Print this page

ከፖሊስ ባልደረባ ኮንስታብል ሞባይል የወሰደው ግለሰብ በአንድ ዓመት ከ8 ወር ጽኑ እስራት ተቀጣ

FanaBC Mar 18 2015

ከፖሊስ ባልደረባ ኮንስታብል ሞባይል የወሰደው ግለሰብ በአንድ ዓመት ከ8 ወር ጽኑ እስራት ተቀጣ።

በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ 1ኛ የወንጀል ችሎት ነው ቅጣቱን ያስተላለፈው።

ተከሳሹ ኢዮሲያስ ገበረሚካዔል አራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 05/06 ነዋሪ ሲሆን፥ በገል ስራ አንደሚተዳደር በክስ መዝገቡ ተጠቅሷል።

ተከሳሹ በተደጋጋሚ በተለያዩ ቀናቶች በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 05 በሚገኘው እና በተለምዶ ጃንሜዳ እየተባለ ወደ ሚጠረው ስፍራ ይመላለሳል።

ግንቦት 17፣ 2006 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት በጃንሜዳ የግል ተበዳይ የሆነው የፖሊስ ባልደረባ ኮንስታብል ሰይድ የሲቪል ልብሰ ለብሶ በስፍራው ከሌሎች የሀብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን ስፖርታዊ ክንውኖችን ይከታተላል።

በዚህ ጊዜም ተከሳሹ ኢዮሲያስ የሲቪል ልብስ ከለበሰው ከግል ተበዳይ የፖሊስ ባለደረባ አጠገብ የቀመጣል።

የግል ተበዳዩ ኮንሰታብል ከ1 ሺህ 600 ብር በላይ የሚያወጣ የሞባይል ስልከ በእጁ ይዞ የነበረ ሲሆን፥ ተከሳሹም አንዴ ሞባይልህን አውሰኝ ብሎት ይቀበለዋል።

ስፖርታዊ ክንውኖችን እየተከታተሉ ተከሳሹም ሞባይሉን እየነካካ ከቆየ በኋላ፥ ተከሳሹ ከቦታው ለቆ ለመሰወረ ሲሞክር የግል ተበዳይም ስልኬን መልስልኝ ይለዋል።

ተከሳሹም በወቅቱ ስለከሀን መልሼልሃለው ሲል ጮክ ባለ ድምጽ ይከራከራል።

በሁኔታው እና ተከሳሹ በምን ቅጽበት ስልኩን እንዳሸሸው ግራ የተጋባው የግል ተበዳዩ የፖሊስ ባለደረባ ጉዳዩን ወደ ፖሊስ ዘንድ እንዲደርስ ያደርጋል።

ፖሊስም ጉዳዩን ሲመረምር ቆይቶ ተከሳሽ ላይ ክስ መስርቶበታል።

ተከሳሹም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ 1ኛ የወንጀል ችሎት ቀርቦ ድርጊቱን አልፈጸምኩም በማለት ተከራክሯል።

ይሁን እንጂ የቀረበበትን የአቃቤ ህግ ማስረጃ መከላከል ባለመቻሉ ጥፋተኛ ተብሏል።

ተከሳሹም የቀደመ የወንጀል ሪከርድ የሌለበት መሆኑ እና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኑ ከግምት ውስጥ ገብቶ በቅጣተ ማቅለያነት ተይዞለት በ1 ዓመት ከ8 ወር ጽኑ እስራት ተቀጥቷል።

Read 35811 times