዉ እያለ አንደኛዉ የተሰጠዉን ስልጣን መከናወን እንዳይችል ከተደረገ ለሌላኛዉም ወኪል የተሰጠዉ ስልጣን ቀሪ እንዲሆን የተመለከተ ስለሆነ 1ኛ ተከሳሽ ከጣምራ ሥራ አስኪያጅነቱ በመሻሩ ከሳሽ ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር በጣምራ የተሰጠዉን ስልጣን ለብቻዉ ለማከናወን አያስችለዉም፡፡
2ኛ ነጥብ በተመለከተ ምንም እንኳን ተከሳሾች ባቀረቡት የመከላከያ መልስ ከ2ኛ ተከሳሽ ማህበር አባላት ወጭ ገለልተኛ ስራ አሰኪያጅ የሚሾመበት የህግ መሰረት የለም በማለት መልሳቸዉን ያቀረቡ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ክስ በሰማ ዕለት ለማህበሩ ጥቅም የሚሰራ እስከሆነ ድረስ ከማህበሩ አባላት ውጭ የሆነ ስራ አስኪያጅ ቢሾም የማይቀወሙ መሆኑን ለችሎቱ አስረድቷል፡፡ይህ ከሆነ ደግሞ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርን ከማህበሩ አባላት ወጭ የሆኑ ሰዎች በስራ አስኪያጅነት ሊመሩት እንደሚችሉ በንግድ ህጉ አንቀጽ 525(1) የተመለከተ በመሆኑ እንዲሁም የማህበሩ አባልት በንግድ ህጉ አንቀጽ 526 የተጠበቀላቸዉን መብት በአከበረ መልኩ የማህበሩ አባላት ስበሰባ ፍርድ ቤቱ በሚመድበዉ ባለሙያ ጥሪ ተድርጎ ለ2ኛ ተከሳሽ ማህብር ገለልተኛ ስራ አስኪያጅ ሊሾም ይገባል ተብሎ ተወሰኗል፡፡
3ኛዉን ነጥብ በተመለከተ የ2ኛ ተከሳሽ ማህበር በገለልተኛ ኦዲተር ኦዲት ተድርጎ የማያውቅ መሆኑን ግራ ቀኙ አልተካካዱም ተከሳሾችም የማህበሩ ሂሳብ በገለልተኛ ኦዲተር ሊመረመር አይገባም በሚል ያቀረቡት ክርክር የለም ተከሳሾች ያቀረቡት ክርክር ቢኖር የ2ኛ ተከሳሽ ማህበር ሂሳብ መመርመር ያለበት ማህበሩ ከተመሰረተበት ከ2001 ዓ/ም ጀምሮ ሊሆን ይገባል በማለት ነዉ ይሁን እንጂ ከሳሽ የማህበሩ ሂሳብ እንዲመረመር ዳኝነት የጠየቁት የጋራ ስራ አስኪያጅነት ስራቸዉን ካቆሙበት ከመስከረም 2009 ዓ/ም ጀምሮ በመሆኑ እንዲሁም ተከሳሾች የማህበሩ ሂሳብ ከ2001 ዓ/ም ጀምሮ እንዲመረመርላቸዉ ያቀረቡት የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ የሌለ በመሆኑ የ2ኛ ተከሳሽ ማህበር ሂሳብ ከመስከረም 2009 ዓ/ም ጀምሮ በገለልተኛ የሂሳብ ባለሙያ ኦዲት እንዲደረግ ተወስኗል፡፡
4ኛዉን ነጥብ በተመለከተ ከሳሽ ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ በ2ኛ ተከሳሽ ማህበር ወጪ የተደረገ ገንዘብ እና የተፈጸሙ ክፍያዎች ህገ ወጥ ሊባሉ ይገባል በማለት ከሳሽ ክርክር ያቀረቡ ሲሆን ተከሳሾች በበኩላቸዉ የተፈጸሙት ክፍያዎችም ሆነ ወጪ የተደረገዉ ገንዘብ ለመንግስት ከፍያ የዋለ መሆኑን ገንዘቡም ወጪ ተድርጎ ክፍያ የተፈጸመዉ ከሳሽ በፈረመዉ ሲፒዮ መሆኑን በመግለጽ ክርክር አቅርቧል፡፡
በተከሳሾች በኩል የቀረቡት ምስክሮች ከማህበሩ ሂሳብ ላይ ወጪ ተድርጎ ክፍያ ሲፈጸም የነበረዉ በከሳሽ ተፈርመዉ የተቀመጡ ሲፒዮችን በመጠቀም መሆኑን ከሳሽ በሌለ ጊዜ ሲፒዮ ፈርሞ ትቶ የሚሄድ መሆኑን 1ኛ ተከሳሽ በሌለ ጊዜ ሲፒዮ ፈርሞ ትቶ የሚሄድ መሆኑን ከሳሽ የስራ አስኪያጅነት ስራቸዉን ካቆሙ በኃላ የማህበሩ ቢሮ መጥተዉ ሲፒዮ እና ቼኮች የፈረሙ መሆኑን በነዚህ ቼኮች እና ሲፒዮች ገንዘብ ወጪ ተደርጎ የደመዉዝ፤የቫት፤የተርፍ ገብር፤የጡርታ፤ዊዝሆልዲንግ እንዲሁም የኪራይ ክፍያ የተፈጸመ መሆኑን ያስረዱ ሲሆን በከሳሽ በኩል የቀረቡት 1ኛ ምስክር ሲፒዮችንም ሆነ ቼኮቹን ከሳሽ ያልፈረመ መሆኑን የነገራቸዉ መሆኑን ገልጸዉ መመስከራቸዉ ሲታይ ምስክሯ ገንዘብ ወጪ የተደረገባቸዉን ሲፒዮች ከሳሽ ይፈረሙ አይፈርሙ የማያውቁ መሆኑን የሚያስረዳ ከመሆኑም በላይ ገንዘቡ ለምን ጥቅም እንደዋለ አላውቅም ማለታቸዉ 1ኛ ተከሳሽ ገንዘቡን ለግል ጥቅሙ ያዋለ መሆኑን አያስረዳም፡፡ከዚህም በላይ ከሳሽ በሲፒዮዎቹ ላይ ያረፉት ፊርማዎች የእኔ አይደለም ከሚሉ በቀር አግባብነት ባለዉ አካል ፊርማዉ እንዲመረመርላቸዉ አልጠየቁም፡፡ ይህ ሁሉ ሲታይ 1ኛ ተከሳሽ ከከሳሽ ጋር ታህሳስ 10 ቀን 2001 ዓ/ም እና ህዳር 13 ቀን 2001 ዓ/ም በተያዘዉ ቃለ ጉባኤ መሰረት በጋራ የ2ኛ ተከሳሽን ሂሳብ ለማንቀሳቀስ የተጣለባቸዉን ግዴታ ጥሷል ሊያስብል አይችልም ይልቁንም ወጪዎች እና ክፍያዎች የተፈጸሙት ከሳሽ በፈረሙት ሲፒዮች እና ቼኮች መሆኑ ሲታይ 1ኛ ተከሳሽ በዚህ ረግድ ጥፋት ያልፈጸሙ መሆኑን መረዳት የሚቻል ከመሆኑም በላይ ከሳሽ በደፈናዉ ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ የተደረጉ ወጪዎች እና ክፍያዎች ህገ ወጥ ይባልልኝ ከሚሉ በቀር ሀገ ወጥ ሊባሉ የሚችሉት ክፍያዎች ምን ምን እንደሆኑ እንዲሁም ህገ ወጥ የሚባልበትን ህገዊ ምክንያት ያላስረዱ ስለሆነ ከሳሽ በዚህ ረገድ የጠየቁትን ዳኝነት ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጓል፡፡
