Legal News - የሕግ ዜናዎች

Legal News - የሕግ ዜናዎች (301)

Abyssinia Law is the Ethiopian's leading legal news and information network for lawyers and other legal professionals. Read up-to-date legal news including civil trials, guilty verdicts and plea deals. 

ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች የሽብርተኝነት ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ወንጀል ችሎት ዓርብ መስከረም 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ክሱን ያቀረበው ዓቃቤ ሕግ፣ የቦምብ ጥቃቱ የተፈጸመው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ለመግደል መሆኑን በክሱ አስታውቋል፡፡ በቦምብ ጥቃቱ ክስ…
በሙስና ወንጀል ተከሰው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት አራት ዓመታት ከስምንት ወራት ፅኑ እስራትና 60,000 ብር የገንዘብ ቅጣት የተወሰነባቸው ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ በይግባኝ ሰሚው ችሎት በነፃ የተሰናበቱ ቢሆንም፣ የሰበር ሰሚ ችሎት የይግባኝ ሰሚ ችሎቱን ውሳኔውን ውድቅ በማድረግ የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ አፀናው፡፡ ዶ/ር ፍቅሩ ለእስራትና ለገንዘብ ቅጣት የዳረጋቸውን…
የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁን ጥሰዋል ተብለው ክስ የተመሠረተባቸው ተከሳሾች ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ የቆጠረባቸውን ምስክሮች የማወቅ ሕገ መንግሥታዊ መብት እንዳለባቸው ለፍርድ ቤት ያቀረቡት ጥያቄ፣ ‹‹የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልገዋል›› በማለት ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት መላኩ የሚታወስ ነው፡፡ ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ነው፡፡ በዚሁ ችሎት ተከሳሾች በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ…
አቢሲኒያ ሎው የሰበር ውሳኔዎችን ከአማርኛ ወደ እንግሊዝኛ በመተርጎም (Case Summary) ውሳኔዎቹን ለተጠቃሚዎቹ ለማድረስ የመጨረሻ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት በአንቀጽ 80 ሥር የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበትን ማናቸውንም የመጨረሻ ውሳኔ ለማረም በሰበር ችሎት የማየት ስልጣን እንደሚኖረው በግልጽ ይደነግጋል፡፡ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሠረታዊ የሆነ የሕግ…
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እርምጃ አፈፃፀም መመሪያን የአዋጁ አስፈፃሚ ኮማንድ ፖስት ይፋ አደረገ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እርምጃ አፈፃፀም መመሪያን አስመልክቶ የኮማንድ ፖስቱ ሴክሬታርያት ዋና ሃላፊ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት በመላ ሀገሪቱ እና በተለየ ሁኔታ ሁከት እና ብጥብጥ ተከስቶባቸው በነበሩ አካባቢዎች የሚጣሉ ልዩ…
ከዕረፍት ላይ በአስቸኳይ የተጠራው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6 አዋጆችንና 16 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ሹመትን አፅድቆ ተበተነ፡፡ ምክር ቤቱ ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. የሥራ ዘመኑን ጨርሶ የተበተነ ቢሆንም አፈጉባዔ አባዱላ ገመዳ ከሳምንት በፊት በብሔራዊ ቴሌቪዥን ባስነገሩት ማስታወቂያ የምክር ቤቱ አባላት ማክሰኞ ሐምሌ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. በአስቸኳይ…
