በውርስ ሕግ አተረጓጎም ዙሪያ በተሰጡ አንዳንድ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ የሕግ ትርጎሞች ላይ የቀረበ ትችት

257 Downloads

የውርስ ሕግ አወቃቀሩ እና አደራጃጀቱን በአግባቡ ባለማጤን እንዲሁም የውርስ ሕጉ የተለያየ መልክት ያላቸውን እሳቤዎች ተመሳሳይ እና ተቀራራቢ በሚባሉ ቃላቶች በመጠቀሙ በውርስ ሕግ ላይ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሳይቀር በአንድ ጉዳይ ላይ የተለያዩ የሕግ ትርጉሞች እየተሰጠ ይገኛል፡፡ ፍርድ ቤቶች የውርስ ሕጉ አተገባበር ላይ ከሕጉ ወጥተዋል፡፡
ይህ ጽሁፍ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከውርስ ሕጉ አጠቃላይ አወቃቀር እና አደረጃጀት ወጥተው በአንደኛው የውርስ ሕግ ክፍል የተደነገገን ድንጋጌ አግባብነት ለሌለው ሌላ የውርስ ሕግ ክፍል ተግባራዊ በማድረግ አንዳንዴም በጉዳዩ ላይ ተፈጻሚነት ያላቸዉን የውርስ ሕግ ድንጋጌዎች በመተዉ አጠቃላይ የዉል ሕግ ድንጋጌዎችን መሠረት በማድረግ ገዥ ትርጉም መስጠታቸውን እና ይህም ሕጉን የተከተለ አለመሆኑን ይከራከራል፡፡እንዲሁም በዚህ ምክንየት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በራሱ ተቃራኒ እና ምክንየታዊ ያልሆኑ ውሳኔዎች እየተሰጡ መሆኑን በማሳየት የውርስ ሕጉ ሊተረጎም እና ተግባራዊ ሊሆን የሚችልበትን መንገድ ይጠቁማል፡፡

File Name: Criticism of some binding legal interpretations of the Federal Supreme Court on the interpretation of inheritance law.pdf
Category: Succession Law
File Size: 1.49 MB
Hits: 328 Hits
Download: 257 times
Created Date: 10-01-2024