5ኛዉን ነጥብ በተመከተ ከሳሽ ባቀረቡት ክርክር የማህበሩ የአገልግሎት ክፍያ በቼክ እየተሰበሰባ በቀጥታ ወደ ማህበሩ ሂሳብ ገቢ ከተደረገ በኃላ ነዉ ከማህበሩ ሂሳብ ላይ ገንዘብ ወጪ የሚደረገዉ በመሆኑም 1ኛ ተከሳሽ የማህበሩን የአገልግሎት ክፍያ ቀጥታ በካሽ እየሰበሰቡ ወጪ አድርጓል ይህም አግባብነት የለዉም ሊባል ይገባል በማለት ክርክር ያቀረቡ ቢሆንም ከሳሽ ይህን ፍሬ ነገር በማስረጃ ያላረጋገጡ ሲሆን ተከሳሾች በበኩላቸዉ ከ2006 ዓ/ም በፊትም ሆነ በኃላ ማህበሩ የሰበሰበዉ የአግልግሎት ክፍያ ቀጥታ ወደ ባንክ ሳይገባ ለተለያዩ ወጪዎች ይውል የነበረ መሆኑን የሂሳብ አወጣጥን በተመለከተ ማህበሩ መመሪያ የሌለዉ መሆኑን እንዲሁም ወጪዎች ስራ አስኪጆቹ በፈለጊት መንግድ ወጪ ሲያደርጉ የነበረ መሆኑን ይህም የማህበሩ የተለመደ አሰራር መሆኑን የቀረቡት ምስክሮች አስርድቷል፡፡ ማህበሩ የሂሳብ አያያዘን በተመለከተ መመሪያ የሌለዉ በሆነበት ሁኔታ 1ኛ ተከሳሽ የማህበሩን የአገልግሎት ክፍያ በካሽ ሰብስቦ ቀጥታ ወጪ ማድረጉ ተገቢ አይደለም የሚባልበት ህጋዊ ምክንያት ስለሌለ ፍርድ ቤቱ በዚህ ረገድም ከሳሽ ያቀረቡትን ክርክር ውድቅ አድርጎታል፡፡
ዉሳኔ
1ኛ) ተከሳሽ ከ2ኛ ከሳሽ ማህበር የጣምራ ሥራ አስኪያጅነት ሊሻር ይገባል ተብሏል፡፡ በመሆኑም ከማህበሩ አባላት ወጪ የሆነ ገለልተኛ ባለሙያ ለ2ኛ ተከሳሽ ማህበር በስራ አስኪያጅነት እንዲሾም ታዟል፡፡
2ኛ) የምድቡ ሬጄስተራር ጽ/ቤት ከዳኛ ረዳቶች መካከል የንግድ ህግ ገንዘቤ ያለዉን የ2ኛ ተከሳሽ ማህበር አባላትን ሰብሰባ ጠርቶ ስራ አስኪያጅ የሚያስመርጥ የዳኛ ረዳት እንዲመድብ ታዟል፡፡
3ኛ) የ2ኛ ተከሳሽ ማህበር ሂሳብ ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ በገለልተኛ ኦዲተር ኦደት እንዲደረግ ስለተወሰነ የምድቡ ሬጅስተራር ጽ/ቤት ገለልተኛ ኦዲትር አንዲመብ ታዟል፡፡
3ኛ) ከሳሽ ያልተከፈላቸዉን ደመዉዝ፤የትርፍ ክፍፍል እንዲሁም በ1ኛ ተከሳሽ ጥፋት የደረሰባቸዉ ጉዳት ካለ ወደፊት ክስ አቅርበዉ የመጠየቅ መብታቸዉ ተጠብቋል፡፡
4ኛ) ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ፡፡
ትዕዛዝ
ይግባኝ ለጠየቀ ገልባጭ ይሰጥ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ፡፡
- Details
- Category: የንግድ ችሎት ውሳኔዎች
- Abyssinia Law | Making Law Accessible! By
- Hits: 4264
የመ/ቁጥር 170468
ቀን 10/4/2012 ዓ/ም
ዳኛ፡- አሸናፊ ለሜቻ
ከሳሾች፡- 1. ቢም አይቲ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግ/ማ አልቀረቡም
2. አቶ ሳሙኤል አርከበ
ተከሳሽ፡- አቶ በረከት ታደገኝ ወኪል ማንያህልሻል ንቦ ፡- ቀረቡ
መዝገቡ ለዛሬ የተቀጠረው ለምርመራ ተብሎ ሲሆን ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰቷል፡፡
ፍርድ
ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው ከሳሾች የካቲት 7 ቀን 2010 ዓ.ም አሻሽለው ያቀረቡት የክስ አቤቱታ ሲሆን ይዘቱም በአጭሩ እንደሚከተለው ነው፡፡
ተከሳሽ እና ከሳሽ በ10/03/2001 ዓ/ም በፈረምነው የመመስረቻ ጽሁፍ ቢም አይቲ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግ/ማን አቋቁመናል፤ ማህበሩም የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን የማማከር አገልግሎት እና የመረጃ ቋት ማደራጀትና የማቀናበር ስራዎችን የሚሰራ የንግድ ማህበር ነው፤ ማህበሩንም ከ25/4/2001 ዓ/ም ጀምሮ 2ኛ ከሳሽ እና ተከሳሽ ተስማምተን በጣምራ ሥራ አስኪያጅነት ስንመራ ቆይተናል፡፡ ነገር ግን ተከሳሽ ያለከሳሾች ፈቃድ የ1ኛን ከሳሽ ድህረ ገጾች እንዲስተጓጎል አድርጓል፤ 1ኛ ከሳሽ ማህበር ውል ተዋውሎ የጀመረውን የድህረገጽና የሶፍትዌር ሲስተም ዝግጅት ስራ ሳይጨርስ እንዲቋረጥና የይለፍ ኮዶችን ይዞ በመሰወር ማህበሩ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል የ1ኛ ከሳሽ ደንበኞች ያለደንበኞቹ ፈቃድ ራሱ አዲስ ወደከፈተው ተመሳሳይ ድርጅት ሰርቨር በማዞር ህግን የሚቃረን ድርጊት ፈጽሟል እንዲሁም የ1ኛ ከሳሽን ገንዘብ አባክኗል፡፡ ተከሳሽ የማህበሩ ጣምራ ሥራ ሰስኪያጅ ሆኖ ሲያገለግል ይጠቀምባቸው የነበሩ የድርጅቱ ንብረቶች ማለትም ግምቱ ብር የሆነ 18,645 /አስራ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ አርባ አምስት ብር / አዲስ ላብቶፕ እና ግምቱ ብር 7130/ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሰላሳ ብር/ ያገለገለ ላብቶፕ ተመላሽ አላደረገም እንዲሁም 1ኛ ከሳሽ ማህበር በብድር የወሰደዉን ብር 369,000.00(ሶስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ) ተመላሽ ሳያደርግ ቀርቷል፡፡ከዚህም በተጨማሪ ተከሳሽ የማህበሩ የባንክ አካውንት አንደኛው ፈራሚ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ከሀላፊነታቸው የተነሱ ሆኖ እያለ ፈራሚነታቸውን ለሌላ ሰው ለማስተላለፍ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የማህበሩን ሂሳብ ማንቀሳቀስ አልተቻለም፡፡ይህ የተከሳሽ ድርጊት 1ኛ ከሳሽ ማህበርን ችግር ላይ ጥሏል ለሠራተኞች የሚከፍለውንም ክፍያ እንዲቋረጥባቸው ሆኗል፡፡ ስለሆነም ተከሳሽ ከ1ኛ ከሳሽ ማህበር አባልነት እንዲወጣ ድርሻውንም ለ2ኛ ከሳሽ ወይም 2ኛ ከሳሽ ለሚመርጣቸው ግለሰቦች እንዲያስተላልፍ ፤የ1ኛ ከሳሽ ንብረት የሆኑትና በክሱ ላይ የተጠቀሱትን ላብቶፓች ለ1ኛ ከሳሽ እንዲያስረክብ ፤ በብድር የወሰደዉን ብር 369,000/ሦስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ብር/እንዲከፈል፤የ1ኛ ከሳሽ ማህበርን ሰነዶች በሙሉ እንዲመልስ፤ተከሳሽ ከጣምራ ስራ አስኪያጅነት ስልጣኑ እንዲነሳ የባንክ አካውንት ከማንቀሳቀስ ስልጣኑ እንዲታገድ እና ከባንክ ፈራሚነቱ እንዲነሳ፤ተከሳሽ ጣምራ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ሲያገለግል ያወቃቸውን የ1ኛ ከሳሽን ደንበኞችን ራሱ በግሉ ወዳቋቋመው ድህረገጽ/ website/ውስጥ እንዳያስገባ እንዲሁም የይለፍ ቁልፍ/pass word/ መረጃዎች እንዳይጠቀም እንዲከለከል እንዲሁም ተከሳሽ በማህበሩ ላይ የሥራ አስኪያጅ ስልጣኑን አላግባብ በመጠቀም በማህበሩ ላይ ያደረሰውን ጉዳት መጠን ተለይቶ በታወቀ ጊዜ ወደፊት ክስ የማቅረብ መብታቸው እንዲጠበቅላቸዉ እንዲወሰንላቸዉ እንዲሁም በዚህ ክስ ምክንያት የደረሰባቸዉ ወጪና ኪሳራ እንዲተካላቸዉ ዳኝነት ጠይቋል፡፡
ከሳሾች ክሱን ያስረዱልኛል ያሏቸውን የሰነድ ማስረጃዎች ከክሱ ጋር አያይዘዉ አቅርበዋል የሰዉ ምስክሮች ቆጥረዋል፡፡
ተከሳሽ በከሳሾች የቀረበዉ የክስ አቤቱታ ከነአባሪዎቹ ድርሶት የመከላከያ መልሱን መጋቢት 3 ቀን 2010 ዓ/ም ያቀረበ ሲሆን ባቀረበዉ የመከላከያ መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የፍሬ ነገር መልስ ሰጥቷል፡፡ ተከሳሽ ያቀረበዉን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ሰኔ 18 ቀን 2010 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት ብይን የሰጠበት በመሆኑ ከዚህ ማስፈር ሳያስፈልግ ታልፏል፡፡
ተከሳሽ በፍሬ ነገሩ ላይ የሰጠዉ የመከላከያ መልስ በአጭሩ 1ኛ ከሳሽ በዋነኝነት ገቢ የሚገኘበትን ኢቲዮ ቴንደር የተባለዉ ዌብሳይት ሀሳብ አመንጪ እና ዴቨሎፐር መሆናቸዉን 1ኛ ከሳሽም በዚህ የሰራ ዘርፍ ከፍተኛ ተዋቂነት ማገኘቱን ተከትሎ 1ኛ ከሳሽ ለሚሰጠው አገልግሎት የአገልግሎት ክፍያ ዋጋ ጭማሪ በማደረጋቸዉ ከ2ኛ ከሳሽ ጋር አለመገባባት ዉስጥ የገቡ መሆኑን ይህን አለመግባባት ምክንያት በማድረግ 2ኛ ከሳሽ አንድ ጊዜ በራሱ ስም ሌላ ጊዜ በአንደኛ ከሳሽ ስም እንዲሁም በማህበሩ ጠበቃ አማካኝነት ማቆሚያ የሌለው ማስፈራሪያና ዛቻ በመላኩ ተከሳሽ በፍርሀት እና በመገደድ በማህበሩ ዉስጥ ያለዉን የአክሲዮን ድርሻ በፈቃደኝነት ለመሸጥ ገልጾ የነበረ ቢሆንም በድርድር ሂደት መስማማት ላይ መድረስ ባለመቻላቸዉ ሀሳባቸዉን የቀየሩ መሆኑን፤ከሳሾች በአንድ በኩል ተከሳሽ የጣምራ ሥራ አስኪያጅነቱን በፈቃዱ ትቶ ሄዷል እያሉ በሌላ በኩል ከሥራ አስኪያጅነቱ ሊነሳ ይገባል በሚል ያቀረቡት ክርክር እርስበርሱ የሚጣርስ መሆኑን፤ተከሳሽ ከሥራ አስኪያጅነቱ እንዲነሳ የሚጠይቀውን ክስ ያቀረቡት ማህበሩና የማህበሩ ሌላኛው ሥራ አስኪያጅ እንጂ ባለአክሲዮን ባለመሆኑ በንግድ ሕጉ ቁጥር 527/5/ መሰረት ክሱ ተቀባይነት ሊኖረው የማይገባ መሆኑን በማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ ሁለቱም ባለአክሲዮኖች ሥራ አስኪያጅ እንዲሆኑ የተደረገው ለቁጥጥር አላማ በመሆኑ አንደኛው ሥራ አስኪያጅ ብቻዬን ሥራውን ልመራ ይገባል በሚል ሌላኛው ሥራ አስኪያጅ እንዲነሳለት ጥያቄ ሊያቀርብ የማይችል መሆኑን ከሳሾች ተከሳሽ ከሥራ አስኪያጅነቱ እንዲነሳ ላቀረቡት ክስ የሰጡት ምክንያት የሌለ መሆኑን ይህ ደግሞ ከንግድ ሕጉ ቁጥር 527/3/ ውጪ መሆኑን ከሳሾች ተከሳሽ ፈጽሟቸዋል ያሉትን ድርጊቶች መቼ እንዴት እንደተፈጸመ በክሱ ላይ ያልተገለጹ እና በማስረጃ ያላስደገፈ መሆኑን 2ኛ ከሳሽ ተከሳሽ ሥራውን እንዳይሰራ ይከፈለው የነበረውንም ደሞዝ እንዲቆም በማድረጉ ተከሳሽ ተገዶ የመሰረተው ኩባንያ የጨረታ መረጃ ሥራዎች ላይ ያልተሰማራ እና የመሰማራት ሀሳብ የሌለው በመሆኑ የጥቅም ግጭት የሌለ መሆኑን፤የይለፍ ቃሉን/ pass word/ በተመለከተ 2ኛ ከሳሽ ስለቀየራቸው ተከሳሽ በድህረገፁ/website/ላይ ለመጠቀም የሚችልበት ሁኔታ የሌለ መሆኑን፤1ኛ ከሳሽ ጥሬ ገንዘብን በተመለከተ ያቀረበው ክስ የትርፍ ክፍፍል በአግባቡና በስርዓቱ ተከናውኖ የማያውቅ ስለሆነ በማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የትርፍ ክፍፍል እስኪካሄድ ድረስ ባለአክሲዮኖች ከትርፍ ላይ የሚታሰብ ገንዘብ እንዲወስዱ ሁለቱም ባለአክሲዮኖች ባደረጉት ስምምነት የወሰዱት ገንዘብ እንጂ የብድር ገንዘብ አለመሆኑን ብድር ተብሎ የተመዘገበዉም ለሂሳብ አያያዝ ተብሎ መሆኑን፤ብር 230,000/ሁለት መቶ ሠላሣ ሺህ ብር/የወሰዱትም ከማህበሩ ትርፍ ታሳቢ የሚደረግ መሆኑን፤ላብቶፖቹ ተከሳሽ ባለአክሲዮን በመሆኑ ለግል አግልግሎት እንዲጠቀምባቸው ተገዝተው የተሰጡት ንብረት እንጂ ተመላሽ የሚሆኑ አለመሆናቸዉን፤የማህበሩ 50/100 ባለድርሻ በመሆናቸዉ የባንክ አካውንት የማንቀሳቀስ ወይም ፈራሚነት ሥራውን ሊያቆሙ የማይገባ መሆኑን የ1ኛ ከሳሽ ምንም ሰነድ በእጃቸዉ የሌለ መሆኑን ገልጸዉ የከሳሾች ክስ ውድቅ እንዲደረግ ዳኝነት ጠይቋል፡፡
ተከሳሽ ክሱን ይከላከልልኛል ያላቸውን የሰነድ ማስረጃዎች ከመልሱ ጋር አይይዞ አቅርቧል የሰዉ ምስክሮች ቆጥሯል፡፡
ፍርድ ቤቱ ታህሳስ 22 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት ክስ የሰማ ሲሆን በዚህም መሰረት ከሳሾች ባቀረቡት ክርክር የንግድ ህጉ አንቀጽ 261 እና 279 ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ላይ ተፈጻሚነት ያላቸዉ ድንጋጌዎች በመሆናቸዉ ተከሳሽ ከ1ኛ ከሳሽ ማህበር አባልነት ሊሰናበት የሚገባ መሆኑን የማህበሩን ሒሣብ ማንቀሳቀስ ያልተቻለ በመሆኑ፤2ኛ ከሳሽ እና ተከሳሽ አብረዉ መስራት የማይችሉ በመሆኑ፤ተከሳሽ ተመሳሳይ ድርጅት ከፍተዉ ከ1ኛ ከሳሽ ጋር የጥቅም ግጭት የፈጠሩ በመሆኑ፤1ኛ ከሳሽ የሚሰራዉን ስራ በድብቅ ከ2005 ዓ/ም ጀምሮ ሲሰራ የነበረ በመሆኑ የ1ኛ ከሳሽን ደንበኞች እራሳቸዉ ወደ አቋቋሙት ድርጅት በመውሰዳቸዉን የ1ኛ ከሳሽ ማህብር ደንበኞች መረጃ ከሰርቨር ላይ እንዲጠፋ ያደረጉ በመሆኑ፤የማህበሩንም ፓስወርድ በመደበቅ ድንበኞች እንዲሻሹ ያደረገ በመሆኑ ተከሳሽ ከጣምራ ስራ እኪያጅነት ሊሻሩ የሚገባ መሆኑን በመግልጽ ክሳቸዉን አጠናክረዉ ሲከራክሩ ተከሳሽ በበኩላቸዉ 2ኛ ከሳሽ ላለፉት ሁለት ዓመታት ከ1ኛ ከሳሽ ማህበር ወጪ ያደረጉት ክፍተኛ ገንዘብ እንዳይታወቅባቸዉ በማሰብ መሆኑን፤ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህብር አባል የሆነ ሌላኛዉ አባል ከማህበሩ እንዲወጣለት ክስ ማቅርብ የማይችል መሆኑን የንግድ ህጉ አንቀጽ 261 እና 279 ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ላይ ተፈጻሚነት የሌላቸዉ መሆኑን እነዚህ ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት አላቸዉ ቢባል ሊተገበሩ የሚችሉት ማህበር ይፈረስ በሚል የተጠየቀ ዳኝነት ሲኖር መሆኑን ነገር ግን ማህበር ይፈረስ የሚል ዳኝነት በዚህ መዝገብ ያልተጠየቀ መሆኑን፤በማህበሩ መመሰረቻ ጽሁፍም ሆነ በመተዳደሪያ ደንቡ አንድ አባል ተገዶ ሊወጣ የሚገባበት አግባብ ያልተቀመጠ መሆኑን ከ2ኛ ከሳሽ ጋር የጋራ ሥራ አስኪያጅ ሆነዉ የተሰየሙ በመሆኑ ከሥራ አስኪጅነት ከተሻሩ ሁለቱም ሊሻሩ የሚገባ መሆኑን የ1ኛ ከሳሽ ዌብሳይት የተፈጠረዉ በተከሳሽ መሆኑን፤ድርጅት ያቋቋሙት ሥራ ከአቆሙ ከአንድ ዓመት በኃላ መሆኑን ይህ የተቋቋመዉ ድርጅትም የኢትዮ ቴንደር ሥራ የማይሰራ መሆኑን የሚሰራዉም የዌብሳይ ዴቨሎፕመንት መሆኑን ድርጅቱም የተዘጋ መሆኑን የሰበሰበዉ ብር 3,000.00(ሦስት ሺህ ብር) መሆኑን ይህም ገንዘብ ለባለጉዳዩ ለቢታኒያ ኃ/የተወ/የግል ማህበር ተመላሽ የተደረገ መሆኑን በመገልጽ የመከላከያ መልሳቸዉን በማጠናክር ክርክራቸዉን አቅርቧል፡፡
የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተዉን ሲመስል ፍርድ ቤቱም ቀጠሎ የተመለከቱትን ጭብጦች በመያዝ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሯል፡፡
1ኛ) ተከሳሽ ከ1ኛ ከሳሽ ማህበር ሊወጣ ይገባል ወይስ አይገባም?
2ኛ) ተከሳሽ ከ1ኛ ከሳሽ ማህብር የጣምራ ስራ አስኪያጅነት ሊሻር ይገባል ወይስ አይገባም?
3ኛ) ተከሳሽ በክሱ ላይ የተጠቀሱትን ላፕቶፖች ለ1ኛ ከሳሽ ሊያስረክብ ይገባል ወይስ አይገባም?
4ኛ) ተከሳሽ የ1ኛ ከሳሽ ማህበርን ሰነዶች ሊያስረክቡ ይገባል ወይስ አይገባም?
5ኛ) ተከሳሽ ከ1ኛ ተከሳሽ ማህበር በበድር ወሰደዋል የተባለዉን ብር 369,000.00(ሶስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ) ለ1ኛ ከሳሽ ሊክፍሉ ይገባል ወይስ አይገባም?
6ኛ) ተከሳሽ የ1ኛ ከሳሽ ማህበርን የባንክ ሂሰብ እንዳያንቀሳቀስ ሊከለከል ይገባል ወይስ አይገባም እንዲሁም ተከሳሽ ከባንክ ፈራሚነት ሊነሳ ይገባል ወይስ አይገባም?
