Sentencing and Execution

የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሰረት ቅጣት የሚወሰንበት ሁኔታ

በሰንጠረዡ መሰረት ቅጣትን ለመወሰን በመጀመሪያ የሚነሳው መሰረታዊ ጥያቄ በዚህ ሰንጠረዥ መሰረት ቅጣትን እንዴት እንወስናለን የሚለው ነው፡፡ ማለትም፣

መነሻ ቅጣት እንዴት እንወስናለን?

በማክበጃዎች መሰረት እንዴት እንወስናለን ?

በማቅለያዎች መሰረት እንዴት እንወስናለን ?

የሚሉት ናቸው፡፡

የወንጀል ደረጃዎችን እንደወንጀሉ ከባድነት መለየት

በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 88(2) ዳኛው ቅጣትን ሲወስን የወንጀል አድራጊውን ግላዊ የአደገኛነት መጠን፣ ያለፈ የህይወት ታሪኩን፣ ወንጀሉን ለማድረግ ያነሳሱትን ምክንያቶችና የሀሳቡን አላማ፣ የግል ኑሮውን ሁኔታ፣ የትምህርቱን ደረጃ እንዲሁም የወንጀሉን ከባድነትና የአፈጻጸሙን ሁኔታዎች በማመዛዘን ነው ይላል፡፡

በዚህ ድንጋጌ የተመለከቱት ምክንያቶች የሚያመለክቱት የተፈጸመው ወንጀልና የተጣሰው የወንጀል ድንጋጌ አንድ ቢሆንም በዚህ ድንጋጌ ውስጥ ከተመለከቱት ምክንያቶች መሟላትና አለመሟላት አንጻር ቅጣት በተለያዩ ወንጀል አድራጊዎች መካከል ሊለያይ እንደሚችል ነው፡፡ ተመሳሳይ አይነት ወንጀል ሆኖ አንዱ ወንጀለኛ ዝቅተኛ ቅጣት ሲቀጣ ሌላው ደግሞ ከባድ ቅጣት ሊቀጣ እንደሚችል የሚያመለክት ነው፡፡ ይህም ወንጀሉ ተመሳሳይ ቢሆንም የተለያየ የከባድነት ደረጃዎች ሊኖሩት እንደሚችሉ የሚያመለክት ነው፡፡

ከዚህ በመነሳትም መመሪያው የተፈጸመው ወንጀል አንድ የወንጀል ህጉን ድንጋጌ የሚጥስ ቢሆንም ወንጀሉ እንደክብደቱ ደረጃዎች ሊወጡለት የሚችሉ መሆኑን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የወንጀል ደረጃዎች ለተለያዩ የወንጀል አይነቶች አዘጋጅቷል፡፡

በመመሪያው መሰረት ለወንጀሎች የተለያየ የወንጀል ደረጃ ሲወጣ ግን በአንቀጽ 88(2) ያሉትን ምክንያቶች በሙሉ በመስፈርትነት አልተጠቀመም፡፡ ምክንያቱም በድንጋጌዎች የተቀመጡት ቅጣትን ለመወሰን ያገለግላሉ ተብለው የተቀመጡት ምክንያቶች በተለያዩ የወንጀል ህጉ ውስጥ ተመልክተው እናገኛቸዋለን፡፡ እነዚህ ምክንያቶች አንዳንድ ጊዜ ቅጣቱን ለማክበድ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ቅጣቱን ለማቅለል ሊውሉ ይችላሉ፡፡

ለምሳሌ፣

1.  የወንጀል አድራጊው ያለፈ የህይወት ታሪኩን በሚመለከት ቀድሞ ወንጀል አድርጎ የተቀጣ ከሆነ በማክበጃነት (አንቀጽ 84(1)(ሐ)፣ ቀድሞ ወንጀል ፈጽሞ ያልነበረና መልካም ጸባይ የነበረው ከሆነ በማቅለያነት (አንቀጽ 82(1)(ሀ) ያገለግላል፣

2.  ወንጀሉን የፈጸመው በከሀዲነት፣ በምቀኝነት ከሆነ በማክበጃነት (አንቀጽ 84(1)(ሀ)፣ ከፍ ባለ ሀይማኖታዊ ወዘተ አላማ ከሆነ በማቅለያነት (አንቀጽ 82(1)(ለ) ያገለግላል፣ ወዘተ…

በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 189 እንደተመለከተው ዳኛው በቅድሚያ ማክበጃ ምክንያቶችን መሰረት አድርጎ እንደሚያከብድ ያስቀመጠ ስለሆነ፣ በማክበጃ ምክንያቶች መሰረትም ቅጣቱን ለማክበድ መጀመሪያ መነሻ ቅጣት ማስቀመጥ ስለሚያስፈልግ፣ መነሻ ቅጣቱ ሲወሰን ማክበጃና ማቅለያ ምክንያቶች ከመታየታቸው በፊት የሚወሰን ነው ማለት ነው፡፡

ስለሆነም የወንጀል ደረጃዎችን ለማውጣት በወንጀል ህጉ 88 ያሉት ምክንያቶች ሁሉ ሳይሆን ታሳቢ የተደረጉት በአንድ ወይም በሌላ መልኩ በማክበጃነት ወይም በማቅለያነት ሊጠቀሱ የማይችሉ በአንቀጽ 88 የተመለከቱት ምክንያቶች ናቸው፡፡

ስለሆነም መመሪያው የወንጀል ደረጃዎችን ለማውጣት ቅድሚያ የሰጠው የወንጀል ደረጃውን ከወንጀሉ ከባድነት አንጻር ደረጃ በማውጣት ነው፡፡

ስለሆነም ጥፋት አድራጊው ጥፋተኛ የተባለበት የወንጀል ድንጋጌ አንድ ቢሆንም፣ የጥፋቱ አፈጻጸም አደገኛነትና ያስከተለው ጉዳት ከባድነት አንዱ ከሌላው የተለየ ከሆነ መነሻ ቅጣታቸውም ተመሳሳይ ሊሆን ስለማይገባው እንደወንጀሉ ከባድነት መነሻው ከዝቅተኛው ጀምሮ ከፍ እያለ ሊሄድ ይገባል የሚል መነሻ አለው፡፡ በዚህ መሰረትም በዚህ መመሪያ ለተወሰኑት ወንጀሎች የወንጀል ደረጃዎች ተዘጋጅተውላቸዋል፡፡

የመነሻ ቅጣት አወሳሰን

1.መመሪያው ህግ አውጪው ለእያንዳንዱ የወንጀል ድርጊት የቅጣት መነሻና ጣሪያ አድርጎ ያስቀመጣቸው የቅጣት መጠኖች ትርጉም ሊኖራቸው በሚችል መልኩም የቅጣት መመሪያው መዘጋጀት አለበት የሚልም መነሻ አለው፡፡ ማለትም በወንጀል አፈጻጸሙም ሆነ ከባድነቱ ቀላልና ዝቅተኛ የሚባለው የቅጣቱ መነሻ በወንጀል ህጉ የተቀመጠው መነሻ መሆን አለበት የሚል መነሻ አለው፡፡ ለምሳሌ ቅጣቱ ከ1 አመት ቀላል እስራት እስከ 5 አመት ጽኑ እስራት የሚል ከሆነ፣ ድንጋጌውን በመጣስ ከሚፈጸመው ወንጀል በተነጻጻሪ ቀላልና ዝቅተኛ የሚባለው የወንጀል ድርጊት መነሻ ቅጣቱ 1 አመት ቀላል እስራት መሆን አለበት የሚል ነው፡፡ ስለሆነም ለእያንዳንዱ የወንጀል ድንጋጌ ዝቅተኛ ደረጃ በወንጀል ህጉ ልዩ ክፍል የተቀመጠው ዝቅተኛ መነሻ ይሆናል፡፡

2.በወንጀል ድንጋጌው ውስጥ ለሚወድቀው ከፍተኛ የወንጀል ደረጃ ለድንጋጌው የተመለከተው ጣሪያ ላይ አይደርስም፡፡ ምክንያቱም በልዩ ክፍል የተመለከቱት የቅጣት ጣሪያ ላይ የሚደረሰው ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃዎች ሲኖሩ ነው፡፡ የወንጀል ህግ ቁጥር 183 ቅጣቱ እንዲከብድ ህጉ በደነገገ ጊዜ (84) ለቅጣቱ ማክበጃ የሆኑትን ምክንያቶች አይነትና ብዛት እንዲሁም ወንጀለኛው የፈጸመውን ጥፋት ከባድነት በማመዛዘን ፍርድ ቤቱ በዚህ ሕግ ልዩ ክፍል በተመለከተው አግባብነት ባለው ድንጋጌ ከተወሰነው ቅጣት ጣሪያ ሳያልፍ ቅጣቱን ይወስናል፡፡ ስለሆነም  በህጉ አንቀጽ 84 የተመለከቱትን ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃዎች አምስት ሲሆኑ፣ ሁሉም ተማልተው ሲገኙ ጣሪያው ላይ እንዲደርስ ታሳቢ በማድረግ፣ ከአምስት እርከን በታች ለከፍተኛው ደረጃ መነሻ እንዲሆን ተደርጎአል፡፡

3.እያንዳንዱን የወንጀል አፈጻጸም በዝርዝር በማስቀመጥ ደረጃ ለማውጣት ስለማይቻል፣ መሰረታዊ ባህርዩን በመለየት፣ ከዚህ በተጨማሪ እያንዳንዱን የወንጀል ድርጊት የሚገልጸውን ባህርይ እየለየ ዳኛው ቅጣቱን ለማስቀመጥ እንዲችል ከሚገባው በላይ ሰፊ ባይሆንም ምክንያታዊ ፍቅድ ስልጣን (ዲስክሬሽን) ዳኛው ሊኖረው ይገባል የሚል መነሻም ያለው ነው፡፡  ስለሆነም በተቀመጠው ፍቅድ ስልጣን ውስጥ ዳኛው መነሻ ቅጣቱን ይወስናል ማለት ነው፡፡

ለእያንዳንዱ የወንጀል ደረጃ የቅጣት መነሻና መድረሻ የተወሰነበት ሁኔታ፣

በስልጣን አለአግባብ መገልገል ወንጀል 407(1)

በወንጀል ሕግ 407(1) ውስጥ ለሚወድቁ የወንጀል ድርጊቶች 6 የወንጀል ደረጃዎች አሉት፡፡

ዝቅተኛው ወይም ደረጃ 1 መነሻው ቅጣት የቅጣት እርከን 7 ሲሆን፣ ይህም በወንጀል ህጉ ከተቀመጠው መነሻ አንድ አመት የሚነሳ ነው፡፡

ከፍተኛ ደረጃ የተባለው ደግሞ መነሻ ቅጣቱ በእርከን 23 የተቀመጠ ሲሆን፣ ይህም ከ 6 አመት እስከ 7 አመት ከ2 ወር ነው፡፡

በ407(1) ከፍተኛ ለተባለው የወንጀል ደረጃ 6 (እርከን 23) አምስት የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች ቢኖሩና ቅጣቱ በአምስት እርከን ቢከብድ እርከን 28 ላይ ይደርሳል፡፡

የእርከን 28 ቅጣት ከ9 አመት እስከ 10 አመት ከ10 ወር ነው፡፡ በወንጀል ህጉ ለወንጀሉ የተቀመጠው የቅጣት ጣሪያ 10 አመት ጽኑ እስራትን ያካተተ ነው፡፡

ስለሆነም በዚህ እርከን ውስጥ ከ10 አመት ሳይበልጥ ቅጣቱ ይወሰናል ማለት ነው፡፡

በስልጣን አለአግባብ መገልገል ወንጀል 407(2)

በወንጀል ሕግ 407(2) ውስጥ ለሚወድቁ የወንጀል ድርጊቶች 4 የወንጀል ደረጃዎች አሉት፡፡

ዝቅተኛው ወይም ደረጃ 1 መነሻው ቅጣት የቅጣት እርከን 25 ሲሆን፣ ይህም በወንጀል ህጉ ከተቀመጠው መነሻ ሰባት አመት የሚነሳ ነው፡፡

ከፍተኛ ደረጃ የተባለው ደረጃ 4 መነሻው የቅጣት እርከን 28 ሲሆን የዚህም የቅጣት መነሻ ከ9 አመት እስከ 10 አመት ከ10 ወር ነው፡፡

በ407(2) ከፍተኛ ለተባለው የወንጀል ደረጃ 4 አምስት የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች ቢኖሩና ቅጣቱ በአምስት እርከን ቢከብድ እርከን 33 ላይ ይደርሳል፡፡

የእርከን 33 ቅጣት ከ14 አመት እስከ 16 አመት ከ10 ወር ነው፡፡ በወንጀል ህጉ ለወንጀሉ የተቀመጠው የቅጣት ጣሪያ 15 አመት ጽኑ እስራትን ያካተተ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ እርከን ውስጥ ከ15 አመት ሳይበልጥ ቅጣቱ ይወሰናል ማለት ነው፡፡

ከባድ ስርቆት 669

·        በወንጀል ሕግ 669 ውስጥ ለሚወድቁ የወንጀል ድርጊቶች 9 የወንጀል ደረጃዎች አሉት፡፡

·  ዝቅተኛው ወይም ደረጃ 1 መነሻው ቅጣት የቅጣት እርከን 7 ሲሆን፣ ይህም በወንጀል ህጉ ከተቀመጠው መነሻ 1 አመት የሚነሳ ነው፡፡

·   ከፍተኛ ደረጃ የተባለው ደረጃ 9 መነሻው የቅጣት እርከን 27 ሲሆን የዚህም የቅጣት መነሻ ከ8 አመት ከ5 ወር እስከ 10 አመት ነው፡፡

