በጋምቤላ ክልል በተለይም በአማራ ተወላጆችን (ደገኞች) ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ በማፈናቀልና በመግደል ወንጀል የተጠረጠሩ 46 የቀድሞ የክልሉ ሹማምንት ክስ ሰሞኑን በአዲስአበባ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት ቀረበ። ከቀበሌ እስከ ዞን በአመራርነት ርከን ነበሩ የተባሉት ተከሳሾች ባቀጣጠሉት ግጭት 126 ሰዎች በግፍ የተገደሉ ሲሆን ከ7 ሺህ የሚልቁ ሰዎችን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።
የፌደራል ዓቃቤ ሕግ በ2006 እና በ2007 ዓ.ም “ደገኞች ከክልላችን ይውጡልን” በሚል በጋምቤላ ክልል ማዣንግ ዞን፣ ጎደሬ እና ሜጢ እንዲሁም በሌሎችም ቀበሌዎች የወንጀል ፈጽመዋል ባላቸውና ከቀበሌ እስከ ዞን በአመራርነት እርከን፣ በሚሊሻነት እና በተለያዩ የግል ሥራ የተሰማሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር በማዋል ክስ መስርቷል።
ዓቃቤ ሕግ ተከሳሾች ዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ዜጎችን በማስታጠቅ አንዱ በሌላው ላይ የጦር መሣሪያ እንዲያነሳ አነሳስተዋል የሚለቱን የወንጀል ሕግ አንቀጾችን ጠቅሶባቸዋል። በተጨማሪም የእርስ በእርስ ግጭት እንዲነሳሳ ለማድረግ በመስማማት፣ በማደም በወንጀል ድርጊቱ ተሳትፈዋል ብሏል።