የቀድሞው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ታዬ ባያብል የ2 ዓመት እሥራት ወደ 6 ዓመት ከፍ አለ

Jan 15 2014

የቀድሞው የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ዋና አፈጉባዔ የነበሩት አቶ ታዬ ባያብል ባለፈው ዓመት የሙስና ወንጀል ፈጽመው ተላልፎባቸው የነበረው የ2 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እሥራት በይግባኝ ወደ 6 ዓመት ከ6 ወር ከፍ እንዲል የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወሰነ፡፡

ተከሳሹ በ2003 ዓ.ም የግብርና ቢሮ ኃላፊ እያሉ በመንደር ማሰባሰብ ፕሮግራም ለታቀፉ አርብቶ አደሮች ከ4 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ የእርሻ መሳሪያ ግዥ ያለጨረታ በፕሪፎርማ ብቻ እንዲካሄድ ማድረጋቸው በቀዳሚነት ጥፋተኛ አስብሏቸዋል።

ከእርሳቸው ጋር ክስ ከተመሰረተበት የቢሮው ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር የስራ ሂደት ባለቤት ከነበሩት አቶ ሙሉጌታ ዱሳ ጋር በመሆን ከጣሱት የጨረታ ሂደት በተጨማሪ ጥራት የሌለው እቃ እንዲቀርብ አድርገዋል የሚለውም ሌላኛው ነው። በዚህ ሕገ ወጥ የጨረታ ሂደት እነርሱም ሕገ ወጥ ተጠቃሚ ሆነው የመንግሥት ግዥ በጨረታ ሂት ባለማለፉ ከ126 ሺ ብር በላይ ማጣቱም ነው ቅጣት እንዲጣልባቸው ያስደረገው፡፡

በዚህም መሠረት የአሶሳ ዞን ከፍተና ፍርድ ቤት ሐምሌ 17 ቀን 2005 ዓ.ም አቶ ታዬ ባያብልን በ2 ዓመት ከ 6 ወር ጽኑ እሥራት እና 2500 ብር፤ ግብራበራቸው አቶ ሙሉጌታ ዱሳንም እንዲሁም በተመሳሳይ ቀጥቷቸዋል ነበር፡፡

የክልሉ ሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ሕግ በውሳኔው ላይ ቅር በመሰኘት ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበውን አቤቱታ ተከትሎ፤ ትላንት ጥር 6 ቀን 2005 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ አቶ ታዬ ባያብል የእሥር ፍርድ ቤቱ ያስተላለፈባቸው የ2 ዓመት ከ6ወር ጽኑ እሥራት ተሽሮ፤ በ 6 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እሥራት እንዲቀጡ ሲደረግ፤ ግብራበራቸው አቶ ሙሉ ጌታም በ5 ዓመት ጽኑ እሥራት እና 3 ሺ ብር እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል፡፡

Read 39437 times Last modified on Jan 15 2014
Abyssinia Law | Making Law Accessible!

Abyssinia Law is  a legal resource portal providing open access to primary and secondary legal materials for Ethiopia, such as laws, court decisions, articles, contact guidance and Lawyers Directory - with texts supplemented by online videos, a discussion forum and user blog. The service gives free access to Federal and State consolidated laws of Ethiopia (with status information whether the law is amended, repealed or effective)