·    በ669 ከፍተኛ ለተባለው የወንጀል ደረጃ 9 (እርከን 27) አምስት የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች ቢኖሩና ቅጣቱ በአምስት እርከን ቢከብድ እርከን 32 ላይ ይደርሳል፡፡

·   የእርከን 32 ቅጣት ከ13 አመት እስከ 15 አመት ከ8 ወር ነው፡፡ በወንጀል ህጉ ለወንጀሉ የተቀመጠው የቅጣት ጣሪያ 15 አመት ጽኑ እስራትን ያካተተ ነው፡፡

·        ስለሆነም በዚህ እርከን ውስጥ ከ5 አመት ሳይበልጥ ቅጣቱ ይወሰናል ማለት ነው፡፡

 

በድንጋጌው ዝቅተኛ የወንጀል ደረጃና ከፍተኛ የወንጀል ደረጃ መካከል ያሉትን የወንጀል ደረጃዎች መነሻ ቅጣት አወሳሰን

በድንጋጌው ዝቅተኛው የወንጀል ደረጃና ከፍተኛው የወንጀል ደረጃ የሚያርፉበት ከታወቀ፣ በእነዚህ መሀከል ያሉት የተለያዩ የወንጀል ደረጃዎች በቁጥራቸው ልክ ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን የቅጣት ዘመን በማካፈል የቅጣት መነሻቸው ተወስኗል፡፡

ምሳሌ 1፣

በ407(1) ስድስት የወንጀል ደረጃዎች አሉ፡፡

ዝቅተኛው ደረጃ መነሻው አንድ አመት ስለሆነ እርከን 7 ላይ ነው፡፡

ከፍተኛው ደረጃ 6 ደግሞ እርከን 23 ላይ ነው፡፡

በመካከላቸው 16 እርከን ልዩነት አለ፡፡

ስለሆነም 16 እርከን ለ5 ሲካፈል (የመነሻው የታወቀ ስለሆነ አንድ ይቀንሳል) የሚገኘው ውጤት 3 አካባቢ ነው፡፡ ስለሆነም ከዝቅተኛው ጀምሮ ለእያንዳንዱ 3 እርከን እያለፈ መነሻ ቅጣቱ ተቀምጧል፡፡ በማጠጋጋት አንዱን 4 እርከን ልዩነት እንዲኖረው ተደርገል፡፡

ምሳሌ 2፣

በ665 7 የወንጀል ደረጃዎች አሉ፡፡

ዝቅተኛው ደረጃ መነሻው አንድ 10 ቀን ስለሆነ እርከን 2 ላይ ነው፡፡

ከፍተኛው ደረጃ 2 ደግሞ እርከን 14 ላይ ነው፡፡

በመካከላቸው 12 እርከን ልዩነት አለ፡፡

ስለሆነም 12 እርከን ለ6 ሲካፈል የሚገኘው ውጤት 2 ነው፡፡ ስለሆነም ከዝቅተኛው ጀምሮ ለእያንዳንዱ 2 እርከን እያለፈ መነሻ ቅጣቱ ተቀምጧል፡፡

የገንዘብ መቀጮን በተመለከተ

የገንዘብ መቀጮውን በተመለከተም ለወንጀሉ ድርጊት ከተቀመጠው ጣሪያ ሳይበልጥ በድንጋጌው ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ወንጀል አድራጊ እስከመቀጮው ጣሪያ እንዲከፍል በሚያደርግ መልኩ፣የወንጀል ደረጃው ዝቅ እያለ በሄደ ቁጥርም የገንዘብ መቀጮ ጣሪያውም በዚያው መልክ እየቀነሰ እንዲሄድ በማድረግ ደረጃው ተዘጋጅቷል፡፡

ምሳሌ

በ407(1) ከፍተኛው የገንዘብ መቀጮ ብር 10000 ነው፡፡

ስለሆነም ከፍተኛው ደረጃ 6 ሲሆን ለዚህ መቀጮው እርከን 6 ነው፡፡ (10000)

የወንጀል ደረጃው ደረጃ 5 ከሆነ የመቀጮው እርከን 5 ነው፡፡ (7000)

በዚህ መልኩ ለሁሉም የወንጀል ደረጃዎች የቅጣት መነሻውን ለማወቅ የሚያርፉበት እርከን

ተመልክቷል፡፡

ደረጃ ለወጣላቸው ወንጀሎች ቅጣት አወሳሰን ዝርዝር አሰራር ማሳያ

ቅጣቱ የሚወሰንበት ቅደም ተከተል

1.  ጥፋተኛ ተብሎ ሲወሰን ጥፋተኛ ተብሎ የተወሰነበት ድንጋጌም የሚታወቅ ስለሆነ፣ ለወንጀሉ ከወጡት የወንጀል ደረጃዎች አንጻር ደረጃው ይለያል፡፡

2.  ለወንጀል ደረጃው የተቀመጠው የቅጣት እርከን ይለያል፡፡

3.  በእርከኑ ውስጥ ዳኛው ቅጣቱን ይወስናል፡፡

በስልጣን አለአግባብ መገልገል የሚፈጸም ወንጀልን በተመለከተ

በመመሪያው መሰረት ዳኛው በወንጀል ህጉ አንቀጽ 407 ቅጣት ለመወሰን ከግምት የሚያስገባቸው ሶስት መሰረታዊ ጉዳዮች ናቸው፡፡ እነርሱም፣ የአጥፊው የስልጣን ደረጃ፣ በወንጀሉ ምክንያት የደረሰ ጥቅም ወይም ጉዳት እና ወንጀሉ የተፈጸመበት አላማ ናቸው፡፡

ምሳሌ 1.

በ407(1) መሰረት ጥፋተኛ የተባለው ሰው የስልጣን ደረጃው የመምሪያ ሀላፊ ሲሆን፣ በወንጀሉ ምክንያት ያገኘው የማይገባ ጥቅም 30000 ብር ነው፡፡

የዚህን ወንጀል አድራጊ ቅጣት ለመወሰን የመጀመሪያው ጥያቄ የስልጣን ደረጃው ምንድነው የሚል ነው፡፡ የስራ ሀላፊነቱ የመምሪያ ሀላፊ ስለሆነ መካከለኛ ባለስልጣን በሚለው ላይ ይወድቃል፡፡

የተገኘው ጥቅም ብር 30000 ስለሆነ መካከለኛ ጥቅም ወይም ጉዳት በሚለው ስር ይወድቃል፡፡ (ተከሳሽ በወንጀሉ ምክንያት ያገኘውን ጥቅም በገንዘብ ተምኖ ማስቀመጥ የማይቻል ከሆነ ዝቅተኛ ጥቅም በሚለው ካታጎሪ ውስጥ ይወድቃል፡፡)

በሶስተኛ ደረጃ የሚጠየቀውና የሚጣራው ወንጀሉን የፈጸመው በምን አላማ ነው የሚለው ነው፡፡ በመመሪያው መሰረት ሁለት መስፈርቶች አሉ፡፡ ወንጀሉን የፈጸመው በችግር ወይም በተጽእኖ ከሆነ ዝቅተኛው ካታጎሪ ውስጥ ሲወድቅ ከዚህ ውጭ ከሆነ ከባድ አላማ በሚለው ውስጥ ይወድቃል ማለት ነው፡፡

በመመሪያው እንደተመለከተው ወንጀሉን የፈጸመው በችግር ወይም በተጽአኖ መሆኑን የሚያስረዳ ማስረጃ ከሌለ ከባድ አላማ እንዳለ እንደሚቆጠር ተመልክቷል፡፡

በዚህ ጉዳይ ወንጀል አድራጊው በችግር ወይም በተጽእኖ ወንጀሉን ለመፈጸሙ የሚያስረዳ ማስረጃ የለም፡፡ ስለሆነም የተፈጸመበት አላማ ከባድ አላማ ነው ማለት ነው፡፡

ከእነዚህ በመነሳት ወንጀለኛው (መካከለኛ ስልጣን ነው/ መካከለኛ ጥቅም ወይም ጉዳት ያገኘ ነው/ በከባድ አላማ የፈጸመ ነው፡፡ )

የእስራት ቅጣትን በተመለከተ፣

·  በእነዚህ መለያዎች መሰረት በመመሪያው አባሪ ሶስት ከ407 አንጻር በተቀመጡት በየትኛው የወንጀል ደረጃ ውስጥ እንዳለ እንመለከታለን፡፡ በዚህ መሰረት በ407(1) ውስጥ በወንጀል ደረጃ 6 እናገኘዋለን፡፡

·    በዚህ የወንጀል ደረጃ 6- እስራትን በተመለከተ ቅጣቱ የሚወድቀው እርከን 23 ላይ እንደሆነ በአባሪ ሶስት አራተኛው ኮለም (አምድ) ላይ ተመልክቷል፡፡ ስለሆነም የቅጣት እርከኑ ተለየ ማለት ነው፡፡

·        በእርከን 23 የቅጣት ሬንጅ (ፍቅድ ስልጣን) ከ 6 አመት እስከ 7 አመት ከ2 ወር ነው፡፡

·   ዳኛው በዚህ ሬንጅ ውስጥ የቤተሰብ አስተዳዳሪነቱን፣ የኑሮውን ሁኔታ ወዘተ ከግምት በማስገባት ቅጣቱን ይወስናል፡፡ በዚህ ጉዳይ ቅጣቱን ለምሳሌ 6 አመት ብሎ ሊወስን ይችላል፡፡

የገንዘብ መቀጮን በተመለከተ፣

· የገንዘብ መቀጮን በተመለከተም በወንጀል ህጉ ከተቀመጠው አንጻር እንዴት እንደሚወሰን በመመሪያው ተመልክቷል፡፡

·      ወንጀል አድራጊው የወንጀል ደረጃው በ407(1) ደረጃ 6 ላይ ነው፡፡ ለዚህ በአባሪ ሶስት የተመለከተው የመቀጮው እርከን 6 ነው፡፡

·        የመቀጮ እርከን 6 ጣሪያው እስከ ብር 10000 ድረስ ነው፡፡

·  ዳኛው ከዚህ ጣሪያ ሳያልፍ ቅጣቱን ይወስናል ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ብር 8000 ብሎ ሊወስን ይችላል፡፡

·        ይሁንና መቀጮ ሲወሰን ታሳቢ የሚደረጉ በርካታ ምክንያቶች ያሉ ስለሆነ መቀጮውን ላይወስንም ይችላል፡፡

የተፈጸመበት አላማ ከባድ ተብሎ በመመሪያው ከተጠቀሰውም በላይ በሆነ ጊዜ ቅጣቱ እንዴት ይወሰናል?

በመመሪያው እንደተመለከተው ከአላማው አንጻር ከባድ አላማ በላይም ሆኖ ዳኛው ቢያገኘው ማለትም ለምሳሌ ወንጀሉ የተፈጸመው የሀገር ምስጢርን ለሌላ አገር ለማሳለፍ ከሆነ፣ በአንቀጽ 407 መሰረት የተፈጸመበት አላማ ቅጣቱን እንደሚያከብደው ያስቀመጠ ስለሆነ በ407(1) ውስጥ ይወድቅ የነበረው በ407(2) ውስጥ ይወድቃል ማለት ነው፡፡

በ407(2) ውስጥ የነበረው ከአንድ በላይ ማክበጃ ምክንያቶች ተሟልተው የሚገኙበት ስለሆነ አላማው ከባድ አላማ ከተባለውም በላይ ከሆነ ከአንድ በላይ ማክበጃ ተደራርበው ስለሚገኙ በ407(3) ውስጥ ይወድቃል ማለት ነው፡፡ ስለሆነም የወንጀል ደረጃው ከዚህ በታች በተመለከተው መሰረት ይስተካከላል ማለት ነው፡፡  

·  የስልጣን ደረጃው ዝቅተኛ/ የተገኘው የጥቅም መጠን ዝቅተኛ/ የተፈጸመበት አላማ ከባድ አላማ ከተባለው በላይ ከሆነ በአንቀጽ 407(2) ደረጃ 7 ይሆናል፡፡

·        የስልጣን ደረጃው መካከለኛ/የተገኘው ጥቅም መጠን ዝቅተኛ/ የተፈጸመበት አላማ ከባድ አላማ ከተባለው በላይ ከሆነ በአንቀጽ 407(2) ደረጃ 8 ይሆናል፡፡

·     የስልጣን ደረጃው ዝቅተኛ/ የተገኘው የገንዘብ መጠን መካከለኛ ከሆነ/ የተፈጸመበት አላማ ከባድ አላማ ከተባለው በላይ ከሆነ በአንቀጽ 407(2) ደረጃ 9 ይሆናል፡፡

·        የስልጣን ደረጃው መካከለኛ/የተገኘው ጥቅምም መካከለኛ ከሆነ/ የተፈጸመበት አላማ ከባድ አላማ ከተባለው በላይ ከሆነ በአንቀጽ 407(2) ደረጃ 10 ይሆናል፡፡

·   በ407(2) በደረጃ 1 እና 2 ውስጥ የሚወድቀው ከአላማው አንጻር ሌላ ተደራቢ ማክበጃ ምክንያት በመኖሩ በ407(3) ደረጃ 11 ውስጥ የሚወድቅ ይሆናል፡፡

·  በ407(2) በደረጃ 3 እና 4 ውስጥ የሚወድቀው ደግሞ ከአላማው አንጻር ሌላ ተደራቢ ማክበጃ ምክንያት በመኖሩ በ407(3) ደረጃ 12 ውስጥ የሚወድቅ ይሆናል፡፡

በሰው አካልና ጤንነት ላይ የሚፈጸም ወንጀልን በተመለከተ

በሰው አካልና ጤንነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በተመለከተ የወንጀል ህጉ ድንጋጌዎች ከ555-560 ድረስ ናቸው፡፡ እነዚህ ቀላል የአካል ጉዳት እና ከባድ የአካል ጉዳት በሚል የተከፈሉ ናቸው፡፡

በ555 መሰረት ጥፋተኛ ነው ተብሎ በተወሰነበት ሰው ላይ ቅጣት እንዴት ይወሰናል?