7ኛ) ተከሳሽ የ1ኛ ከሳሽ ስራ አስኪያጅ ሆኖ ሲያገለግል ያወቃቸዉን የ1ኛ ከሳሽ ድህረ ገጽ ዉስጥ አንዳይገባ፤የይለፍ ቁጥሩን እና መረጃዎችን አንዳይጠቀም ሊከለከል ይገባል ወይስ አይገባም?
8ኛ) ተከሳሽ ያደረሰዉ ጉደት መጠን በተመለከተ ለከሳሾች ወደፊት ክስ የማቅርብ መብታቸዉ ሊጠበቅ ይገባል ወይስ አይገባም?
የመጀመሪያዉን ነጥብ በተመለከተ 1ኛ ተከሳሽ ማህበር ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሲሆን ይህን ማህበር የሚገዛዉ የንግድ ህጉ ክፍል ከአንቀጽ 510-543 ስር የተገለጹት ድንጋጌዎች ናቸዉ፡፡ እነዚህ ደንጋጌዎች ደግሞ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አባል የሆነ ሰዉ ከማህበሩ ሊሰናበት የሚችልበትን አግባብ አያስቀምጡም፡፡በርግጥ ሃላፊነቱ የተወሰነ ማህበር የሽርክና ማህበር እና የአክሲዮን ማህበራት የተቀላቀለ ባህሪ ያለዉ ማህበር መሆኑን ከላይ ከተጠቀሱት ድንጋጌዎች መረዳት ይቻላል፡፡
በሽርክና ማህበራት ዉስጥ የአባሉቱ ማንነት እና ባህሪ (personality of members) ለማህበሩ ቀጣይነት ዋሳኝ ነዉ ይህም የሆነዉ የሽርክና ማህበራት የሰዎች ስብስብ (association of persons) ስለሆነ ሲሆን የአክሲዮን ማህበር ዉስጥ ደግሞ የአባላቱ ማንንትም ሆነ ባህሪ ለማህበሩ ቀጣይነት ጠቃሚ አይደለም ይህም የሆነበት ምክንያት የአክሲዮን ማህበራት የካፒታል ስብስብ(association of capital) በመሆናቸዉ ነዉ፡፡ ከዚህ አንጻር ተከሳሽ ከማህበሩ ሊሰናበት ይገባል ወይስ አይገባም የሚለዉን ነጥብ ሃላፊነቱ የተወሰነ ግል ማህበር ያለዉን የተቀላቀለ ባህሪ መሰረት በማድረግ መመርመር ያስፈልጋል፡፡
ከሳሾች ተከሳሽ ከማህበሩ እንዲሰናበት መሰረት አድርገዉ የሚከራክሩት የንግድ ህጉን አንቀጽ 261 እና 279 ሲሆን እነዚህም ድንጋጌዎች እንደየቅደመተከተላቸዉ የሚገኙት በንግድ ህጉ ስለ ተራ ሽርክና እና ስለ እሽሙር ማህበር በሚደነግገዉ የህግ ክፍል ነዉ፡፡ የነዚህንም ድንጋጌዎች ይዘት ስንመለከተ ፍርድ ቤት በቂ ምክንያት ሲኖር እንዱን ማህበርተኛ ከማህበሩ እንዲወጣ ሊፈርድ እንደሚችል ያስቀምጣል፡፡እነዚህ ድንጋጌዎችም የሚገኙት ስለ ተራ የሽርክና ማህበር እና ስለ እሽሙር ማህበር በሚደነግገዉ የህግ ክፍል እንደመሆኑ መጠን እና ስለ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በሚደነግገዉ የንግድ ህጉ ክፍል ተጠቃሾቹ ድንጌዎች አገልግሎት ላይ ሊውል እንደሚችል የተመለከተ ገልጽ ነገር ባለመኖሩ ደንጋጌዉ በሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ላይ ተፈጻሚነት የሌለዉ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡በመሆኑም በንግድ ህጉ አንቀጽ 261 የተራ ሽርክና ማህብርተኞችን እና በአንቀጽ 279(1) ላይ የእሽሙር የሽርክና ማህበር አባልን በፍርድ ቤት ከሽርክና ማህበር እንዲወጣ ለመወሰን የሚያስችል በግልጽ ተደንግጎ እያለ ስለ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አባልን ፍርድ ቤት ከአባልነት እንዲሰርዝ ለመወሰን እንደሚቻል ያለመደነገጉ ተጠቃሾቹ ደንጋጌዎች በሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ላይ ተፈጻሚነት የሌላቸዉ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ከዚህም በተጨማሪ በ1ኛ ከሳሽ ማህበር የመመሰረቻ ጽሁፍም ሆነ የመተዳደሪያ ደንብ የማህበሩ አባል ከማህበሩ አባል ሊሰናበት የሚችልበትን አግባብ አልተቀመጠም፡፡ እንዲሁም ተራ የሽርክና ማህበር በንግድ ህጉ አንቀጽ 5 ስር በተዘረዘሩት የንግድ ስራዎች ላይ መሳተፍ እንደማይችል እንዲሁም ተራ የሽርክና ማህበር የንግድ ማህበራት ባህሪ የሌለዉ መሆኑን ከንግድ ህጉ አንቀጽ 213 እና 227 መረዳት የሚቻል ሲሆን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዓላማዉ ምንም ቢሆን የንግድ ማህበር መሆኑ በንግድ ህጉ አንቀጽ 10(2) ስር የተቀመጠ በመሆኑ እና ሁሌም የንግድ ስራ የሚስራ ከመሆኑ አንጻር እና ተራ የሽርክና ማህበር እንደ ንግድ ድርጅት የማይቆጠረ ከመሆኑ አንጻር በተራ የሽርክና ማህበር ስር የተደነገገን ደንጋጌ አመሳሰሎ(analogy) በግልጽ የንግድ ማህበር መሆኑ የተቀመጠ የንግድ ማህበር ላይ ተፈጻሚ ማድረግ አግባብነት የለዉም፡፡ ስለሆነም ተከሳሽ ከ1ኛ ከሳሽ ማህበር ሊሰናበት የሚችልበት የህግ አግባብ የሌለ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ የከሳሾች በዚህ ረገድ የጠየቁትን ዳኝነት ውድቅ አድርጓል፡፡