የገጠማቸውን ሕመም ለማወቅ ባደረጉት ምርመራ በግራ ኩላሊታቸው ላይ ጠጠር መኖሩ የተነገራቸው የ37 ዓመት ሴት፣ ጠጠሩን በቀዶ ሕክምና ለማስወገድ በቤተል ቲቺንግ አጠቃላይ ሆስፒታል የተኙ ቢሆንም፣ ሕክምናው ተደርጎላቸው በሰላም ከተጠናቀቀ ከአራት ዓመታት በኋላ ባደረጉት የአልትራ ሳውንድ ምርመራ የግራ ኩላሊታቸው ሙሉ በሙሉ ተነጥሎ መውጣቱን በማወቃቸው የፍትሐ ብሔር ክስ መሠረቱ፡፡ ያለፈቃዳቸውና ያለዕውቀታቸው የግራ ኩላሊታቸው…
በሽብር ድርጊት ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው፤ እነ አቶ በቀለ ገርባ ታስረው የሚገኙበት የፌዴራል ማረሚያ ቤት የተለያዩ በደሎችን እየፈጸመባቸው መሆኑን ለፍርድ ቤት በማመልከታቸው የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ፍርድ ቤት ቀርቦ እንዲያስረዳ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ እነ አቶ በቀለ ገርባ በተመሠረተባቸው ክስ ላቀረቡት የመጀመርያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ላይ የከሳሽ ዓቃቤ ሕግን ምላሽ ለመቀበል…
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያና በሱዳን መንግሥታት መካከል በወንጀል የሚፈለጉ ግለሰቦችን አሳልፎ ለመስጠት የተፈረመውን ስምምነት ሰኔ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. በዋለው መደበኛ ጉባዔ አፀደቀው፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት ለምክር ቤቱ ቀርቦ ወደ ውጭ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተመራው የማፅደቂያ ረቂቅ አዋጅ በሁለቱ አገሮች በኩል ሰላምና መረጋጋት ለማስፈንና በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ሊቃጣ የሚችልን…
ክራውን ሆቴል (CROWN HOTEL) እና ክራውን ፕላዛ (CROWNE PLAZA) በንግድ ስያሜና በንግድ ምልክት ምዝገባ ላይ ባደረጉት ክርክር፣ አዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤትና የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ሁለቱም ስያሜውን መጠቀም እንደሚችሉት አስተላልፈውት የነበረውን ውሳኔ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት፣ ውሳኔውን በመሻር፣ የንግድ ምልክቱንም ሆነ ስያሜውን የመጠቀም ሕጋዊ መብት ያለው ክራውን…
አምነስቲና ተቃዋሚ ፓርቲዎች እግዱ እንዲነሳ መንግስትን ጠይቀዋል በጠበቃቸው አማካይነት ትናንት ለጠቅላይ ፍ/ቤት ያመለከቱት የቀድሞው የአንድነት አመራር አባል አቶ ሀብታሙ አያሌው፤ “በቂ ምክንያት አላቀረቡም” በሚል ፍ/ቤቱ ጥያቄያቸውን አልተቀበለም፡፡ ፍ/ቤቱ ትናንት ከሰዓት በኋላ የቀረበለትን ጥያቄ ከተመለከተ በኋላ “ዛሬውኑ እግዱን ለማንሳት የቀረበው ምክንያት በቂ አይደለም፤ ታማሚው ህክምናቸውን ሀገር ውስጥ እንደማያገኙና ህይወታቸው አስጊ ደረጃ…
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፕሮፌሰርነት የደረጃ እድገቴን ያለ አግባብ ከልክሎኛል ያሉት ዶ/ር መረራ ጉዲና፤ ከዩንቨርስቲው ማግኘት የሚገባኝን የአገልግሎትና ልዩ ልዩ ክፍያዎችም ነፍጎኛል ሲሉ ክስ አቀረቡ፡፡ ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ መናገሻ ምድብ ሥራ ክርክር ችሎት የቀረበው የዶክተር መረራ የክስ ማመልከቻ፤ በዩንቨርስቲው ውስጥ ከግማሽ በላይ ዕድሜዬን ያገለገልኩና ብርቱ፣ ብቁና ተጠያቂ ዜጐችን ሳፈራ…
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንት ሹመት አጸደቀ፡፡ ምክር ቤቱ አቶ ዳኜ መላኩ መሐሪን ፕሬዝዳንት፤ አቶ ጸጋዬ አስማማው ነጋን ደግሞ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾሟል፡፡ ሹመቱ የጸደቀው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም ለፌዴራል ከፍተኛና አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤቶች እጩዎችን ባቀረቡት…
የኢትዮ ጂቡቲ የምድር ባቡር ኩባንያ 20 ሚሊዮን ዩሮ ዋጋ ባለው የግልግል ክርክር በሔግ የተወሰነበት ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እንዲከልሰው ጠበቆቹ ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት አገኘ፡፡ እ.ኤ.አ. በ2006 በተፈረመ ስምምነት መሠረት በአውሮፓ ልማት ፈንድ የፋይናንስ ድጋፍ የጥገና ሥራ ለመሥራት የተስማማው የጣሊያን ኮንትራክተር በምድር…