ቅጣቱን ለመወሰን ዳኛው ከግምት የሚያስገባው የደረሰው የጉዳት መጠንን እና አጥፊው የሙያ ግዴታ ያለበት መሆኑን መሰረት ባደረገ መልኩ ነው፡፡  ስለሆነም የደረሰው ጉዳት፣ 1) ሊድን የሚችል ነው? 2) ዘላቂ የማይጠፋ ነው? 3) ለህይወቱ ያሰጋዋል? ለሚሉት ጥያቄዎች ምላሹን ያስቀምጣል፡፡

ምሳሌ ሁለት

·        በቀረበው ጉዳይ ላይ በወንጀል ሰለባው ላይ የደረሰው ጉዳት ለህይወቱ የሚያሰጋ ነው፡፡

·        ወንጀል አድራጊው ሙያዊ ግዴታ እንዳለበት ተረጋግጧል፡፡

ስለሆነም ወንጀለኛው ያደረሰው ጉዳት 1) ለህይወቱ የሚያሰጋ ነው እንዲሁም 2) ሙያዊ ግዴታ ያለበት ነው፡፡

·        እነዚህን ሁለት መስፈርቶች ያሟላ የወንጀል ደረጃ 7 ነው፡፡

·        የእስራት ቅጣቱን ለመወሰን ደረጃ 7 በእርከን 27 ላይ ይወድቃል፡፡

·        በእርከን 27 ላይ የቅጣት መነሻና መድረሻው ከ8 አመት ከ5 ወር እስከ 10 አመት ነው፡፡

·  ዳኛው በዚህ እርከን ውስጥ ቅጣቱን ይወስናል ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ 9 አመት በሚል ሊወስን ይችላል፡፡

እነዚህ መስፈርቶች በተመሳሳይ በ558 እንዲሁም በ559 መሰረት ቅጣት ለመጣል የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ በመካከላቸው ያለው ልዩነት የወንጀል አድራጊው የሞራላዊ ሁኔታ ብቻ በመሆኑ ነው፡፡

አንቀጽ 557 ንኡስ አንቀጽ በጥቅሉ ማቅለያ ነው፡፡

ስለሆነም በ557 (1) ከተመለከቱት ማቅለያዎች ተሟልተው ከሆነ ዳኛው ቅጣቱን ለመወሰን በሰንጠረዡ ወደተቀመጠው መስፈርት መሄድ ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡

የወንጀል ደረጃዎቹ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ የቅጣት እርከኑን ለመወሰን ብቻ ነው ወደ557 የሚሄደው፡፡

ስለሆነም ከዚህ በላይ የተመለከትነው ምሳሌ ማለትም

·        የደረሰው ጉዳት ለህይወቱ የሚያሰጋ ከሆነ እና ሙያዊ ግዴታ እያለበት ከሆነ የወንጀል ደረጃው 6 ነው፡፡

·        በዚህ ደረጃ ላይ ያለ የሚወድቅበት  የቅጣት እርከን 10 ለመቀጮ ደግሞ እርከን 4 ነው፡፡

·      እርከን 10 ቅጣቱ ከ1 አመት ከ6 ወር እስከ 1 አመት ከ10 ወር ነው፡፡ ዳኛው በዚህ ውስጥ ይወስናል ማለት ነው፡፡

·  የመቀጮ እርከን 4 ጣሪያው እስከ ብር 5000 ነው፡፡ ስለሆነም ዳኛው ከዚህ ባልበለጠ መቀጮውን ይወስናል ማለት ነው፡፡

በ557 ውስጥ ያሉት ማቅለያዎች ቢኖሩም በንኡስ አንቀጽ 2 በተመለከተው መሰረት ተጎጂው ፈቃዱን ቢሰጥም ተጎጂው እሺታውን የሰጠው የሚያስከትለውን ውጤት የማይረዳ መሆኑን መረዳት ከተቻለ በ557(1) መሰረት ከተደረሰበት የቅጣት እርከን 7 በመጨመር ቅጣቱ ይወሰናል ማለት ነው፡፡ በዚህ መሰረትም

1.  ደረጃ 1 የቅጣት እርከኑ 5 (ከ6 ወር-9 ወር) የነበረው የቅጣት እርከኑ 12 (ከ2 አመት-2 አመት ከ6ወር) ይሆናል፡፡

2.  ደረጃ 2 የቅጣት እርከኑ 6 (ከ8ወር- 1 አመት ) የነበረው የቅጣት እርከኑ 13 (ከ2 አመት ከ3 ወር-2 አመት ከ9 ወር) ይሆናል፡፡

3.  ደረጃ 3 የቅጣት እርከኑ 7 (ከ1 አመት-1 አመት ከ3 ወር) የነበረው የቅጣት እርከኑ 14 (ከ2 አመት ከ6 ወር- 3 አመት ይሆናል፡፡

4.  ደረጃ 4 የቅጣት እርከኑ 8 (ከ1 አመት ከ2 ወር -1 አመት ከ6 ወር) የነበረው የቅጣት እርከኑ 15 (ከ2 አመት ከ9 ወር-3 አመት ከ3 ወር ይሆናል)

5.  ደረጃ 5 የቅጣት እርከኑ 9(ከ1 አመት ከ4 ወር-1 አመት ከ8 ወር) የነበረው የቅጣት እርከኑ 16 (ከ3 አመት-3 አመት ከ7 ወር ይሆናል)

6.  ደረጃ 6 የቅጣት እርከኑ 10 ( ከ1 አመት ከ6 ወር-1 አመት ከ10 ወር) የነበረው የቅጣት እርከኑ 17 (ከ3 አመት ከ3 ወር-3 አመት ከ11 ወር ይሆናል፡፡

7.  ደረጃ 7 የቅጣት እርከኑ 11 (ከ1 አመት ከ8 ወር-2 አመት ከ2 ወር) የነበረው የቅጣት እርከኑ 18 (ከ3 አመት ከ7 ወር-4 አመት ከ4 ወር) ይሆናል፡፡ ይሁንና ተጨማሪው 4 ወር በህጉ ከተቀመጠው ጣሪያ በላይ ስለሆነ ቅጣቱ ከ4 አመት አይበልጥም ማለት ነው፡፡

በወንጀል ህጉ 556 መሰረት ቅጣቱን ለመወሰን ዳኛው ከግምት የሚያስገባቸው የሚከተሉትን ነው፡፡

በድንጋጌው ቅጣቱን ለመወሰን ከግምት የሚገቡ በድንጋጌው ያሉ ሶስት መስፈርቶች አሉ፡፡

1.  የደረሰው ጉዳት በ555 ከተመለከቱት ውጭ መሆኑ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በ556 መሰረት ጥፋተኛ ተብሎ ስለሚወሰን እናም በድንጋጌው ያሉት ማክበጃዎች ከሌሉ ደረጃ 1 ሆኖ በቅጣት እርከን 2 ውስጥ ስለሚወድቅ ቅጣቱ ከ10 ቀን እስከ ሶስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ይወሰናል፡፡

2.  ከዚህ ሌላ ቅጣቱን ለመወሰን ታሳቢ የሚደረጉት የሚከተሉት መስፈርቶች ናቸው፡፡ 1) ጉዳት ለማድረስ መሳሪያ መጠቀም አለመጠቀሙ፣ 2) የሙያ ወይም ሌላ ግዴታን በመተላለፍ እንደሆነ፣ 3) ተጎጂው በሽተኛ፣ ደካማ ወይም ራሱን መከላከል የማይችል እንደሆነ ናቸው፡፡

3.  ስለሆነም ዳኛው ቅጣቱን ለመወሰን ወንጀል አድራጊው መሳሪያ መጠቀም አለመጠቀሙ፣ የሙያ ግዴታ ያለበት መሆን አለመሆኑን እና ተጎጂው በሽተኛ፣ ደካማ ወዘተ መሆኑን ከግምት በማስገባት ቅጣቱን ይወስናል ማለት ነው፡፡

ለምሳሌ ወንጀል አድራጊው መሳሪያ ተጠቅሟል፣ ተጎጂው በሽተኛ ወይም ራሱን መከላከል የማይችል ነው፡፡ ይሁንና ወንጀል አድራጊው የሙያ ግዴታ የለበትም፡፡

ስለሆነም ሁለቱ ማክበጃዎች ተሟልተዋል ማለት ነው፡፡

ሁለት ማክበጃዎች ተሟልተው ሲገኙ ድርጊቱ የሚወድቀው በወንጀል ደረጃ 3 ላይ ነው፡፡

የወንጀል ደረጃ 3ትን በተመለከተ የተቀመጠው የቅጣት እርከን ለእስራቱ እርከን 7 ሲሆን፣ ለገንዘብ መቀጮው እርከን 5 ነው፡፡

እርከን 7 ቅጣቱ ከ1 አመት እስከ 1 አመት ከሶስት ወር ነው፡፡ ስለሆነም ዳኛው በዚህ ሬንጅ ወይም ፍቅድ ስልጣን ውስጥ ቅጣቱን ይወስናል ማለት ነው፡፡

የገንዘብ መቀጮውን በተመለከተ እርከን 5 እስከ ብር 7000 ድረስ ነው፡፡ ስለሆነም በወንጀል ህጉ አንቀጽ 90 መሰረት ያሉትን መስፈርቶች መሰረት በማድረግ ከብር 7000 ሳይበልጥ መቀጮውን ይወስናል ማለት ነው፡፡

የስርቆት ወንጀልን በሚመለከት የቅጣት አወሳሰን

የስርቆት ወንጀልን በሚመለከት በ665 እና በ669 መሰረት የተለያዩ መስፈርቶች ቅጣቱን ለመወሰን ይውላሉ፡፡

በ665 መሰረት ቅጣት አወሳሰን

በ665 መሰረት ጥፋተኛ የተባለ ከሆነ፣ ደረጃውን ለመወሰን ከግምት የሚገባው በስርቆት ወንጀሉ የተገኘው ጥቅም መጠን ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ደረጃው ይወሰናል ማለት ነው፡፡

1.  የገንዘብ መጠኑ እስከ ብር 100 ከሆነ በደንብ መተላለፍ የሚታይ ስለሚሆን በዚህ ድንጋጌ መሰረት ቅጣት አይወሰንም፡፡

2.  የገንዘብ መጠኑ ከብር 100 በላይ እስከ ብር 1000 ከሆነ የወንጀል ደረጃው 1 ሆኖ የቅጣት እርከኑ 2 ይሆናል፡፡

3.  የቅጣት እርከን ሁለት ቅጣቱ ከ10 ቀን-3 ወራት ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ዳኛው ቅጣቱን ይወስናል፡፡

4.  ይህንን ወደግዴታ ስራ ወይም ወደመቀጮ ሊቀይረው ይችላል፡፡ ወደግዴታ ስራ ሲቀየር አንድ ቀን እስራት ከአንድ ቀን የግዴታ ስራ (8 ሰአት ጋር) እኩል ነው፡፡ መቀጮው ደግሞ እስከ ብር 500 ድረስ ነው፡፡

5.  የገንዘብ መጠኑ ከብር 1000 በላይ እስከ ብር 2000 ከሆነ ደግሞ የወንጀል ደረጃው 2 የቅጣት እርከኑ 4 ይሆናል፡፡

6.  የቅጣት እርከን 4 የቅጣት መነሻው ከ4 ወር-7 ወር ነው፡፡

7.  ወዘተ

ይሁንና በስርቆት ከተገኘው የገንዘብ መጠን በተጨማሪ የስርቆት ወንጀሉ፣

1.  ወንጀል በተፈጸመበት ሰው የእለት ኑሮ ወይም የድርጅቱ ስራ አደጋ ላይ ከወደቀ ከተቀመጠው እርከን በ2 ደረጃ ያድጋል፡፡ በዚህም መሰረት፣

·        የወንጀል ደረጃው 1 ለሆነው የቅጣት እርከኑ 4 ይሆናል፡፡

·        የወንጀል ደረጃው 2 ለሆነው የቅጣት እርከኑ 6 ይሆናል ማለት ነው፡፡

·        ወዘተ…

2.  የተሰረቀው ንብረት ፈንጂ ተቀጣጣይ ነገር ከሆነ በተመሳሳይ እርከኑ በ2 ደረጃ ያድጋል፡፡ በዚህም መሰረት፣

·        የወንጀል ደረጃው 1 ለሆነው የቅጣት እርከኑ 4 ይሆናል፡፡

·        የወንጀል ደረጃው 2 ለሆነው የቅጣት እርከኑ 6 ይሆናል ማለት ነው፡፡

ወዘተ…

3.  በዚህ መመሪያ መሰረት እነዚህ ቅጣቱን የሚያከብዱ ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ የሚያስጨምሩት የእርከን መጠን ይደመራል ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ፣

·    ወንጀሉ በተሰረቀው ሰው ወይም ድርጅት ስራ አደጋ ላይ የጣለ ከሆነ (2 እርከን ጭማሪ) እና የተሰረቀው ንብረት ፈንጂ ወይም ተቀጣጣይ ከሆነ (2 እርከን ጭማሪ) በድምሩ 4 እርከን ያስጨምራል ማለት ነው፡፡