2ኛዉን ነጥብ በተመለከተ ኃ/የተ/ግ/ማህበር በአንድ ወይም ብዙ ሥራ አስኪያጆች ሊተዳደር አንደሚችል እንዲሁም ሥራ አስኪያጅ ከማህበሩ አባላት ወይም ከማኅበረተኞች ውጭ ሊምረጥ እንደሚችሉ የንግድ ሕጉ አንቀጽ 525 እና 526 ይደነግጋል፡፡ አሁን በተያዘው ጉዳይ ተከሳሽ የ1ኛ ከሳሽ ማህበር ጣምራ ስራ አስኪያጅ ሆነዉ የተሰየሙ መሆኑን ማህበሩ ህዳር 13 ቀን 2001 ዓ/ም የያዘዉ ቃለ ጉባኤ ያስረዳል፡፡ይህ ቃለ ጉባኤም የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ አካል እንደሆነ በቃለ ጉባኤዉ ላይ ተመልክቷል፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ተከሳሽ በማህበሩ መመሰረቻ ጽሁፍ የጣምራ ስራ አስኪያጅ ሆነዉ የተሾሙ መሆኑን መገንዘብ የሚቻል ሲሆን በማህበሩ የመመስረቻ ጽሁፍ የተሾመ ሥራ አስኪያጅ ከሥራ አስኪያጅ ስልጣኑ ሊሻር የሚችለዉ በንግድ ህጉ 527(1) እና 536(2) መሰረት ከማህበሩ ባለአክሲዮኖች መካከል በሶስተኛ አራተኛ ድምጽ ባላቸዉ ባለአክሲዮኖች ሲደገፍ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ ይህ ድንጋጌም ተፈጻሚነት ያለዉ የማህበሩን ሥራ አስኪያጅ በጠቅላላ ጉባኤ ለመሻር በቀረበ ጊዜ ሲሆን በሌላ በኩል እንድ ስራ አስኪያጅ በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ የተሾመ ቢሆንም ስራ አስኪያጁ ከስልጣኑ እንዲነሳ ሊያደረጉ የሚችሉ ጥፋቶች እስካሉ የማህበሩ አባላት ስራ አስኪያጁ በፍርድ ቤት ዉሳኔ እንዲሻር መጠየቅ እንደሚቻሉ በንግድ ህጉ አንቀጽ 527(5) ተመልክቷል፡፡ ይህ ድንጋጌ የማህበሩን ሥራ አስኪያጅ ከሥራ አስኪያጅነት ለማንሳት የሚስችሉ ጥፋቶችን በዝርዝር አለስቀመጠም፡፡ እንዲህ በሆነ ጊዜ ደግሞ አንድ የማህበር ስራ አስኪያጅ በህግ ፤በማህበሩ የመመስረቻ ጽሁፍ እንዲሁም መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ግዴታዉን ካልተወጣ ጥፋት እንደፈጸመ የሚቆጠር መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡
ከሳሾች ተከሳሽ ከጣምራ ስራ አስኪያጅነቱ ሊሻር ይገባል በማለት በዋንኝነት የሚከራክሩት ተከሳሽ ያለከሳሾች ፈቃድ የ1ኛን ከሳሽ ድህረ ገጾች እንዲስተጓጎል አድርጓል፤1ኛ ከሳሽ ማህበር ውል ተዋውሎ የጀመረውን የድህረገጽና የሶፍትዌር ሲስተም ዝግጅት ስራ ሳይጨርስ እንዲቋረጥና የይለፍ ኮዶችን(Password) ይዞ በመሰወር ማህበሩ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል በማለት ሲሆን ተከሳሽ ይህን ድርጊት ስለመፈጸሙ በበቂ ማስረጃ አላስረዱም፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ከሳሾች ይህን ምክንያት በመጠቀስ ተከሳሽ ከጣምራ ስራ አስኪያጅነቱ ሊነሳ ይገባል በማለት ያቀረቡትን ክርክር ፍርድ ቤቱ አልተቀበለዉም፡፡ሌላዉ ከሳሾች ተከሳሽ ከጣምራ ሥራ አስኪያጅነቱ ሊሻር ይገባል በማለት ያቀረቡት ምክንያት ተከሳሽ የ1ኛ ከሳሽ ደንበኞች ያለደንበኞቹ ፈቃድ ራሱ አዲስ ወደከፈተው ተመሳሳይ ድርጅት ሰርቨር በማዞር ህግን የሚቃረን ድርጊት ፈጽሟል በማለት ነዉ፡፡
የሥራ አስኪያጅ መብቶችና ግዴታዎች ሰለ ውክልና በተወሰኑት ደንጋጌዎች መሰረት የሚመራ መሆኑን አግባብነት ካላቸዉ የንግድ ህጉ ድንጋጌዎች ማለትም ከአንቀጽ 33፤289፤292፤355 እና 364 መረዳት የሚቻል ሲሆን እነዚህ ድንጋጌዎች በማመሳሰል(by analogy) ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ላይ ተፈጻሚነት ያላቸዉ መሆኑ አከራካሪ አይደለም፡፡ከዚህ አንጻር አንድ የማህበር ስራ አስኪያጅ የሆነ ግለሰብ ለማህበሩ በቅን ልቦና ስራዉን መሰራት ያለበት መሆኑን እንዲሁም የጥቅም ግጭት ማሰወገድ ያለበት መሆኑን ከላይ ከተጠቀሱት የንግድ ህግ ድንጋጌዎች መረዳት የሚቻል ከመሆኑም በላይ ከፍ/ሕ/ቁ 2208 እና 2209 መገንዘብ ይቻላል፡፡ በተያዘዉ ጉዳይ ተከሳሽ የ1ኛ ከሳሽ ማህበር ጣምራ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ሳለ ከ1ኛ ከሳሽ ማህበር ጋር ተመሳሳይ ሥራ የሚሰራ ቢቲኤ ቴክኖሎጂ የተባለ ማህበር መሰርቶ ሲሰራ የነበረ መሆኑን ተከሳሽ እራሱም ካለመካዱም በላይ በከሳሾች በኩል የቀረቡት ማስረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ ይህም የተከሳሽ ተግባር በንግድ ህጉ አንቀጽ 292፤355 እና 364 እንዲሁም በፍ/ሕ/ቁ 2208 እና 2209 የተጣለበትን ህጋዊ ግዴታ የጣሰ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡ከዚህም በተጨማሪ ተከሳሽ የ1ኛ ከሳሽ ደንበኛ የሆነዉን ቢቲኒያ አስጎብኚና የጉዞ ወኪል ኃ/የተ.