የደቡብ ክልል ፍትሕ ቢሮ 60 ዐቃቢያነ ሕግን በሥነ-ምግባር ግድፈት ከሥራ አሰናበተ:: ቢሮው ሌሎች 211 የሚሆኑትን ከቀላል እስከ ከባድ የሚደርስ ርምጃ ወስዶባቸዋል። በተመሳሳይ የክልሉ ማረሚያ ኮሚሽንም 42 የሰራዊቱ አባላት ላይ ከባድ ርምጃ የወሰደ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 10 የሚሆኑት ሙሉ በሙሉ ከስራቸው የተሰናበቱ ናቸው፡፡
የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ሃላፊ አቶ አድማሱ አንጎ እና የማረሚያ ኮሚሽን ኮሚሽነሩ አዳነ ዲንጋሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ግለሰቦቹ ርምጃው የተወሰደባቸው ጉቦ በመቀበል፣ ፍትሕ በማዛባት፣ በወገናዊነት መስራት እና እስረኞች እንዲያመልጡ ማድረግ የመሳሰሉትን ወንጀሎች ፈፅመው በመገኘታቸው ነው።
ከቀበሌ እስከ ክልል ድረስ ነዋሪዎችን ባሳተፈ ሁኔታ የተካሄደው ርምጃ ቀጣይነት የሚኖረው መሆኑንም የሥራ ሃላፊዎቹ ተናግረዋል። ርምጃ ከተወሰደባቸው ግለሰቦች መካከልም አብዛኛዎቹ ክስ ይመሠረትባቸዋል ተብሏል።
ጥያቄያችን ክስ ሳይመሠረትባቸውና ጥፋታቸው ሳይረጋገጥ የተወሰደባቸው ርምጃ ከሕግ እና ሥነ ሥርዐት አንፃር እንዴት ያዩታል?