·        ስለሆነም የወንጀል ደረጃው 1 ለሆነው የቅጣት እርከኑ 6 ይሆናል፡፡

·        የወንጀል ደረጃው 2 ለሆነው የቅጣት እርከኑ 8 ይሆናል፡፡

·        ወዘተ

በ669 መሰረት ቅጣት አወሳሰን፣

በዚህ ድንጋጌ መሰረት ዳኛው ቅጣት ለመወሰን የሚጠቀምባቸው መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡ 1) የገንዘቡ መጠን፣ 2) የተሰረቀው እቃ አይነት፣ 3) ድርጊቱን የፈጸመው አድራጊ ማንነት፣ 4) የወንጀል አፈጻጸሙ ነው፡፡

ስለሆነም በ669 መሰረት ጥፋተኛ ነው ተብሎ ከተወሰነ በኋላ ቅጣቱ ሲወሰን ከተራ ቁጥር 2 እስከ ተራ ቁጥር 4 ያሉት  ማክበጃዎች ስለሆኑ በዚህ ደረጃ አንድ ማክበጃ፣ ሁለት ማክበጃ ወይም ሶስት ማክበጃ ተብለው ተለይተዋል፡፡

ምሳሌ

1.  ወንጀል አድራጊው የሰረቀው ብር 2000 የሚያወጣ ነው፡፡

2.  የተሰረቀው እቃ አይነት በ669 (1) ውስጥ ከተዘረዘሩት ዝርዝሮች ውስጥ የሚካተት አይደለም፡፡

3.  የወንጀል አድራጊው ማንነት የወኪልነት ስልጣን የተሰጠው ሆኖ በእጁ የገባውን ንብረት ላይ ነው፡፡

4.  በድርጊቱ አፈጻጸም አንጻር በ669(3) ውስጥ የሚወድቅ አይደለም፡፡

ስለሆነም ሁለት ነገሮች ተለይተዋል፡፡

1.  የገንዘቡ መጠን ብር 2000 ይገመታል፡፡

2.  አንድ ማክበጃ ተሟልቷል፡፡

ስለሆነም በ669 መሰረት እስከ ብር 2000 ሆኖ አንድ ማክበጃ የተሟላ ከሆነ የወንጀል ደረጃው 2 ነው፡፡

በ669 የወንጀል ደረጃው 2 የሆነ የመነሻ ቅጣት እርከኑ 9 ነው፡፡

የቅጣት እርከን 9 ቅጣት ከ1አመት ከ4 ወር- 1 አመት ከ8 ወር ነው፡፡ ስለሆነም ዳኛው በዚህ ማእቀፍ ውስጥ ቅጣቱን ይወስናል ማለት ነው፡፡

የውንብድና ወንጀሎችን በተመለከተ ቅጣት አወሳሰን፣

በ670 መሰረት ቅጣት አወሳሰን

የውንብድና ወንጀል ጥፋተኛ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ቅጣቱን ለመወሰን ዳኛው ከግምት የሚያስገባው ሁለት መስፈርቶችን ነው፡፡ እነርሱም፣

1.  በወንጀሉ ለማግኘት የተፈለገው የንብረት መጠን ግምት፣ (ይህ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ድረስ በገንዘብ ግምት ተለይቶ ተቀምጧል፡፡

2.  የሀይል አጠቃቀሙ፡፡ ይህንን በተመለከተ ሀይል የተጠቀመው እንዴት ነው ለሚለው ሶስት መስፈርቶች ተዘጋጅተዋል፡፡ እነርሱም 1) መሳሪያ ሳይዝ ከሆነ ዝቅተኛ፣ 2) መሳሪያ ይዞ ከሆነ መካከለኛ፣ 3) የጦር መሳሪያ ይዞ ከሆነ ደግሞ ከፍተኛ ይባላል ማለት ነው፡፡

ምሳሌ 1

1.  ወንጀል አድራጊ ብር 8000 የሚገመት ገንዘብ ወስዷል፡፡

2.  የሀይል ተግባሩ የተፈጸመው መሳሪያ በመያዝ ነው፡፡ (መካከለኛ የሚባል የሀይል አጠቃቀም ነው)

እነዚህ ሁለት መስፈርቶች ተሟልተው የሚገኙበትን በሰንጠረዡ ስንመለከት የምናገኘው በደረጃ 3 ነው፡፡

ደረጃ 3 ደግሞ የቅጣት እርከኑ 11 ነው፡፡

በቅጣት እርከን 11 ደግሞ ቅጣቱ ከ1 አመት ከ8 ወር -2 አመት ከ2 ወር ነው፡፡ ስለሆነም ዳኛው በዚህ ውስጥ ቅጣቱን ይጥላል ማለት ነው፡፡

ምሳሌ 2

1.  ወንጀል አድራጊው ብር 8000 የሚገመት ገንዘብ ወስዷል፡፡

2.  ወንጀሉ ሲፈጸም የሀይል ተግባሩን ለመፈጸም የጦር መሳሪያ ይዞ ነው፡፡

እነዚህ ሁለት መስፈርቶች ተሟልተው ሲገኙ በ670 መሰረት የወንጀል ደረጃው ደረጃ 4 ውስጥ ይወድቃል፡፡

ደረጃ 4 የቅጣት እርከኑ 13 ነው፡፡

የቅጣት እርከን 13 የቅጣት መነሻ ከ2 አመት ከ3 ወር- 2 አመት ከ9 ወራት ነው፡፡ ስለሆነም ዳኛው በዚህ ሬንጅ ውስጥ ቅጣቱን ይወስናል ማለት ነው፡፡

በ671 መሰረት የቅጣት አወሳሰን

በዚህ መሰረት ቅጣት ለመወሰን የተቀመጡ መስፈርቶች አሉ፡፡ እነርሱም፣

1.  የገንዘብ መጠኑ፣

2.  ወንጀሉ በቡድን መፈጸሙ ወይም የተጠቀመበት መሳሪያ ናቸው፡፡

ምሳሌ ቁ.1.

1.  የገንዘብ መጠኑ እስከ ብር 2000 ከሆነ

2.  ወንጀሉ በቡድን የተፈጸመ ከሆነ

በ671- ደረጃ 1 ላይ ይወድቃል፡፡ ይህም በቅጣት እርከን 21 ላይ ይወድቃል ማለት ነው፡፡

ምሳሌ ቁ.2

1.  የገንዘብ መጠኑ እስከ ብር 2000 ከሆነ

2.  የሀይል ተግባሩን ለመፈጸም ጉዳት የሚያደርስ መሳሪያ ተጠቅሞ የአካል ጉዳት ያደረሰ ከሆነ፣

በደረጃ 2 ውስጥ ይወድቃል፡፡ የቅጣት እርከኑም 22 ነው፡፡

ምሳሌ ቁ. 3

1.  የገንዘብ መጠኑ እስከ ብር 2000 ከሆነ

2.  ድርጊቱን ለመፈጸም የጦር መሳሪያ የተጠቀመ ከሆነና የአካል ጉዳት ያደረሰ ከሆነ

በደረጃ 3 ውስጥ ይወድቃል፡፡ የቅጣት እርከኑም 23 ይሆናል ማለት ነው፡፡

ደረጃ ላልወጣላቸው ወንጀሎች የቅጣት አወሳሰን

ጥፋተኛነቱ ከተረጋገጠ በኋላ ዳኛው የሚያደርገው የሚከተለውን ነው፡፡

1.  በወንጀል ድንጋጌው ከተቀመጠው መስፈርት አንጻር ወንጀሉን ዝቅተኛ፣ መካከለኛ ወይም ከባድ ብሎ ይለያል፡፡ ለዚህም ምክንያቱን ያስቀምጣል፡፡

2.  በወንጀል ህጉ የተቀመጠውን ቅጣት ከመነሻው እስከ መድረሻው ለአራት እኩል ይከፍላል፡፡ (እርከን 1፣ እርከን 2፣ እርከን 3 እና እርከን 4 ይባላሉ፡፡)

3.  በመቀጠል ለዝቅተኛው እርከን አንድ ውስጥ ቅጣት ይወስናል፣ ለመካከለኛው እርከን ሁለት ውስጥ ቅጣት ይወስናል፣ ለከባዱ እርከን ሶስት ውስጥ ቅጣት ይወስናል፡፡

4.  ከዚህ በመቀጠል፣ የወሰነው ቅጣት በአባሪ አንድ በተያያዘው ሰንጠረዥ የሚወድቅበትን ዝቅተኛ እርከን ይለይና የተቀጣበትን እርከን ያስቀምጣል፡፡ (ማክበጃና ማቅለያ ምክንያቶች ከሌሉ ይህ አያስፈልግም፡፡)

ምሳሌ

1.     ወንጀሉ የተፈጸመው አስገድዶ መድፈር ሲሆን፣ በ620 (1) መሰረት ጥፋተኛ ተብሏል፡፡

2.     በ620 (1) መሰረት ቅጣቱ ከ5 አመት እስከ 15 አመት ነው፡፡

3.     ዳኛው ከተፈጸመው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል አንጻር፣ ለምሳሌ በወንጀሉ ምክንያት የወንጀሉ ሰለባ የሆነችው ሴት የምታውቀውና የምታምነው በመሆኗ እናም ወንጀሉ ሊፈጸምባት ሲሞከር ባደረገችው መከላከል ሀይል በመጠቀም ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባት በመሆኑ ወንጀሉን የሚያከብደው ስለሆነ ‹መካከለኛ› አፈጻጸም ተብሎ ተሰይሟል በማለት ምክንያቱን ያስቀምጣል፡፡

4.     በመቀጠል ከአምስት አመት እስከ አስራ አምስት አመት ያለው ልዩነት 10 አመት ነው፡፡ ይህ ለአራት ሲካፈል እያንዳንዱ ሁለት አመት ከ6 ወር ይሆናል፡፡ ስለሆነም

·        እርከን አንድ-- ከ5 አመት እስከ 7 አመት ከ6 ወር

·        እርከን ሁለት-- ከ7 አመት ከ6 ወር እስከ 10 አመት

·        እርከን ሶስት-- ከ10 አመት እስከ 12 አመት ከ6 ወር

·        እርከን አራት ከ12 አመት ከ6 ወር እስከ 15 አመት ይሆናል፡፡

5. ዳኛው መካከለኛ የወንጀል አፈጻጸም በማለት የመደበው ስለሆነ የሚወድቀው በእርከን 2 ውስጥ ነው፡፡

6.  እርከን ሁለት ከ7 አመት ከ6 ወር እስከ 10 አመት ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ ውስጥ ቅጣቱን ይወስናል ማለት ነው፡፡ ስለሆነም 8 አመት ነው በማለት ወስኗል እንበል፣

7. 8 አመት እስራት እርከን 25 እና 26 ውስጥ ይወድቃል፡፡

8. መመሪያው ዝቅተኛውን እርከን እንዲመረጥ ስለሚያዝ እርከን 25 ይመረጣል ማለት ነው፡፡ (ማክበጃ እና/ወይም ማቅለያ ምክንያቶች ካሉ ለማክበድ ወይም ለማቅለል)

የቅጣት ማክበጃና ማቅለያ በሚኖርበት ጊዜ የቅጣት አሰላል፣

ዳኛው መነሻ ቅጣቱን ከወሰነ በኋላ የቅጣት ማክበጃዎች ሲኖሩ ምን ማድረግ እንዳለበት እንዲሁም የቅጣት ማቅለያ ሲኖር ምን ማድረግ እንዳለበት በመመሪያው ተቀምጧል፡፡

ጠቅላላ ማክበጃና ማቅለያ በሚኖርበት ጊዜ የቅጣት አሰላል፣

ጠቅላላ ማክበጃዎችን በሚመለከት፣

በመመሪያው እንደተመለከተው፣

1.  በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 84 በአምስት ንኡሳን አንቀጾች የተቀመጡት ምክንያቶች እያንዳንዳቸው እንደአንድ ማክበጃ ምክንያቶች ተወስደዋል፡፡ ማለትም በዝርዝሩ ውስጥ ከተመለከቱት ሁሉም ቢሟሉም፣ በከፊል ቢሟሉም አንዱ ብቻ ቢሟላም እንደአንድ ማክበጃ ምክንያት የሚወሰድ ነው፡፡

2.  በዚህ ማክበጃ ምክንያት መሰረት በማድረግ ቅጣቱ የሚከብደው በአንድ የቅጣት እርከን ነው፡፡

3.  ስለሆነም በሚኖረው የማክበጃ ቁጥር መሰረት ቅጣቱ ይከብዳል ማለት ነው፡፡

ምሳሌ ቁ 1

1.  የተፈጸመው ወንጀል ከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ነው፡፡ (አንቀጽ 555)፡፡

2.  የተፈጸመው ወንጀል ደረጃ 6 ሲሆን የቅጣት እርከን 23 ነው እንበል፡፡

3.  በማስረጃ ተረጋግጠው የቀረቡ የቅጣት ማክበጃዎች፣

·        በስግብግብነት፣

·        በተለየ ክፋት ወይም ጨካኝነት

·        የጦር መሳሪያ በመጠቀም ከሆነ

4.  ከዚህ በላይ በተመለከተው መሰረት የተዘረዘሩት ምክንያቶች ሶስት ቢሆኑም በማክበጃነት ያሉት ምክንያቶች 2 ናቸው፡፡ (ስግብግብነትና የተለየ ክፋት ወይም ጨካኝነት በአንድ ድንጋጌ ውስጥ የተመለከቱ በመሆናቸው)