የግል ማህበርን ድረ ገጽ እራሱ ወደ መሰረተዉ ቢቲኤ ቴክኖሎጂ ያዛወረ በመሆኑ ቢታኒያ አስጎብኚና የጉዞ ወኪል ከ1ኛ ከሳሽ ሲያገኝ የነበረዉ አገልግሎት የተቋረጠ መሆኑን፤ኢሜሎችን በአገባቡ መከታተል እና መመለስ ያልቻለ መሆኑን ድረገጹም ተከሳሽ ወደ መሰረተዉ ማህበር የተዛወረዉ ያለ ፈቃዳኛዉ መሆኑን ገለጸዉ ይህም እንዲሰተካከልላቸዉ 1ኛ ከሳሽን የጠየቁ መሆኑን የቀረበዉ ማስረጃ ያስረዳል እንዲሁም ተከሳሽ 1ኛ ከሳሽ የሚሰጠዉን አገልግሎት ማለትም የዌብሳይት ሆስቲንግ አገልግሎት በመስጠት ከላይ ከተገለጸዉ የ1ኛ ከሳሽ ደንበኛ ብር 3,000.00(ሦስት ሺህ ብር) የተቀበለ መሆኑን በማስረጃነት የቀረበዉ ደረሰኝ ያስረዳል ተከሳሽ ይህን የገንዘብ መጠን ተመላሽ ያደረገ መሆኑን በመግለጽ ክርክር ያቀረበ ቢሆንም እራሱ በሰጠዉ የምስክርነት ቃል ገንዘቡን ተመላሽ ያለደረገ መሆኑን መስክሯል እንዲሁም ተከሳሽ ማህበሩ አገልግሎት በመስጠት የሰበሰበዉን ገንዘብ ወደ ማህበሩ ሂሳብ ገቢ ሳያደርጉ ስራቸዉን ጥለዉ የሄዱ መሆኑን ተከሳሽ ካለመካዳቸዉም በላይ የከሳሾች ምስክሮች አስረድቷል፡፡ከላይ ከቀረቡት ማስረጃዎችም ተከሳሽ ጣምራ ስራ አስኪያጅ ሆነዉ ሳለ ከ1ኛ ከሰሽ ማህበር ጋር የጥቅም ግጭት የፈጠሩ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ደምድሟል፡፡ በሌላ በኩል ተከሳሽ የመሰረተዉን ቢቲኤ ቴክኖሎጂ የተባለዉን ማህበር ክሱ ከቀረበ በኃላ ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ/ም ከንግድ መዝገባ የተሰረዘ ቢሆንም ተከሳሽ ከ1ኛ ከሳሽ ማህበር ጣምራ ስራ አስኪያጅ ሆነዉ የጥቅም ግጭት የፈጠሩ መሆኑን የሚያስቀር አይደለም እንዲሁም ተከሳሽ የመሰረትኩት ማህበር 1ኛ ከሳሽ ማህበር ከሚሰራዉ ሥራ ጋር የሚገናኛ አይደለም በማለት ያቀረቡት ክርክር ከ1ኛ ከሳሽ ማህበር መመሰረቻ ጽሁፍ ለመመልከት እንደሚቻለዉም ሆነ 1ኛ ከሳሽ በተግባር የሚሰረዉ ሥራ በምስክሮች ከተረጋገጠዉ አንጻር እንዲሁም ተከሳሽ ለመሥራት በኢንተርኔተ ሲያሰተዋውቃቸዉ የነበሩት ስራዎች በ1ኛ ከሳሽ የሚሰሩ ሥራዎች ናቸዉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ተከሳሽ ጣመራ ሥራ አስኪያጅ ሆነዉ የተሾሙት ለቁጥጥር መሆኑን በመገልጽ ክርክር አቅርቧል፡፡ለአንድ ማህበር ጣምራ ሥራ አስኪያጅ የሚሾመዉ በአብዛኛዉ ለቁጥጥር ዓለማ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ይገነዘባል ይሁን እንጂ ከጣምራ ሥራ አስኪጆቹ መካከል 1ኛዉ ጣምራ ሥራ አስኪያጅ በህግ የተጣለበትን ግዴታ ያልተወጣ እንደሆነ ከሥራ አስኪጅነት እንዳይሻር የሚያስቀር አይደለም እንዲሁም ሌላኛዉ ጣምራ ሥራ አስኪያጅ የማህበሩ አባል እስከሆነ ድረስ ጥፋት ፈጸሚዉ ሥራ አስኪያጅ ከስራ አስኪያጅነቱ እንዲሻር የመጠየቅ መብቱን የሚያስቀር አይደለም፡፡በመሆኑም ተከሳሽ 2ኛ ከሳሽ ጣምራ ሥራ አስኪያጅ ስለሆነ ከጣምራ ሥራ አስኪያጅነት እንዲሻር ዳኝነት ሊጠይቅ አይገባም በማለት ያቀረቡትን ክርክር ፍርድ ቤቱ አልተቀበለዉም፡፡ ተከሳሽ 1ኛ ከሳሽ ወኪል እንደ መሆናቸው ለማህበሩ ጥቅም ሊሰጥ የሚችል ተግባር መፈጸም ብቻ ሲገባቸው ነገር ግን ተከሳሽ ከዚህ በተቃራኒ ማህበሩን አደጋ ላይ በሚጥል ተግባር ሲፈጽሙ እንደ ነበር ከቀረበው ማስረጃ መመልከት ይቻላል፡፡ስለሆነም ተከሳሽ ከ1ኛ ከሳሽ ማህበር የጣምራ ሥራ አስኪያጅነት ሊሻር ይገባል በማለት ፍርድ ቤቱ ፍርድ ሰጥቷል፡፡ይሁን እንጂ የማህበር ሥራ አስኪያጆች እንደ ማህበሩ ወኪል የሚቆጠሩ መሆኑን የንግድ ህጉ አንቀጽ 33 የሚደነግግ በመሆኑ፤የንግድ ህጉ ከአንድ በላይ የሆኑ ሥራ አስኪያጆች ማህበሩን የሚመሩ እና የተሰጣቸዉም ስልጣን በጋራ አንድ አይነት ጉዳይ ለመከናወን እንዲችሉ ከሆነ የአንዱ ሥራ አስኪያጅ ከሥራ አሰኪያጅነት መሻር ያላዉን ዉጤት የማያሰቀምጥ ስለሆነ በንግድ ህጉ አንቀጽ 1 በተደነገገዉ መሰረት የፍ/ህ/ቁ 2231ን መጠቀም አሰፈላጊ ነዉ፡፡ከዚህ አንጻር ተከሳሽ እና 2ኛ ከሳሽ የማህበሩን የባንክ ሂሳብ በጋራ ለመከፈት፤ለማንቀሳቀስ፤ለመዘጋት የማህበሩን ንብረት በዋስትና ለማሲያዝ ከባንክም ሆነ ከድርጅት ገንዘብ በብድር ለመውሰድ በጣምራ እንዲሰሩ የተሰየሙ መሆኑን ማህበሩ ታህሳስ 10 ቀን 2001 ዓ/ም እና ህዳር 13 ቀን 2001 ዓ/ም ከያዘዉ ቃለ ጉባኤ መረዳት የሚቻል ሲሆን በፍ/ሕ/ቁ 2231(1) ድግሞ ከአንድ በላይ የሆኑ ተወካዮች ተመሳሳይ ጉዳይ በጋራ እንዲያከናውኑ ስልጣን ተሰጥቷቸዉ እያለ አንደኛዉ የተሰጠዉን ስልጣን መከናወን እንዳይችል ከተደረገ ለሌላኛዉም ወኪል የተሰጠዉ ስልጣን ቀሪ እንዲሆን የተመለከተ ስለሆነ ተከሳሽ ከጣምራ ሥራ አስኪያጅነቱ በመሻሩ 2ኛ ከሳሽ ከተከሳሽ ጋር በጣምራ የተሰጠዉን ስልጣን ለብቻዉ ለማከናወን አያስችለዉም፡፡
3ኛዉን ነጥብ በተመለከተ ተከሳሽ በክሱ ላይ የተጠቀሱትን አዲስ ላፕቶፕ ግምቱ ብር 18,645 (አስራ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ አርባ አምስት) የሆነ እና ግምቱ ብር 7,130 የሆነ ያገለገለ ላፕቶፕ) ከ1ኛ ከሳሽ ማህበር የወሰደ መሆኑን አልካደም ተከሳሽ ያቀረቡት ክርክር ቢኖር ላፕቶፖቹ ከማህበሩ የተሰጡኝ ለግል አገልግሎት ነዉ በማለት የተከራከሩ ቢሆንም ይህን በማስረጃ አላረጋገጡም ከማህበሩ የጣምራ ሥራ አሰኪያጅነትም ስልጣን እንዲሻር የተወሰነ ስለሆነ እነዚህን ንብረቶች የማያስረክበበበት ህጋዊ ምክንያት የለም፡፡ በመሆኑም ተከሳሽ በክሱ ላይ የተጠቀሱትን ላፕቶፖች በአይነት እንዲያስረክብ ወይንም ግምታቸዉን እንዲከፍል ተወስኗል፡፡
4ኛዉን ነጥብ በተመለከተ ከሳሾች ተከሳሽ የ1ኛ ከሳሽ ማህበር ሰነዶችን እንዲያስረክበን ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት የጠየቁ ቢሆንም በተከሳሽ እጅ የሚገኙት ሰነዶች ምን ምን እንደሆኑ ያቀረቡት ዝርዝር የለም እንዲሁም የ1ኛ ከሳሽ ማህበር ሰነዶች በተከሳሽ እጅ የሚገኙ ስለመሆኑም በማስረጃ አላረጋገጡም፡፡ ስለሆነም ከሳሾች በዚህ ረገድም ያቀረቡትን ክርክር ፍርድ ቤቱ አልተቀበለዉም፡፡
