የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ጌታቸው አምባዬ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሆነው ተሾሙ

May 17 2016

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ግንቦት 9 ቀን 2008 . ባካሔደው ስብሰባ የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙትን ክቡር አቶ ጌታቸው አምባዬን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አድርጎ ሾመ፡፡ ምክር ቤቱ  ሹመቱን አዲስ ለተዋቀረው ለፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት ያፀደቀው ጠቅላይ ሚንስትሩ ለምክር ቤቱ ሹመቱ እንዲፀድቅ  ባቀረቡት መሠረት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ አቶ ጌታቸው አምባዬን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ  ሆነው እንዲሾሙ የቀረበውን ሀሳብ ምክር ቤቱ  በሙሉ ድምፅ ተቀብሎታል።

አቶ ጌታቸው አምባዬ የፍትሕ ሥርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ ይህንን ኃላፊነት ለመወጣት ብቃት ያላቸው መሆኑ እምነት ተጥሎባቸዋል፡፡ አቶ ጌታቸው አምባዬ በጠቅላይ ፍርድ ቤት  ምክትል ፕሬዝዳንት አማካኝነት ቃለ  መኃላ ፈጽመዋል፡፡

Read 46214 times Last modified on May 17 2016
Abyssinia Law | Making Law Accessible!

Abyssinia Law is  a legal resource portal providing open access to primary and secondary legal materials for Ethiopia, such as laws, court decisions, articles, contact guidance and Lawyers Directory - with texts supplemented by online videos, a discussion forum and user blog. The service gives free access to Federal and State consolidated laws of Ethiopia (with status information whether the law is amended, repealed or effective)