5.  እነዚህ ምክንያቶች ወንጀሉን ለማቋቋምና መነሻ ቅጣቱን ለመወሰን አገልግለው ከሆነ አሁን በድጋሚ በማክበጃነት አይጠቀሱም፡፡

6.  ስለሆነም ዳኛው በሁለት እርከን ወደላይ ቅጣቱን ከፍ ያደርጋል ማለት ነው፡፡ እርከን 25 ይሆናል ማለት ነው፡፡

ጠቅላላ ማቅለያዎችን በሚመለከት፣

1.     በቀላል እስራት ለሚያስቀጡ በአንድ ማቅለያ አንድ እርከን ይቀንሳል፡፡

2.     የቅጣት መነሻቸው 1 አመት ጽኑ እስራት ለሆነ በእያንዳንዱ ማቅለያ ሁለት እርከን ይቀንሳል፡፡ ይሁንና ከስድስት ወር ጽኑ እስራት በታች አይወርድም፡፡

3.     የቅጣት መነሻቸው ከአንድ አመት ጽኑ እስራት በላይ እስከ 7 አመት ጽኑ እስራት ለሆኑ ለእያንዳንዱ ማቅለያ በ2 እርከን ይቀንሳል፡፡ ይሁንና ከአንድ አመት ጽኑ እስራት በታች አይወርድም፡፡

4.     የቅጣት መነሻቸው ሰባት አመትና ከሰባት አመት በላይ ለሆኑ ወንጀሎች በእያንዳንዱ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት ሶሰት እርከን ይቀነሳል፡፡  ይሁንና ከአንድ አመት ጽኑ እስራት በታች አይወርድም፡፡

5.     የቅጣት መነሻቸው እድሜ ልክ ጽኑ እስራት ለሆኑ ወንጀሎች በእያንዳንዱ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት ሶስት እርከን ይቀነሳል፡፡ ይሁንና ቅጣቱ ሲቀል ከአስር አመት በታች አይወርድም፡፡

6.     የቅጣት መነሻቸው የሞት ቅጣት ለሆኑ ወንጀለኞች በእያንዳንዱ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት አራት እርከን ይቀነሳል፡፡ ይሁንና ቅጣቱ ሲቀል ከሃያ አመት በታች አይሆንም፡፡

ምሳሌ

1.  ጥፋተኛው በቸልተኝነት ሰውን በመግደል ወንጀል በመፈጸም በወንጀል ህጉ አንቀጽ 543 (1) መሰረት ጥፋተኛ ተብሎ ተወስኗል፡፡

2.  ዳኛው የፈጸመው ወንጀል ‹ዝቅተኛ› በሚል የወሰነ ሲሆን፣ ዝቅተኛ ለሆነው ወንጀል መነሻ ቅጣቱን በእርከን አንድ ከ6 ወር እስከ 1 አመት ከ3 ወር ባለው ውስጥ 1 አመት በማለት ወስኗል፡፡

3.  በመመሪያው መሰረት 1 አመት እስራት ቅጣት የሚወድቅበት እርከን 6 እና 7 ሲሆኑ ዝቅተኛው እርከን 6 (ከ8 ወር-1 አመት) እንደሚሆን ታውቋል፡፡

4.  የቀረቡ የማቅለያ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

·        ከዚህ በፊት የነበረው የዘወትር ጸባይ መልካም ነበር፡፡

·        ወንጀሉን ያደረገው ባልታሰበና ድንገተኛ አጋጣሚ ነው፡፡

·        ወንጀሉን ከፈጸመ በኋላ በእውነት በመጸጸት ወንጀል ለደረሰበት አስፈላጊውን እርዳታ አድርጓል፡፡

5.  ከዚህ በላይ እንደተመለከተው ሶስት ምክንያቶች ቢጠቀሱም፣ ሁለቱ በንኡስ አንቀጽ 82(1)(ሀ) ውስጥ የሚካተቱ ስለሆነ እንደ አንድ ማቅለያ ምክንያት ነው የሚታዩት፡፡ ስለሆነም ሁለት ማቅለያ ምክንያቶች አሉት፡፡

6.  ወንጀሉ የሚያስቀጣው በቀላል እስራት ስለሆነ ለእያንዳንዱ ማቅለያ የሚደረገው ቅናሽ አንድ እርከን ነው፡፡ ስለሆነም ለሁለት ማቅለያ በሁለት እርከን ሲቀንስ እርከን 4 (ከ4 ወር-7 ወር) በሚለው ውስጥ ይወድቃል፡፡

7.  ዳኛው ቅጣቱን በዚህ ውስጥ 4 ወር ብሎ ሊወስን ይችላል፡፡ ይህንን ወደግዴታ ስራ ወይም መቀጮ ሊቀይረው ይችላል ማለት ነው፡፡

ልዩ ማክበጃና ማቅለያ ምክንያቶች በሚኖሩበት ጊዜ የቅጣት አሰላል፣

1. ተደራራቢነትን በተመለከተ፣

ተደራራቢ ሆኖ በ184 በተመለከተው መሰረት የሚደመር በሆነ ጊዜ ዳኛው ለእያንዳንዱ ወንጀል ቅጣት መነሻ ካስቀመጠ በኁዋላ እነዚህን በመደመር የሚደርስበት ቅጣት የሚወድቅበት እርከን ላይ ቅጣቱ ይቀመጣል፡፡

ምሳሌ፣

      ጥፋተኛው በአንደኛው ወንጀል 2 አመት፣ በሁለተኛው ወንጀል 3 አመት መነሻ ቅጣት ይወሰናል፡፡

      እነዚህ ሲደመሩ 5 አመት ይሆናል፡፡

      5 አመት በቅጣት እርከን 20 እና 21 ውስጥ ይወድቃል፡፡ ስለሆነም ዝቅተኛው ማለትም እርከን 20 የቅጣት መነሻው የሚያርፍበት እርከን ይሆናል ማለት ነው፡፡

      ከዚህ በመቀጠል በማስረጃ ተረጋግጠው የቀረቡ ጠቅላላ ማክበጃና ማቅለያ ምክንያቶችን መሰረት በማድረግ ቅጣቱ ይሰላል፡፡

ተደራራቢ ጥፋቱ በ187 ንኡስ አንቀጽ አንድ ሁለተኛ ፓራግራፍ ወይም ንኡስ አንቀጽ 2(ለ) ከሆነ፣

      ዳኛው ለከፍተኛው ወንጀል መነሻ ቅጣት ካስቀመጠ በሁዋላ ለከፍተኛው ወንጀል ከተቀመጠው ጣሪያ ሳይበልጥ በሁለት እርከን ያከብዳል፡፡

      ቀጥሎም ጠቅላላ ማክበጃ ምክንያቶችን መሰረት አድርጎ በእያንዳንዱ ምክንያት በአንድ እርከን ያሳድጋል፡፡

2. ደጋጋሚነትን በተመለከተ

      ደጋጋሚ ለሆነው ከአንድ እርከን ጀምሮ እጥፍ እስኪሆን ድረስ ቅጣቱን ያሳድጋል፡፡

      በመቀጠልም ጠቅላላ ማክበጃ ምክንያቶችን መሰረት በማድረግ ቅጣቱን ያከብዳል፡፡

3. ልዩ ማቅለያ ምክንያት በሚኖር ጊዜ

በወንጀል ሕጉ ቅጣትን በመሰለው እንዲያቀል በፈቀደ ጊዜ ፍርድ ቤቱ በዚህ መመሪያ በተመለከተው መሰረት ሳይወሰን ቅጣቱን በማቅለል ይወስናል፡፡

የቅጣት አሰላል ቅደም ተከተል (በማሳያ ምሳሌዎች ተደግፍ የቀረበ፣)

የወንጀል ደረጃ ለወጣላቸው የወንጀል አይነቶች

የወንጀል ቅጣቱ አሰላል ቅደም ተከተል፣

1.  የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በዚህ መመሪያ በክፍል ሶስት በተመለከተው መሰረት የወንጀሉ ደረጃን ይወስናል፡፡

2.  በመቀጠልም የወንጀሉ ደረጃ የሚወድቅበትን የቅጣት እርከን በአባሪ አንድ ከተያያዘው የቅጣት ሰንጠረዥ ላይ ይለያል፡፡

3.  በመቀጠልም በእርከኑ በተቀመጠው የቅጣት መነሻና መድረሻ መካከል ባለው ፍቅድ ስልጣን (range) ውስጥ መነሻ ቅጣት ይወስናል፡፡

4.  በማስረጃ የተረጋገጡ ልዩ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች ካሉ በዚህ መመሪያ መሰረት ቅጣቱን አክብዶ ቅጣቱ የሚደርስበትን እርከን በማስቀመጥ ቅጣቱን ይወስናል፡፡

5.  በመቀጠል በማስረጃ በተረጋገጡ ጠቅላላ ማክበጃ ምክንያቶች መሰረት እርከኑን በመጨመር ቅጣቱን ይወስናል፡፡

6.  በማስረጃ በተረጋገጡ ማቅለያ ምክንያቶች መሰረት የሚቀነሰውን እርከን በመለየት ወርዶ እርከኑ የሚያርፍበትን በመለየት ቅጣቱን ይወስናል፡፡

7.  የሚጣለው የእስራት ቅጣት እስከ ስድስት ወር ወይም ከስድስት ወር በታች በሚሆንበት ጊዜ በዚህ መመሪያ ተያይዞ በሚገኘው የቅጣት እርከን ሰንጠረዥ መሰረት በግዴታ ስራ እንዲለወጥ ሊወስን ይችላል፡፡

8.  በቅጣት ማቅለያ ጊዜ የእስራት ቅጣትን ወደ መቀጮ መቀየር እንደሚቻል በህጉ በተደነገገው መሰረት ወደመቀጮ ሲቀየርም በዚህ መመሪያ መሰረት ይሆናል፡፡

ምሳሌ 1

      ጥፋተኛው የወ/ሕ አንቀጽ 665 በመጣስ ብር 3000 የሚያወጣ ንብረት በመስረቅ ተረጋግጦበታል፡፡

      ሁለት ማክበጃ ምክንያቶች መኖራቸው ተረጋግጣል፡፡

      ሶስት ማቅለያ ምክንያቶች መኖራቸው ተረጋግጣል፡፡

የቅጣት አወሳሰን ስርአት፣

1.  በወንጀሉ ከተገኘው ጥቅም በ665 ደረጃ 3 ውስጥ ይወድቃል፡፡ ደረጃ 3 በቅጣት እርከን 6 ውስጥ የሚወድቅ ነው፡፡

2.  የቅጣት እርከን 6 ቅጣት (ከ8 ወር-1 አመት ነው)

3.  ዳኛው በዚህ ሬንጅ ውስጥ መነሻ ቅጣቱን ይወስናል፡፡ ለምሳሌ 10 ወር ሊሆን ይችላል፡፡

ሁለት ማክበጃ ምክንያቶች በመኖራቸው እርከኑን

በሁለት ያሳድጋል፡፡  ስለሆነም

4.  እርከን 6 የነበረው እርከን 8 ይሆናል (ከ1 አመት ከ2 ወር- 1 አመት ከ6 ወር)

ሶስት ማቅለያ ምክንያቶች ስላሉ እርከኑን በሶስት

ሲቀንስ እርከን 5 ላይ ይወድቃል፡

5.  እርከን 5 (ከ6 ወር--- 9 ወር)

6.  በእርከኑ ውስጥ ቅጣቱን ይወስናል፡፡ ለምሳሌ 8 ወር በማለት ዳኛው ሊወስን ይችላል ማለት ነው፡፡

ምሳሌ 2፣

ጥፋተኛው በውንብድና ወንጀል 471 ጥፋተኛ ሆኖ

ተገኝቷል፡፡

      ጉዳት የሚያደርሱ መሳሪያዎችን በመያዝ እገልሀለሁ ብሎ አስፈራርቶ የአካል ጉዳት አድርሳል፡፤

      የተገኘው ጥቅም ብር 1500 ነው፡፡

እንደገና 10000 በማታለል ወንጀል 690 ጥፋተኛ ሆኖ

ተገኝቷል፡፡

      አንድ ማክበጃ ምክንያት እና 3 ማቅለያ ምክንያቶች መኖራቸው ተረጋግጣል፡፡

      በውንብድና ከተፈጸመው ጥፋት አንጻር በ671 ደረጃ 2 ውስጥ ይወድቃል፡፡

      የደረጃ ሁለት የቅጣት እርከን ደግሞ 22 ነው፡፡

      የቅጣት እርከን 22 ቅጣት መነሻና መድረሻ (ከ5 አመት ከ6 ወር- 6 አመት ከ7 ወር ነው)

      ዳኛው በዚህ ውስጥ ሲወሰን 6 አመት ይሆናል ብሎ ወስናል እንበል፡፡

      ለማታለል ወንጀል ከገንዘቡ መጠን አንጻር ደረጃ 4 ውስጥ ይወድቃል፡፡

      ደረጃ 4 ማታለል ለእስራት ቅጣት እርከን 8 ውስጥ ነው፡፡ (ከ1 አመትከ2 ወር - 1 አመት ከ6 ወር)፡፡

      ዳኛው እንበል 1 አመት ከ3 ወር ቅጣት አስቀመጠ፡፡

      ለውንብድና ወንጀል የተቀመጠው መነሻ 6 አመትና የማታለሉ 1 አመት ከ3 ወር ሲደመር 7 አመት ከ3 ወር ይመጣል፡፡

      7 አመት ከ3 ወር የሚወድቅበት እርከን 24 እና 25 ናቸው፡፡

      ዝቅተኛው ስለሚመረጥ እርከን 24 ይሆናል (ለ6 አመት ከ6 ወር- 7 አመት ከ8 ወር፡፡

ጠቅላላ ማክበጃና ማቅለያ ምክንያቶች ከዚህ ቀጥሎ እንደሚከተለው ይሰላሉ፡፡

      አንድ ማክበጃ ምክንያት በመኖሩ በአንድ እርከን ሲያድግ የቅጣት እርከን 25 ውስጥ ይወድቃል፡፡

      ሶስት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ስለአሉ፣ ለከባዱ መነሻው 1 አመት ስለሆነ ለእያንዳንዱ ማቅለያ ምክንያት በሁለት እርከን ይቀነሳል፡፡ ለሶስት ምክንያቶች 6 እርከን ሲቀነስ እርከን 19 ላይ ያርፋል፡፡ (ከ4 አመት- 4 አመት ከአስር ወር)