5ኛዉን ነጥብ በተመለከተ ተከሳሽ ከ1ኛ ከሳሽ ማህበር በብድር ብር 369,000.00(ሶስትመቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ብር) ወስዷል በመሆኑም ይህን የበድር ገንዘብ ተመላሽ ያላደረገ ስለሆነ ተመላሽ እንዲያደርግልን ይወሰንልን በማለት ጠይቋል፡፡ ተከሳሽ በበኩሉ ከ1ኛ ከሳሽ የተበደሩት የብድር ገንዘብ የሌለ መሆኑን ከ1ኛ ከሳሽ የወሰዱት ገንዘብም በብድር ተብሎ የተመዘገበዉ ለሂሳብ አያየዝ እንዲያመች ተብሎ ከሚደረሳቸዉ የትርፍ ክፍያ ላይ የተከፈላቸዉ ክፍያ መሆኑን ገልጸዉ ክርክራቸዉን አቅርቧል፡፡
በፍ/ህ/ቁ 2472 እንደተደነገገዉ በብድር የተሰጠዉ ገንዘብ ከ500 የኢትዮጵያ ብር በላይ ሲሆን የብደሩን ውል በጽሁፍ ወይም በፍርድ ቤት በተደረገ የእምነት ቃል ወይም መሐላ ካልሆነ በቀር ለማስረዳት እንደማይቻል እንዲሁም ለብድር ውል ማናኛቸዉም ሌላ አይነት ማስረጃ ለማቅርብ እንደማይቻል ተመልክቷል፡፡ከዚህ አንጻር የተያዘዉን ጉዳይ ስንመለከተ ተከሳሽ ከከሳሽ ጋር የብድር ውል ያለዉ ስለመሆኑ ክዶ የተከራከረ ከመሆኑ አንጻር ከሳሽ ከተከሳሽ ጋር የብድር ውል ግኑኝነት ያለዉ ስለመሆኑ የማስረዳት ሸክም አለበት፡፡ይህ ከሆነ ደግሞ ከሳሽ የጠየቀዉ ከብር 500 ብር(አምስት መቶ ብር) በላይ የብድር ገንዘብ ስለሆነ ከተከሳሽ ጋር የፈጸመዉን የብድር ውል ከላይ በተጠቀወሰዉ ድንጋጌ መሰረት በማስረጃነት ሊቀርብ ይገባል፡፡ይሁን እንጂ ከሳሽ በማስረጃነት ያቀረበዉ በቀን 4/12/2007 ዓ/ም የገንዘብ መከፈያ በሚል ሰነድ ላይ የተከፈለበት ምክንያት የባለአከሲዮን ብድር በሚል ተከሳሽ ብር 24,000.00(ሃያ አራት ሺህ ብር) የተከፈለዉ መሆኑን የሚገለጽ፤በቀን 26/7/2008 ዓ/ም የጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ በሚል ብር 40,000.00(አርባ ሺህ ብር) ለባለአክሲዮን ብድር ተብሎ ለተከሳሽ የተከፈለበትን ደረሰኝ፤በቀን 7/6/2008 ዓ/ም ብር 75,000(ሰባ አምስት ሺህ ብር) ብድር በሚል ለተከሳሽ የተከፈለበትን ደረሰኝ እንዲሁም በቀን 10/1/2009 ዓ/ም ለተያዥ ዲቪደንድ በሚል ለተከሳሽ ብር 230,755(ሁለት መቶ ሰላሳ ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ አምስት) የተከፈለበተን ደረሰኝ ነዉ፡፡እነዚህ ማስረጃዎች ድግሞ በከሳሽ እና በተከሳሽ መካከል የብድር ውል ግኑኝነት ስለመኖሩ እንዲሁም የብድር ውል ሰለመኖሩ አያስረዱም፡፡በመሆኑም 1ኛ ከሳሽ ተከሳሽ በብድር የወሰደዉን ብር 369,000.00(ሶስት መቶ ስልሳ ዘጠን ሺህ ብር) እንዲወሰንልኝ በማለት ያቀረቡት ክርክር አግባብነት ባለዉ(የብድር ውል) ማስረጃ ያልተደገፈ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል፡፡
6ኛዉን ነጥብ በተመለከተ ተከሳሽ ከ1ኛ ከሳሽ ማህበር የጋራ ሥራ አስኪያጅነት እንዲሻሩ በተራ ቁጥር 1 በተያዘዉ ጭብጥ የተወሰነ ስለሆነ ተከሳሽ የ1ኛ ከሳሽን የባንክ ሂሳብ እንዳያንቀሳቅሱ እንዲሁም ከ1ኛ ከሳሽ ማህበር የባንከ ፈራሚነት እንዲነሱ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡
7ኛዉን ነጥብ በተመለከተ ተከሳሽ ከ1ኛ ከሳሽ ማህበር የጣምራ ሥራ አስኪያጅነት የተሻረ ሰለሆነ እና የ1ኛ ከሳሽ ማህበርን ዌብሳይት የሚገባበት ህጋዊ ምክንያት ስለሌለ ተከሳሽ የ1ኛ ከሳሽ ማህበር ዌብሳይት ዉስጥ እንዳይገባ፤የይለፍ ቁጥር እና መረጃዎችን እንዳይጠቀም ተብሎ ተወስኗል፡፡
ዉሳኔ
1ኛ) ተከሳሽ ከ1ኛ ከሳሽ ማህበር ሊሰናበት የሚችልበት የህግ አግባብ የለም ተብሎ ተወሰኗል፡፡
2ኛ) ተከሳሽ ከ1ኛ ከሳሽ ማህበር የጣምራ ሥራ አስኪያጅነት ሊሻር ይገባል ተብሏል፡፡
3ኛ) ተከሳሽ አዲስ ላፕቶፕ ግምቱ ብር 18,645 (አስራ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ አርባ አምስት) የሆነ እና ግምቱ ብር 7,130 የሆነ ያገለገለ ላፕቶፕ ለ1ኛ ከሳሽ ማህበር በአይነት ያስረከክብ ወይንም ግምቱን ይክፈል ተብሏል፡፡
4ኛ) ተከሳሽ የ1ኛ ከሳሽ ማህበር ዌብሳይት ዉስጥ እንዳይገባ፤የይለፍ ቁጥር እና መረጃዎችን እንዳይጠቀም ተብሎ ተወስኗል፡፡
5ኛ) ተከሳሽ የ1ኛ ከሳሽን የባንክ ሂሳብ እንዳያንቀሳቅሱ እንዲሁም ከ1ኛ ከሳሽ ማህበር የባንከ ፈራሚነት እንዲነሱ ተወስኗል፡፡
6ኛ) ከሳሾች በከሳሽ ጥፋት የደረሰባቸዉ ጉዳት ካለ ወደፊት ክስ አቅርበዉ የመጠየቅ መብታቸዉ ተጠብቋል፡፡
7ኛ) ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ፡፡
ትዕዛዝ
ይግባኝ ለጠየቀ ገልባጭ ይሰጥ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ፡፡
- Details
- Category: የንግድ ችሎት ውሳኔዎች
- Abyssinia Law | Making Law Accessible! By
- Hits: 4227