የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ማውጫ ቅጽ 01-25

31665 Downloads

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሕግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ማውጫ ቅጽ 01-25

አዘጋጅ፡ - አረጋይ ገ/እግዚአብሔር (LLB, LLM) የሕግ አማካሪና ጠበቃ

የዚህ ፅሑፍ/ማውጫ ዝግጅት ዓላማ አንድ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሕግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ዝርዝር ማውጫ ሰንጠረዥ አስቀድሞ ከቅጽ 01 እስከ 16 ቀጥሎም ከቅጽ 01 እስከ 24 ተዘጋጅቶ በኢንተርኔት ጭምር የሚገኙ ቢሆንም የተዘጋጁበት አገባብ/መንገድ በጥቅል በዘርፍ ደረጃ (ለምሳሌ ውል) ስለሆነ አንድ ነገር (ለምሳሌ የሽያጭ ውል) ለመፈለግ ጥቅል ዘርፉ በሙሉ ማየት ስለሚያስፈልግ ጥቅል ዘርፉ እዳለ ሆኖ በዛ ዘርፍ ያሉ ውሳኔዎችን በንኡስ ዘርፍ በመለየት/በመከፋፈል ማለት በቅጹ ቀደም ተከተል ሳይሆን በይዘታቸው ተመሳሳይነት ያላቸው ጉዳዮች አንድ ላይ በማምጣት በቀላሉ በመፈለግ ለመጠቀም ያለመ ነው።

ሁለት  ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ ውሳኔዎች (ለምሳሌ የውል፣ ዳኝነት ሥልጣን፣ አፈፃፀም፣ የጉምሩክ ወንጀሎችና ሌሎች ጉዳዮች) ከተቀመጠ ጥቅል ዘፍር ውጪ በሌላ ዘርፍ የሚገኙት ወይም/እና ከሌላ ዘርፍ ተያያዥነት ያላቸው ውሳኔዎች ስላሉ እነዛን ውሳኔዎች ከተቀመጡበት ጥቅል ዘርፍ “ኮፒ ፓስት” በማለት መቀመጥ በሚገባቸው ወይም/እና ተያያዥነት ወዳላቸው ጥቅል ዘርፍ የራሱ አርእስት ተሰጥቶት በድጋሜ እንዲቀመጡ በማድረግ ስለአንድ ዘርፍ በአንድ ላይ እንዲገኙ በማድረግ በቀላሉ በመፈለግ ለመጠቀም ያለመ ነው። ሶስት  በልዩ ልዩ ዘርፍ ያሉ ውሳኔዎች ከጥቂቶቹ ውሳኔዎች በስተቀር ባሉት ጥቅል ዘርፎች መቀመጥ እየተገባቸው ልዩ ልዩ በሚል ዘርፍ ስለተቀመጡ እነዛን ውሳኔዎች የጥቅል ዘርፉ አቀማማጥ ግምት ውስጥ በማስገባት በዛ ልዩ ልዩ በሚል ዘርፍ በንኡስ ዘርፍ ደረጃ ለይቶ/ከፋፍሎ በማስቀመጥ በቀላሉ በመፈለግ ለመጠቀም ያለመ ነው። አራት  በማውጫው ያሉ ብዙ ውሳኔዎች ጥቅል ዘርፉ እንዳለ ሆኖ በንኡስ ዘርፍ ደረጃ ስለምን ጉዳይ መሆናቸው ስለማያሳዩ እነዛ ውሳኔዎች ዋና ምንጭ ከሚባለው ከመፅሓፉ ይዘታቸውን በማየት ጥቅል ዘርፉ ባለበት ቦታ ወደ ሚመለከታቸው ንኡስ ዘርፍ በማስቀመጥ ስለአንድ ንኡስ ዘርፍ በአንድ ላይ እንዲገኙ በማድረግ በቀላሉ በመፈለግ ለመጠቀም ያለመ ነው። አምስት በተለያየ ዘርፍ ያሉ ከማስረጃና የህግ ግምት ጋር የተያያዙ የፍትሐብሔር ጉዳዮች ለብዙ ነገር ያገለግላሉ ተብለው የተመረጡትን “ኮፒ ፓስት” በማለት በድጋሜ በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ዘርፍ በማስቀመጥ በቀላሉ በመፈለግ ለመጠቀም ያለመ ነው።

File Name: FSCCD-Vol1-25-AregayG.pdf
Category: Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions
File Size: 10 Byte
Hits: 10393 Hits
Download: 31665 times
Created Date: 03-30-2023