      ዳኛው በዚህ ውስጥ ቅጣቱን ይወስናል፡፡ ለምሳሌ 4 አመት ከ6 ወር ሊሆን ይችላል፡፡

      በማታለል ወንጀል በመቀጮ ለሚጣለው ቅጣት በእርከን 3 ውስጥ ማለትም ጣሪያው እስከ 3000 ብር ይላል፡፡ ስለሆነም ከብር 3000 ሳይበልጥ ቅጣቱ ይጣላል ማለት ነው፡፡

ደረጃ ላልወጣላቸው የቅጣት አወሳሰን ቅደም ተከተል

      የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በድንጋጌው ከተቀመጠው አንጻር የወንጀሉ ከባድነትን በተመለከተ ‹ዝቅተኛ› ወይም ‹መካከለኛ› ወይም ‹ከባድ› በማለት በቅድሚያ ዳኛው ይለያል፡፡

      ዳኛው ከባድ፣ ዝቅተኛ ወይም መካከለኛ ለማለት ምክንያቱን ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡

      በመቀጠል ጥፋተኛ በተባለበት የወንጀል ድንጋጌ መነሻና መድረሻ መካከል ያለውን ጊዜ ለአራት እኩል ይከፍላል፡፡

ምሳሌ

ቅጣቱ ከ1 አመት - 10 አመት ከሆነ ለአራት ሲከፈል

1.  ከ1 አመት----3 አ/ከ3 ወር (እርከን አንድ)

2.  ከ3 አ/ከ3 ወር----5 አ/ከ6 ወር (እርከን ሁለት)

3.  ከ5አ/ከ6 ወር----7 አ/ከ9 ወር (እርከን ሶስት)

4.  ከ7አ/ከ9 ወር-----10 አመት (እርከን አራት) ይሆናል፡፡

በመቀጠል፣

1.  ዝቅተኛ ተብሎ ለተሰየመው በእርከን አንድ ውስጥ ቅጣቱ ይወሰናል፡፡ (ከ1 አመት-3 አመት ከ3 ወር)

2.  መካከለኛ ለተባለው በእርከን ሁለት ውስጥ ቅጣቱ ይወሰናል፡፡ (ከ3አ/ከ3 ወር- 5 አመት ከ6 ወር)

3.  ከባድ ለተባለው በእርከን ሶስት ውስጥ ቅጣቱ ይወሰናል፡፡ (ከ5 አመት ከ6 ወር-7 አመት ከ9 ወር)

4.  ለምሳሌ በእርከን ሁለት የሚወድቅ ሆኖ ዳኛው 5 አመት ብሎ ሊወስን ይችላል፡፡

5.  የተወሰነው ቅጣት የሚወድቅበት እርከን ይለይና ዝቅተኛው ይመረጣል፡፡

6.  5 አመት እርከን 20 እና 21 ውስጥ የሚወድቅ ነው፡፡

7.  ከዚህ መሀል ዝቅተኛው እርከን 20 ይመረጣል፡፡

8.  ከዚህ ቀጥሎ ደረጃ ለወጣላቸው እንዳለው በተመሳሳይ ቅጣቱ ይሰላል ማለት ነው፡፡

ምሳሌ 2

1.  በወ/ሕ አንቀጸ 540 መሰረት ጥፋተኛ ተብሎ ተወስኗል፡፡

2.  ዳኛው ጥፋቱን እንደክብደቱ ዝቅተኛ፣ መካከለኛ ወይም ከባድ ተብሎ ይሰየማል፡፡ በዚህ ጉዳይ ዝቅተኛ ተብሎ ተሰይማል፡፡

3.  የወንጀል ድንጋጌው የቅጣት ሬንጅ ለአራት ይከፈላል፡፡

      እርከን አንድ (ከ5---9 አመት)

      እርከን ሁለት (ከ9—13 አመት)

      እርከን ሶስት  (ከ13- 16 አመት

      እርከን አራት (ከ16-20 አመት ይሆናል፡፡

ዳኛው ጥፋቱን ዝቅተኛ ብሎ ስለሰየመ የመጀመሪያው እርከን ውስጥ 6 አመት ብሎ ወሰነ እንበል፡፡

4.   6 አመት በዋናው የቅጣት ሰንጠረዠ እርከን ውስጥ የትኛው ውስጥ እንደሚወድቅ እንለያን፡፤ (እርከን 21 እና 22 ናቸው)

5.  ዝቅተኛው እርከን 21 ይወሰድና መነሻ ይሆናል፡፡

ከዚህ በመቀጠል እንደማክበጃ ምክንያቱና ማቅለያ ምክንያቱ ከእርከኑ ወደላይ እየተደመረ ወይም ወደታች እየተቀነሰ ይሰላል ማለት ነው፡፡

ምሳሌ

8.  ጥፋተኛው በቸልተኝነት ሰውን በመግደል ወንጀል በመፈጸም በወንጀል ህጉ አንቀጽ 543 (1) መሰረት ጥፋተኛ ተብሎ ተወስኗል፡፡

9.  ዳኛው የፈጸመው ወንጀል ‹ዝቅተኛ› በሚል የወሰነ ሲሆን፣ ዝቅተኛ ለሆነው ወንጀል መነሻ ቅጣቱን በእርከን አንድ ከ6 ወር እስከ 1 አመት ከ3 ወር ባለው ውስጥ 1 አመት በማለት ወስኗል፡፡

10.         በመመሪያው መሰረት 1 አመት እስራት ቅጣት የሚወድቅበት እርከን 6 እና 7 ሲሆኑ ዝቅተኛው እርከን 6 (ከ8 ወር-1 አመት) እንደሚሆን ታውቋል፡፡

11.         የቀረቡ የማቅለያ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

·        ከዚህ በፊት የነበረው የዘወትር ጸባይ መልካም ነበር፡፡

·        ወንጀሉን ያደረገው ባልታሰበና ድንገተኛ አጋጣሚ ነው፡፡

·  ወንጀሉን ከፈጸመ በኋላ በእውነት በመጸጸት ወንጀል ለደረሰበት አስፈላጊውን እርዳታ አድርጓል፡፡

12.  ከዚህ በላይ እንደተመለከተው ሶስት ምክንያቶች ቢጠቀሱም፣ ሁለቱ በንኡስ አንቀጽ 82(1)(ሀ) ውስጥ የሚካተቱ ስለሆነ እንደ አንድ ማቅለያ ምክንያት ነው የሚታዩት፡፡ ስለሆነም ሁለት ማቅለያ ምክንያቶች አሉት፡፡

13. ወንጀሉ የሚያስቀጣው በቀላል እስራት ስለሆነ ለእያንዳንዱ ማቅለያ የሚደረገው ቅናሽ አንድ እርከን ነው፡፡ ስለሆነም ለሁለት ማቅለያ በሁለት እርከን ሲቀንስ እርከን 4 (ከ4 ወር-7 ወር) በሚለው ውስጥ ይወድቃል፡፡

ዳኛው ቅጣቱን በዚህ ውስጥ 4 ወር ብሎ ሊወስን ይችላል፡፡ ይህንን ወደግዴታ ስራ ወይም መቀጮ ሊቀይረው ይችላል ማለት ነው፡፡

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

1.  በሙከራ ደረጃ ለቀረ ወንጀል፣ ማነሳሳት እና አባሪነትን በተመለከተ ሁለት እርከን ዝቅ ብሎ የቅጣቱ መነሻ ይሆናል፡፡

2.  ዳኛው በህጉ ከተቀመጡት ውጪ ያሉ ማቅለያ ወይም ማክበጃ ምክንያቶችን በሚጠቀም ጊዜ ለጠቅላላ ቅጣት ማክበጃና ማክበጃ በሚኖረው ስሌት መሰረት እርከኑን ይወስናል፡፡

3.  ዳኛው፣ የወንጀል አፈጻጸሙም ሆነ ባህርይው በዚህ መመሪያ ደረጃ በወጣላቸው ሊወከል የማይችል ሆኖ ባገኘው ጊዜ ወይም በዚህ መመሪያ በተቀመጠው መሰረት ቅጣቱን መወሰን ፍትህ የሚዛባ ነው ብሎ ያመነ ከሆነ፣ ምክንያቱን በማስቀመጥ የተለየ ቅጣት ሊጥል ይችላል፡፡

4.  ዳኛው በዚህ እንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 በተደነገገው መሰረት መመሪያው ከሚያስቀምጠው በተለየ እርከን ላይ እንዲያርፍ በማድረግ በሚወስንበት ጊዜ ሁሉ፣  ይህንኑ ለሚመለከተው አካል ማስታወቅ ወይም መረጃውን ማስተላለፍ ይኖርበታል፡፡ ፍርድ ቤቶችም በዚህ መሰረት የሚያሰባስቡትን መረጃዎች ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የማስተላለፍ ግዴታ እንዳለባቸው መመሪያው አስቀምጧል፡፡

የንብረት ግምት በተመለከተ

1.  ወንጀሉ የተፈጸመው በውጭ ገንዘብ ላይ ከሆነ፣ የገንዘቡ ምንዛሪ መጠን ቅጣቱ ሊወሰን ባለበት ጊዜ ባለው ምንዛሪ መሰረት ይሆናል፡፡

2.  በወንጀሉ የተወሰደው ንብረት በሚሆንበት ጊዜ የንብረቱን ግምት በተመለከተ ተከሳሹ ክርከር ካቀረበ እና የተከሳሹ ክርክር ተቀባይነት ቢያገኝ የቅጣት እርከኑን የሚቀየር ከሆነ እና በፍርድ ቤቱ እምነት በአቃቤ ህግ የቀረበው ግምት ምክንያታዊ ያልሆነና ፍትህን ያዛባል ብሎ ሲያምን የራሱን ግምት በማስቀመጥ የወንጀል ደረጃውንና የቅጣት እርከኑን ይወስናል፡፡ 

የመመሪያው አላማና ግብ

በመመሪያው አንቀጽ 3 የሚከተለው ተደንግጎ እናገኛለን

አንቀጽ 3 . የመመሪያው አላማና ግብ፣

1.  የመመሪያው አላማ በወንጀል ፍትህ ስርአቱ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ባረጋገጠ መልኩ  ውጤታማና ተገማችነት ያለው ቅጣት የሚሰጥበትን ስርአት በመመስረት ወንጀል እንዳይፈጸም መከላከል ነው፡፡

2.  መመሪያው የሚከተሉት ግቦች ይኖሩታል፡፡

ሀ. በተቀራራቢና ተመሳሳይ የወንጀል ጉዳዮች መካከል ተቀራራቢነት ያለው የቅጣት አወሳሰን (ወጥነትን) ማረጋገጥ፣

ለ. እንደወንጀሉ ክብደትና አደገኛነት መሰረት ተመጣጣኝ ቅጣት ያለው የቅጣት አወሳሰን ማረጋገጥ ነው፡፡

2. የቅጣት እርከን ሰንጠረዥ

በመመሪያው ቅጣትን ለመወሰን ዝርዝር ሰንጠረዦች ተዘጋጅተዋል፡፡ እነዚህም ነጻነትን የሚያሳጡ ቅጣት ሰንጠረዥ እና የገንዘብ መቀጮ ሰንጠረዥ በሚል ተከፋፍለዋል፡፡

2.1. ነጻነትን የሚያሳጡ ቅጣት እርከን ሰንጠረዥ

ይህ በመመሪያው አባሪ አንድ ሆኖ ተያይዞ የሚገኝ ሰንጠረዥ ሲሆን የወንጀል ሕጉን ዝቅተኛ የቅጣት መነሻ (1 ቀን የግዴታ ስራ) እና ከፍተኛውን የሞት ቅጣት መሰረት በማድረግ 39 ደረጃዎች ያሉት የቅጣት እርከኖች እንዲኖሩት ሆኖ የተዘጋጀ ነው፡፡

አላማው አሁን በወንጀል ህጉ ያለውን በመነሻና በመድረሻ መካከል ያለውን ሰፊ ፍቅድ ስልጣን (discretion) በማጥበብ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 88 ንኡስ አንቀጽ 4 እንደተመለከተው ወጥነትንና ተመጣጣኝነትን ማረጋገጥ ነው፡፡

ሰንጠረዡ ሲዘጋጅ ለእያንዳንዱ የቅጣት እርከን መነሻና መድረሻ ያለው ሲሆን፣ የሚከተሉትን መሰረተ ሀሳቦች መሰረት ባደረገ መልኩ የተዘጋጀ ነው፡፡ 

  1. የቅጣት መነሻቸው ከዝቅተኛው ጀምሮ ከፍ እያለ ሲሄድ በመነሻውና በመድረሻው መካከል ፍቅድ ስልጣን (range) እንዲኖር ሆኖ ተዘጋጅቷል፡፡ (ሬንጁ ዝቅተኛው 3 ወር ሲሆን ከፍተኛው 5 አመት ነው፡፡

