ፍቺ ከፍርድ ቤት ውጭ፡- የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔዎች አጭር ዳሰሳ

556 Downloads

ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነው ጸሀፊው በሥራ ምክንያት በሚያያቸው መዝገቦች ስር ሲገጥሙት የነበሩ ክርክሮች እንዲሁም በተለያዩ አጋጣሚዎች ከስራ ባልደረቦቹ ጋር ጋብቻ ከፍርድ ቤት ውሳኔ ውጭ በሁኔታዎች ስለሚፈርስበት አግባብ ያደረጋቸው ውይይቶች ሲሆኑ በዋነኛነት ግን የቅርብ ምክንያቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ የሰጠው ውሳኔ ነው። በፌደራሉ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 75 ስር እንደተመለከተው ጋብቻ የሚፈርስባቸው ብቸኛ ሶስት ምክንያቶች ሞት ወይም የመጥፋት ውሳኔ፤ ጋብቻ ለመፈጸም መሟላት ካለባቸው ሁኔታዎች አንዱ በመጣሱ ምክንያት ጋብቻው እንዲፈርስ ሲወሰን እንዲሁም ፍቺ መሆናቸው የተመለከተ ሲሆን በአንቀጽ 117 ስር እንደተመለከተው ደግሞ ጋብቻን በፍቺ ለማፍረስ ስልጣን የተሰጠው ለፍርድ ቤቶች ብቻ ነው።

File Name: ፍቺ ከፍርድ ቤት ውጭ፡- የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔዎች አጭር ዳሰሳ.pdf
Category: Family Law
File Size: 892.67 KB
Hits: 335 Hits
Download: 556 times
Created Date: 05-31-2024