የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የትምባሆ ቁጥጥር ስምምነት አዋጅን አፀደቀ። አዋጁ ህዝብ በሚሰበሰብባቸው ሰፍራዎች ሲጋራ ማጨስን የሚከለክል ነው። በትምባሆ ላይ የሚጣል ግብርን ማሳደግና የትምባሆ ዋጋ እንዲጨምር ማድረግም በቁጥጥር አዋጁ ላይ ተካትቷል። አዲሱ አዋጅ የትምባሆ ምርቶች ማሸጊያና ገላጭ ፅሁፎች የትንባሆን ጎጅነት እንዲያመለክቱም የሚያስፈድድ ነው። የትምባሆ ምርቶችን ማስተዋወቅና ተጠቃሚነትን የሚያበረታቱ ተግባራትን በመገናኛ ብዙሃን ማሳየትንም አዋጁ ይከለክላል። አዋጁ እንደታተመ አቢሲኒያሎው ሕጎችን ያግኙ በሚለው ክፍል ውስጥ ያካትታል፡፡