የቅጣት እርከን 1 ሬንጁ 3 ወር(በትክክል 2 ወር ከሃያ ቀን) ሆኖ ደረጃ በደረጃ እያደገ ይሄዳል፡፡

ከቅጣት እርከን 12 ማለትም (ከ2 አመት- 2 አመት ከ6 ወር) ጀምሮ ሬንጁ ከስድስት ወር ያላነሰ ነው፡፡

ከእርከን 21 ማለትም (ከ5 አመት መነሻ) ጀምሮ ሬንጁ ከአንድ አመት ያላነሰ ነው፡፡

ከእርከን 29 ማለትም (ከ10 አመት መነሻ) ጀምሮ ሬንጁ ከሁለት አመት ያላነሰ ነው፡፡

ከእርከን 34 ማለትም (ከ15 አመት መነሻ) ጀምሮ ሬንጁ ከሶስት አመት ያላነሰ ነው፡፡

በየደረጃው ያለው የቅጣት እርከን መነሻ ሲቀመጥ፣ ከቅጣት እርከኑ ዝቅ ብሎ ከነበረው የቅጣት እርከን አማካይን መነሻ

በማድረግ የቅጣት መነሻና መድረሻው ተወስኗል፡፡

ለዚህ መመሪያ አላማ የአንድ ቀን እስራት ከአንድ ቀን (8 ሰአት) የግዴታ ስራ ጋር ተመጣጣኝ ተደርጎ ተወስዷል፡፡

በቅጣት ማቅለያ ጊዜ የእስራት ቅጣት ወደመቀጮ እንደሚቀየር በወንጀል ሕግ አንቀጽ 179 የሚደነግግ በመሆኑ ወደመቀጮ

ሲቀየር ስንት ሊሆን እንደሚችል በሚያሳይ መልኩም የቅጣት እርከኑ ተዘጋጅቷል፡፡

 

2.2. የገንዘብ መቀጮን የሚመለከተው ሰንጠረዥ፣

የወንጀል ህጉን አንቀጽ 90 መሰረት በማድረግ የገንዘብ መቀጮም ደረጃ ወጥቶለታል፡፡

መነሻ ያደረገውም በአንቀጽ 90(1 እና 2) መሰረት ነው፡፡

ዝቅተኛ መነሻ ግን ለሁሉም ተመሳሳይ በህጉ የተመለከተው ነው፡፡  (10 ብር እና 100 ብር)

በዚህ መሰረት የገንዘብ መቀጮ ከዝቅተኛው ጣሪያ 1000 ብር እስከ ብር 500 ሺህ ሊደርስ በሚችል መልኩ

ተዘጋጅቷል፡፡

3. መመሪያው የሚመራባቸው አጠቃላይ ድንጋጌዎች፣

  1. በወንጀል ሕግ 189 ፍርድ ቤቶች ቅጣትን ሲወስኑ መጀመሪያ ማክበድ እንደሚገባቸው ቀጥለው ደግሞ ማቅለያ ምክንያቶችን መሰረት በማድረግ ማቅለል እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡ ይህም ቅጣቱን ለማክበድ በመጀመሪያ መነሻ ቅጣት ሊወስኑ እንደሚገባ ያመለክታል፡፡ ስለሆነም ዳኞች ማክበጃና ማቅለያ ምክንያቶችን መሰረት አድርገው ቅጣት ከመወሰናቸው በፊት መነሻ ቅጣት ማስቀመጥ እንደሚገባቸው ያመለክታል፡፡ ስለሆነም ዳኞች በቅድሚያ መነሻ ቅጣት ሊያስቀምጡ እንደሚገባ መመሪያው ያስገድዳል፡፡
  2. በወንጀል ህጉ አንቀጽ 88 ንኡስ አንቀጽ 4 ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቅጣት አወሳሰን ወጥነትና ትክክለኛነትን ለማረጋገጥ መመሪያ እንደሚወጣ ይደነግጋል፡፡ ከዚህ በመነሳትም ወንጀሎችን በተመሳሳይ ደረጃ የሚያስቀምጣቸውን ባህርይ መሰረት በማድረግ ለተመሳሳይ ወንጀሎች ተመሳሳይና ተቀራራቢ ቅጣት መቅጣት፡፡ (ወጥነት)፣ እንዲሁም የወንጀል ፍሬነገሩ ተመሳሳይ ቢሆንም እንደወንጀሉ ከባድነትና አደገኛነት ደረጃዎችን በማውጣት ቅጣት መቅጣት ( ተመጣጣኝነት/ትክክለኛነት) ለማረጋገጥ እንዲቻል ለወንጀሎች የወንጀል ደረጃ ሊወጣላቸውና በዚህ መሰረት ቅጣቱ ሊወሰን እንደሚገባ ያስቀምጣል፡፡
  3. ህግ አውጪው ለእያንዳንዱ የወንጀል ድርጊት የቅጣት መነሻና መድረሻ ያስቀመጠ ሲሆን፣ ይህም እንደወንጀሉ ሁኔታ ከመነሻው ጀምሮ ቅጣቱን ሊወስን እንደሚችል የሚያሳይ ነው፡፡ ስለሆነም በወንጀሉ ከባድነት ወይም አፈጻጸም ቀላል የሚባለው ለወንጀሉ ከተቀመጠው መነሻ ቅጣት ጀምሮ እንደወንጀሉ ከባድነት ደረጃ በደረጃ እያደገ በሚሄድ መልኩ ቅጣቱ ሊወሰን እንደሚገባው ያስቀምጣል፡፡
  4. ህግ አውጪው በወንጀል ልዩ ክፍሉ ለእያንዳንዳንዱ ወንጀል ያስቀመጠው ጣሪያ ላይ የሚደረሰው ጠቅላላ ማክበጃ ምክንያቶች ሲኖሩ እንደሆነ ያመለክታል፡፡ ስለሆነም ማክበጃ ምክንያቶችን መሰረት አድርጎ ቅጣቱ ከመክበዱ በፊት የሚቀመጠው መነሻ ቅጣት የወንጀሉ ከባድነት ከፍ ያለ ቢሆንም (በህጉ ካልተወሰነ በስተቀር (ለምሳሌ ያህል በሞት ይቀጣል፣ በእድሜ ልክ እስራት ይቀጣል በሚል መልኩ ካልተቀመጠ) ጣሪያው ላይ አይሆንም፡

ቅጣቱ እንዲከብድ ህጉ በደነገገ ጊዜ (84) ለቅጣቱ ማክበጃ የሆኑትን ምክንያቶች አይነትና ብዛት እንዲሁም ወንጀለኛው የፈጸመውን ጥፋት ከባድነት በማመዛዘን ፍርድ ቤቱ በዚህ ሕግ ልዩ ክፍል በተመለከተው አግባብነት ባለው ድንጋጌ ከተወሰነው ቅጣት ጣሪያ ሳያልፍ ቅጣቱን ይወስናል፡፡ (አንቀጽ 183)

  1. በተመሳሳይ የቅጣት እርከን ላይ ለሚገኙ ወንጀሎች በቅጣት ማክበጃና ማቅለያ መሰረት የሚኖረው ጭማሪ ወይም ቅነሳ ተመሳሳይ ሊሆን ይገባል፡፡
  2. ዳኞች በተቀመጠው ፍቅድ ስልጣን (range) ከመነሻው እስከ መድረሻው በመመሪያው ያልተመለከቱ ሌሎች ምክንያቶችን መሰረት በማድረግ ለመወሰን ይችላሉ፡፡
  3. መመሪያው በወንጀል ህጉ የተቀመጡትን የቅጣት አወሳሰን ድንጋጌዎች ለማስፈጸም የሚወጣ በመሆኑ፣ በወንጀል ህጉ ውስጥ የተቀመጡትን አጠቃላይ መርሆዎችና ድንጋጌዎች መሰረት አድርጎ እየተተረጎመ ሊሰራበት እንደሚገባ ያስቀምጣል፡፡ 

ቅጣትን የሚመለከቱ የወንጀል ህጉ ድንጋጌዎች ይዘት

ወንጀል ህጉ ሁለተኛ ታላቅ ክፍል (ልዩ ክፍል) ለእያንዳንዱ የወንጀል ድርጊት መነሻና መድረሻ ቅጣት ተቀምጠዋል፡፡ አብዛኛዎቹ የቅጣት መነሻና መድረሻዎች የሚከተሉትን ይመስላሉ፡፡

 • ከ1 አመት እስከ 10 አመት
 • ከ3 አመት እስከ 10 አመት
 • ከ5 አመት እስከ 15 አመት

በህጉ ልዩ ክፍል ከተመለከቱት ቅጣቶች በተጨማሪ አጠቃላይ የቅጣት አወሳሰን ድንጋጌዎች አሉ፡፡

 • አንቀጽ 88 (የቅጣቶች አወሳሰን)
 • አንቀጽ 84 (ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃዎች)
 • አንቀጽ 82 (ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያዎች)
 • አንቀጽ 85 (ልዩ የቅጣት ማክበጃዎች)
 • አንቀጽ 83 (ልዩ የቅጣት ማቅለያዎች)
 • ከአንቀጽ 179-189 (ቅጣቱ ሲከብደና ሲቀል ስለሚጣለው ቅጣት መጠን)
 • ከአንቀጽ 190-200 (ቅጣትን ስለመገደብ) ናቸው፡፡

እነዚህን የተለያዩ ድንጋጌዎች መሰረት አድርጎ ቅጣት እንዴት ይወሰናል? በወንጀል ህግ አንቀጽ 189(1) የሚከተለው ተደንግጎ እናገኛለን፡፡

‹በአንድ ወንጀል ላይ ቅጣት የሚያከብዱና የሚያቃልሉ ጠቅላላ ምክንያቶች በተደራረቡ ጊዜ ፍርድ ቤቱ አስቀድሞ ማክበጃ ምክንያቶቹን ከግምት በማስገባት ያከብድና ቀጥሎ የሚያቃልሉትን ምክንያቶች መሰረት አድርጎ ቅጣቱን ያቃልላል›

ይላል፡፡

ከዚህ መረዳት እንደምንችለው መጀመሪያ ለማክበድ ከየት ይነሳል? የሚል ጥያቄ እንድናነሳ ያደርገናል፡፡ ስለሆነም በግልጽ ባይቀመጥም ዳኛው፣

 • በቅድሚያ መነሻ ማስቀመጥ እንደሚኖርበት፣
 • ቀጥሎ ማክበጃ ምክንያቶች ከአሉ ቅጣቱን ማክበድ እንደሚኖርበት፣
 • ቀጥሎ ማቅለያ ምክንያቶች ከአሉ ቅጣቱን ማቅለል እንደሚኖርበት፣

ያስረዳል፡፡

ይሁንና፣

 • መነሻው ስንት ይሁን? በሕጉ መልስ የለም፡፡
 • ማክበጃዎች ሲኖሩ በምን ያህል ሊከብድ ይገባል ? በሕጉ መልስ የለም፡፡
 • ማቅለያዎች ሲኖሩ በምን ያህል ሊቀል ይገባል ? በሕጉ መልስ የለም፡፡

ስለሆነም በወንጀል ህጉ የተቀመጡትን የቅጣት ድንጋጌዎችና ስለቅጣት አወሳሰን የተቀመጡት ድንጋጌዎች በፍርድ ቤት የሚሰጡ ቅጣቶች፣

 • ወጥነት፣
 • ትክክለኛነት ያለው፣

ለማድረግ የሚያስችሉ አይደሉም፡፡

የቅጣት ውሳኔዎች ግምገማ

ቅጣት የተሰጠባቸው መዝገቦችን ስንመለከት፣

አቃቤ ህግ፣

 • ቅጣቱ ከብዶ ይወሰን፣
 • ተመጣጣኝ ቅጣት ይሰጠው፣

ከሚል ባለፈ ከብዶ ሲባል ከባዱ ምን ያህል እንደሆነ፣

 1. መነሻው ስንት ሆኖ ሊከብድ እንደሚገባ፣
 2. ተመጣጣኝ የሚሆነው ምንእንደሆነ ፣

የሚያመለክቱ አይደሉም፡፡

በተከሳሽ በኩል የሚቀርቡ የቅጣት አስተያየቶችም ጥቅል ሆነው ከሚቀርቡ በስተቀር ተመሳሳይ ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡ዳኛው ቅጣትን ሲወስንም፣ ቅጣትን ለማክበድ፣

 • የወንጀል ሪከርድ አለው
 • የወንጀል አፈጻጸሙ አደገኛነት አለው፣
 • ድርጊቱ የተፈጸመው በአፍቅሮ ንዋይ በመሆኑ የሚሉ ምክንያቶችን በመጥቀስ፣

ቅጣቱን ለማቅለል

 • የወንጀል ሪከርድ የለውም ስለሆነም አደገኛ አይደለም፡፡
 • የቤተሰብ አስተዳዳሪ ነው፡፡ ወዘተ የሚሉ ምክንያቶችን በመጥቀስ፣

ቅጣት ይወስናል፡፡

ይሁንና ዳኞች እነዚህን ምክንያቶች ይጥቀሱ እንጂ፣

 • በየትኛውም መዝገብ ቅጣቱን ለመወሰን መነሻው ስንት መሆን እንዳለበት ተመልክቶ አይታይም፡፡
 • በማክበጃነት የቀረቡትንና በማቅለያነት የቀረቡትን ምክንያቶች የሚቀበለውና የሚቀበሉትንና የማይቀበሉትን ከለዩ በኋላ፣ ከምክንያቶቹ ጋር ግንኙነቱን ለማስረዳት በማይቻል መልኩ በጥቅሉ የቅጣቱ መጠን ይቀመጣል፡፡

ስለሆነም፣

 • መነሻ የቅጣት መጠኑ ስንት እንደሆነ፣
 • በማክበጃነት የተቀመጡት ምክንያቶች ቅጣቱን በማክበድ ያላቸው አስተዋጽኦ እንዲሁም
 • ማቅለያ ምክንያቶች እንዴት አገልግለው ቅጣቱ እንደቀለለ፣

ለማወቅ አይቻልም፡፡

ከዚህ አጠቃላይ ግንዛቤ በመነሳት በአገራችን ቅጣት አወሳሰን ምክንያታዊነት የጎደለው፣ በእርግጥም የተጣለው ቅጣት አግባብነት ያለው መሆኑን ለማስረዳት አይቻልም፡፡ በዚህም ምክንያት፣

በአንድ ዳኛ በተለያየ ጊዜ ወይም በተለያዩ ዳኞች ተቀራራቢና ተመሳሳይ ለሆኑ ወንጀሎች የሚሰጡ የተለያዩ ቅጣቶች መኖራቸው፣

ከዚህም የተነሳ በቅጣት አወሳሰን ተገማችነት የሌለው መሆኑ፣

ቅጣት አወሳሰን ግልጽነት የሌለውና በፍትህ አካላቱ ባለሙያዎች ላይ ተጠያቂ ለማድረግ የማያስችል ሆኖ እናገኘዋለን::

Although punishment has been a crucial feature of every legal system, a widespread disagreement exists over the moral principles that can justify its imposition.

One fundamental question is why and whether the social institution of punishment is warranted.  The second question concerns the necessary conditions for punishment in particular cases. The third relates to the degree of severity that is appropriate for particular offenses and offenders.

Since punishment involves pain or deprivation that people wish to avoid, its intentional imposition by the state requires justification. The difficulties of justification cannot be avoided by the view that punishment is an inevitable adjunct of a system of criminal law.

The question: "what are the rationales behind punishment?’’ remains unanswered.  This question will soon take us to the theories of punishment. Generally, punishment contributes to the preservation of public order through inflicting the wrong doer who is expected to behave in the future to become a good citizen and to inspire fear in any one "who witness the punishment of wrong doer, and to make them prudent."  This is the primary rational of punishment. 

There are theories of punishment of which the following are generally been regarded as the most important

Retribution

It is the oldest of the rationales for punishment tracing its root to the Bible.  For instance Leviticus 24:17-22 reads:

" when one man strikes another and kills him ,he shall be put to death … when one injures and disfigures his fellow country man, it shall be done to him as he has done; fracture for fracture, eye for eye, tooth for tooth."

Retribution is often assimilated to revenge, but a public rather than a private one.  Retribution is based on the principle that people who commit crimes deserve punishment.  In that sense, the theory is backward looking: the justification for punishment is found in the prior wrong doing.

Retribution theory punishes the offenders because they are deserving of punishment. It says to the offenders: "you have caused harm to society; now you must pay back society for that harm. You must atone for your misdeeds.

Implicit in retribution is the condemnation or denunciation of both the offender and the offending behavior.

Retribution, however, is not in a kind.  Society cannot rape rapist or steal from thief, although in some countries death penalty is exacted for murder.

Instead, the law tries to convert the offence into a common currency to impose a sentence which is proportional to the harm caused.

In this regard, it might be observed that retribution, with its emphasis on proportional punishment, provides a basis for the grading of offences.

Deterrence

Deference is one of the several rationales of sentence.  It is described as 'consequentionalist' in the sense that it looks into the preventive consequence of sentence.  It relies on the threats and fear though sentencing.  Deterrence is based on the belief that crime is rationale and can be prevented if people are afraid of penalties.

There are two types of deterrence; namely General deterrence and specific deterrence.

General Deterrence

Knowledge that punishment will follow crime deters people from committing crime, thus reducing future violations of right and the unhappiness and insecurity they would cause.

It aims at deterring other people who witness punishment and like minded with the offender, from committing this kind of offence.

It makes other people prudent by inducing the public to refrain from criminal conduct by using the defendant as an example of what will befall a person who violated the law.

J. Bentham, the main proponent of this theory argues that all punishment is pain, and should therefore be  avoided, however, it might be justified if the benefit in terms of general deterrence would outweigh the pain inflicted on the offender punished and if the same benefits could not be  achieved by non-punitive methods

Sentence should therefore be calculated to be sufficient to deter other from committing this kind of offence, no more no less.

Specific Deterrence

A goal of criminal sentencing that seeks to prevent a particular offender from engaging in repeated criminality.  The actual imposition of punishment creates fear in the offender that if the repeats his act, he will be punished again.

Adults are more able than small children to draw conclusions from the punishment of others, but having a harm befall oneself is almost always a sharper lesson than seeing the harm occur to others.  To deter an offender from repeating his actions, a penalty should be severer enough to outweigh in his mind the benefits of the crime.

For the utilitarian, more severe punishment of repeat offenders is warranted partly because the first penalty has shown itself ineffective from the stand point of individual deterrence.

Incapacitation

Incapacitation is the use of imprisonment or other means to reduce the likelihood that an offender will be capable of committing future offenses.

It makes the offender incapable of offending for substantial period of time.  It is popular form of "public protection" and sometimes advanced as general aim.

This pragmatic theory argues that offenders need to be separated from the rest of the society in order to protect ordinary citizens from their committing other offences. The implicit premise is that, if not incarcerated, offender will continual in their criminal way.

In ancient times, mutilation and amputation of the extremities were sometimes used to prevent offenders form repeating their crimes.

Modern incapacitation strategies separate offenders from the community to reduce opportunities for further criminality.  Incapacitation is sometimes called the " lock' em up approach’’ and  forms the basis for the movement forward prison  "warehousing."

It is confined to particular group, such as "dangerous" offenders, career criminals or other persistent offenders.

                                                                

Capital punishments and severing of limbs could be included as incapacitation punishment. But there are formidable humanitarian arguments against such irreversible measures.

What has been claimed for incapacitating sentencing is the imposition of long, incapacitating custodial sentence on the offender deemed to be dangerous.  The proponents of this theory argue that one can identify certain offenders as dangerous who are likely to commit serious offence if released into community in the near future and the risk of victims are so great that it is justifiable to detain  such offender for long period.

Opponents of this theory have chief objection: over prediction.  They say that incapacitating sentencing draws into its net more non dangerous than dangerous offenders. For instance, in the UK study indicates that only 9 of 48 offenders predicted as dangerous committed dangerous offences within five years of release from prison.

An equal number of dangerous offences were committed by offenders not classified as dangerous.

This indicates that there are hundreds of offenders serving discretionary sentence of life imprisonment in the UK and Wales, imposed on the ground of predicted dangerousness, and  there is no way of telling, whether the predictions on which these sentences rest are not over caution in ratio of two – to – one.

Rehabilitation

Rehabilitation seeks to bring about fundamental changes in offenders and their behavior.   As in the case of deterrence, the ultimate goal of rehabilitation is a reduction in the number of criminal offenses.  Whereas deterrence depends upon a fear of the law and the consequences of violating it, rehabilitation generally works through education and psychological treatment to reduce the likelihood of future criminality. This theory argues that too much alternation was given for crime, and little was given to the criminals

This theory rests upon the belief that human behavior is the product of antecedent causes that these causes can be identified, and that on these basis therapeutic measures can be employed to effect changes in the behavior of the person treated.

This requires modification of attitudes & behavioral problem through education and skill training. The belief is that these might enable offenders to find occupation other than crime

If a dangerous offender needs to be located until he/she is no longer dangerous, it is the duty of the state to rehabilitate the offenders so that they can be released.  That is why rehabilitation is termed as the other side of restraint coin.

This theory closely related with forms of positivist criminology which locates the causes of criminality in individual pathology or individual maladjustment whether psychiatric, psychological or social.

This theory tends to regard the offender as a person in need of help and support.  At says that criminals are socially sick people who need some kinds of treatment.

Social theories of Sentencing.

They are contemporary theories. It is a dissatisfied response to the four "traditional" theories of punishment which deal with sentencing in isolation from its wider social and political setting.  These theories attempt to make sentencing principles more responsive to social condition and community expectation.  Three of these tendencies are:

Barbara Hudson

According to Barbara, priority should be given to crime prevention and to reducing the use of custody by the penal system.  Hence, changes in social policy (employment, education, housing, leisure facilities) are more important to justice than debate about proportionality of sentence.

When coming to sentencing, there should be greater concern with the problems of whole human being than particular pieces of behavior. More emphasis should be given to "rehabilitative’’ opportunities.

Nicola Lacey

The first thing must be the states recognition of its duty to foster a sense of community by providing proper facilities and fair opportunities for all citizens.  Once this is achieved in a community, punishment is justified as re-enforcing the value that has been decided to protect through criminal law.

John Braitwaite & Phillip Petit: Republican Theory of Criminal Justice.

The central value of this theory is dominion, defined in terms of  each citizen’s ability to make life choices with a social and political framework which each citizen has  participated & then to be protected in those choices.

Conflict among Different Theories 

 

For many years, most of the literatures on the subject of punishment were devoted to advocacy of a particular theory to the exclusion of others.

Those who espoused the rehabilitation theory condemned the other theories, while, those who favored the deterrence theory denied the validity of all the others, and so on.

For instance, if criminals are sent to prison in order to be transformed to good citizen by physical, intellectual, and moral training, prison must be turning into dwelling house  far too comfortable to serve  as any effective deterrent to those classes from which criminals are chiefly drawn.

In the cases of incorrigible offenders, there are people incurably bad, or some men who by some vice of nature, are even in their youth beyond the reach of reformative influence.

The application of purely reformative theory therefore, would lead to astonishing and inadmissible result. The perfects system of criminal justice is based on neither the reformative nor the deterrent principle exclusively, but the result of compromise between them.

In this compromise, it is the deterrent principle which would possess predominate influence, and its advocates who have the last word. This is the primary and essential end of punishment. All others are merely secondary and accidental.

It is necessary, then, in view of modern theories and tendencies, to insist on the primary importance of deterrent element in criminal justice.  The reformative element must not be overlooked.

For instance, in case of youth criminals and first offenders, chances of effective reformation are greater than that of adults who have fallen into offences.

Finally' let us evaluate the Federal Criminal Code (2004) inline with these theories. Article of the code declares the object and purpose of the Criminal Code and it reads: The purpose of the Criminal Code   of the Federal Democratic Republic of Ethiopia is to ensure order, peace and security of the State, its peoples, and inhabitants for the public good.

It aims at the prevention of crimes by giving due notice of the crimes and penalties prescribed by law and should this be ineffective, by providing for the punishment of criminals in order to  deter them from committing another crime and make them a lesson to others , by providing  for their reform  and measures to prevent  the  commission of further crimes.( Emphasis added by the writer)

The first paragraph of the above Article talks about the overall purpose of the Criminal Code, whereas the second paragraph states how that purpose can be attained, As it is clearly stated ,  the Criminal Code  has been designed to attain it  by preventing the commission of the crime. Prevention of the crime in turn is intended to be attained by giving due notice of the crime and penalties prescribing in the Code Due notice the public may be given to the public through publication of the Criminal Law and this may in turn gives access to all citizens and inhabitants to be aware of what acts or omissions are crimes and the respective penalties.

This does not mean that all those who are aware of the crime and penalties may always respect the law always. It is true that people may disregard and transgress the law. It is this situation the criminal Law in advance predicts and provides penalties when saying: "…should this be ineffective, providing for the punishment of criminals…"

The very Provision states the prime purpose of punishment. As it is clearly stated under this Article, the vital purpose of punishment is to deter the offender from committing fresh crime  and also to deter other with inclination to commit a crime .This conclusion can be inferred from the phrases  of the provision which says : …in order to deter them from committing another and make them a lesson to others….

This is also emphasized in the Preface of the Code on page IV, and it reads: Punishment can deter wrongdoers from committing other crimes; it can also serve as a warning to prospective wrongdoers.

Hence, the words lesson used in Art.1 and warning used in the Preface address the general deterrence, while the Code directly intends to deter the wrongdoers.

One can also understand the fact that the Code has also incorporated a rehabilitation theory for the Code clearly states this when it says: …by providing for their reform and measure …

The rehabilitative approach of the Code is further elaborated in the Preface page IV and it reads: …with the exception of the death sentence, even criminals sentenced to life imprisonment can be released on parole before serving the whole term; in certain crimes convicts can be released on probation with out the pronouncement of sentence or without enforcement of sentence pronounced. This helps wrongdoer to lead a peaceful life and it indicates the major place with the Criminal Law has allocated for their rehabilitation(Emphasis supplied)

The Preface further reads:  The fact that the wrongdoers instead of being made to suffer while in prison take vocational training and participate in academic education which would benefit them upon their release, reaffirms the great concern envisaged by the Criminal Code about the reform of criminals. (Emphasis supplied)

Different kinds of punishments are devised in the Code to attain the purposes. Just to mention some, simple imprisonment and pecuniary penalties have deterrent value. The same holds true for warning, reprimand, admonishment and apology from secondary penalties. (Art.122)  It may also give a chance to an offender for rehabilitation.

Neither Art.1 nor the Preface makes reference to incapacitation theory. However, does not mean that the Code has not adopted this theory, because this can be inferred from the following kinds of punishment: rigorous imprisonment that may be imposed on offenders committed serious offence. As it is provided for as per Art. 108 of the Code, besides punishment rigorous imprisonment is intended to separate the offender from the community  by applying strict confinement of the criminal for special protection to society. But the law tried to attain trio of purpose by rigorous imprisonment: incarceration, rehabilitation, and deterrence.

Death penalty is another typical example of incapacitation incorporated in the Code. Furthermore it has deterrence value to others with similar potential to commit a crime.

To mention secondary penalties of incapacitate nature, suspension and withdrawal of license, Art. 142 prohibition and closing of undertaking, Art.143 Measures entailing a Restriction on personal liberty, Arts.145 and the following and etc.

One can rightly say that the Ethiopian Criminal Code has followed the modern approach because it has incorporated different types of theories and different kinds of penalties are incorporated to serve these purposes. However, no single punishment is devised just to serve a single function of punishment.